አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱሁ
ወደ ተወዳጁ ሐድራ-ቲዩብ እንኳን በደህና መጣችሁ።
ይህ ቻናል በሐገራችን ታላላቅ ኡለሞች የተጻፉ መድሆችን በታላላቅ ማዲሆች እና በወጣት ሙንሺዶች በየጊዜው ወደናንተ የሚቀርብበት ቻናል ነው።
የትም ያልተሰሙ አዳዲስ እና የድሮ መንዙማ, ነሸዳ,የሰርግ ነሺዳዎ፣የሰርግ ቪዲዮዎች፣ቂሷ፣የቁርአን ተፍሲር እንዲሁም ዳዕዋዎችን ያገኛሉ።
ሰብስክራይብ ያድርጉን ቤተሰብ እንሁን ።
ሐድራ-ቲዩብ Hadra-tube
ሰሞኑን ተወዳጅነት ያገኘው الشيخ إبراهيم الميرغني ስለ ፋጢመቱ ዘህራ ሙሉ ነሺዳ ተለቆዋል ነሺዳውን ለማገኘት ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን)ይጫኑ👇
https://youtu.be/UuDbjZrJtwg?si=iP-mN...
እንደዚህ አይነት ተወዳጅ ነሺዳ ለማገኘት ሐድራ-ቲዩብን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
3 days ago | [YT] | 77
View 8 replies
ሐድራ-ቲዩብ Hadra-tube
ውዶቸ ዛሬኮ ጁሙዓ ነው
አሏሁመሶሌ አላሙሀመድ ወአላአሊ
ሀቢቢና ወረሱሊና ሙሀመድ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም
Subscribe my channel
7 months ago | [YT] | 53
View 1 reply
ሐድራ-ቲዩብ Hadra-tube
ሱማመቱ ኢብኑ አሳል" (ረዲየሏሁ ዓንሁ)
የኛ ፈንታ ﷺ ውቡ ገፅታቸው፤ በዓለማቱ ጌታ (አሏህ) የተወደሰው ታላቅ ጠባይ፥ ስነ ምግባርና ምሉዑ ስብዕናቸው ወደ ኢስላም ተጣሪ ነበር።
ስንትና ስንት ጭፍን ጠይዎችና ወቃሾች፥
ሰይዳችንን ﷺ ባዩበት ቅፅበት ተማርከው ከግራቸው ስር ወድቀዋል!! ሳያውቋቸው (በሩቅ) ይጠሏቸው የነበሩ አለታማ ልቦች፣ (የእሳቸውን) ስብዕና ገሃድ በቃኙበት ቅፅበት በፍቅር ሟሙተዋል!!
ሱማመቱ ኢብኑ አሳል (ረዲየሏሁ ዓንሁ)
ነብዩን ﷺ ቀርቦ ገሃድ ከማዬቱ በፊት እንዲሁ በጭፍን ይጠላቸው የነበር ሰው ነው።
ባንድ አጋጣሚ አገኛቸው፤ ውበታቸው፣ ርህራሄና ይቅር ባይነታቸው ማረከው፤
በይፋ "ሸሐደተይን" በማለት መሰክሮ ወደ ኢስላምም ገባ፤ ወደ ነቢያችን በመቅረብም እንዲህ አለ፦
يَا مُحَمَّدُ وَاللَّهِ مَا كَانَ عَلَى وَجْهٌ الْأَرْضِ أَبْغَضَ إِلَيَّ مِنْ وَجْهِكَ فَقَدْ أَصْبَحَ وَجْهُكَ أَحَبَّ الْوُجُوهِ كُلِّهَا إِلَيَّ
"ሙሐመድ ሆይ! በጌታዬ ይሁንብኝ! በምድር ገፅ ላይ እንዳንቱ መልክ የምጠላው አልነበረም፤ አሁን ደግሞ ከመልኮች ሁሉ አብልጨ የምወደው ያንቱን መልክ ሆኗል"
የነብዩ ﷺ ወዳጆች ሆይ! ስነ ምግባራችን፣ ስብእናችን ወደ ኢስላምና ወደ መልካምነት የሚስብ ይሆን ዘንድ ልንጥር ይገባናል!!
ነብዩን ﷺ መውደድና መከተል ማለትም ይኼው ነው!
ዑስታዝ ሰኢድ አህመድ
8 months ago | [YT] | 94
View 4 replies
ሐድራ-ቲዩብ Hadra-tube
እናመሰግናለን 10k ገብተናል
9 months ago | [YT] | 23
View 1 reply
ሐድራ-ቲዩብ Hadra-tube
አንከቡት (ሸረሪት) በአራት ቦታዎች ላይ ድሯን አድርታለች
1.ነብያችን ከአቡበከር ሲዲቅ ጋር ወደ መዲና ሲጓዙ በዋሻ ውስጥ ድሯን አድርታ ከጥላት ሽፍናቸዋለች።
2.አቡዱላህ ኢብኑ ኡነይስ ነብያችን አንድ ከሀዲን ለመግደል በላኩት ጊዜ ያንን ከሀዲ ገሎ እራሱን ቆርጦ ይዞ ከሗላው እሱን ለመፈለግ በመጡ ጊዜ ዋሻ ውስጥ ገባም ሸረሪቷም የዛን ግዜ ድሯንም አድረታለታለች።
3.ዘይኑል አቢዲን ቢን ሁሰይን በዟሊሞች እራቁታቸውን በተሰቀሉ ጊዜ ሰውነታቸው በሙሉ በድሯ ሸፍናቸዋለች።
4.ነብዩሏህ ዳውድ ላይ ጧሉት የሚባለው ጥላት በሚፈልግባቸው ጊዜ ድሯንም አድርታለች ሸፍናቸዋለች።
ምንጭ፦ኪታብ ነዋዲር የኢማሙ ቀልዩቢ
9 months ago | [YT] | 69
View 0 replies
ሐድራ-ቲዩብ Hadra-tube
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!
አሽሩኝ ነብዬ በጀማል ነዝራሁ!
የወለላው ነቢ ሥም አንጀት ያምማታል። የፍቅራቸው ጥዝጣዜ አጥንት ይሰረስራል። የህመም እርካታው ልብን ተሻግሮ ጉበት ይዘልቃል። ከወዳጃቸው ዓይን የእንባ ጅረት ይፈልቃል። ሙሒቡ የናፍቆት ነበልባል ውስጥ ውስጡን ሲለበልበው ሩሑ የምታሰማው እሪታ ከምድር ቀበሌ እድርተኞች አልፎ የሰማይ መላዕክትን ያናጋል።
ነቢ ፊት በአዘል ኑር ሆነው ተኸልቀው በሠይድ አደም ጀሰድ የቀልብ ቦታ ላይ ተደላደሉ። ያንን ኑር ኢብሊስ ቢመለከተው ደነገጠ። ነፀብራቁ ሸቃዋውን ገልጦ አወጣበት። አደም ሶፍዩላህ በዚያ ኑር ተጠበቁ። ሠይድ አደም ነብዩን ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በዛት አላዩም። ግና አንድ ቀን የሰማይ ቀበሌን፣ የጀነት ግቢን፣ በይተል መዕሙርን እና ዓርሹንም ፈርሹንም ተዛዙረው ሲጎበኙ አንዳች የሚያምር የቀለም አለላ ተመለከቱ። "ላኢላሀ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" ሲል ተነበባቸው። የድንገቴ ሰርፆ በሩሐቸው አደረ። ማዕናው ቢጠናቸውም ቸል አላሉትም። እየሞጠሉት ሰነባበቱ። ጣማቸውና ከረሙበት። የነቢ ነገር እንኳን እርዳታቸው ተጠርቶ፣ የሥማቸው ነዝራ ብቻ ሒርዝ ነው። በነቢ ኑር የተቃጠለው ኢብሊስ አድብቶ በጀነት ግቢ ዘለቀና "ያቺን ዛፍ ቅመሷት" ብሎ አቡና አደምን ወሰወሰ። አደም ሶፍዩላህ ከባለቤታቸው ጋር ሆነው ቀመሷት። ከመላኢካ ሊበልጡ ስሜት እና ነፍስያ ተደርጋባቸው፣ መርሳትም ተጭኗቸው እንጂ የአላህ እንቁ ኸልቅ እንዴትስ የጌታቸውን የሐይባ ሸማ ከደረቡ ኋላ በጠላት እጅ ይወድቃሉ?! ሐሸ‐ሏህ! ያን ጊዜ የለበሱት ቀሚስ ከላያቸው እየበረረ ጠፋባቸው። የሹመት ካባ እና ጡሩራቸው ሸሻቸው። የተቀመጡበት ዙፋን ከዳቸው። ወዲያው ታድያ ያ የኑር መላ ታወሳቸው። በግንባራቸው ተደፉና "ጌታዬዋ በሙሐመድ ሥም ይሁንብህ ማረኝ!" ብለው ተማፀኑ። በሠይዲ ስም ተለምኖ እምቢ አይልምና ተቀበላቸው።
አባታችን አደም ወደ ምድር በመላኢካ ታጅበው ሲወርዱ ሀዘን በርትቶባቸው ነበር። ይሄን ያየው ሠይድ ጂብራኢል ሊያፅናናቸው ፈለገ። ከለውሁ ላይ ገላልጦ ቢሻራ ነገራቸው። "አደም ሆይ! አትዘን። ወደ ዱንያ የምትላከው ውዱን ሒርዝህን፣ ጥንፍፉን ልጅህን ሙስጦፈል‐ዓለሚንን ልትወልድ ነው!" ብሎ አስደሰታቸው። ፊት ገና ሳይወለዱ በሥም እና ቢሻራ ዕይታ መስከር መጥበርበር ጀመሩ። ይህ ዊራሳ ከነብያት ነብያት ተንከባለለ። ጀማሉ በአውሊያኡ ደረት ሁላ ተቀበረ። ከአደም ሺህ ዓመታትን ተሻግሮ በሠይድ ዩሱፍ ወጅህ በኩል ፈለቀ። ለአባታቸው የዕቁብም ይደንቃቸው ነበረ። መቼስ ጌትዬው ቀድሮት ለዙለይኻም ተነበባት። በዕይታው ሰክራ መነመነች። ሚልኳ አድርጋው አሳደገችው። መች በዚህ ጠገበች ከመንፈሷም ልታቆራኘው ጣደፈች። የናፍቆቱ ጠሀይ ለብልቦ አጃጃት። በዚያኛው በኩል ከንዓን ተቀምጠው ሠይድ የዕቁብ ይንሰቀሰቃሉ። ኑሩን ለመመልከት ይባዝናሉ። ዓይናቸውን አጥተው አብቅተዋል። አንድ እለት የአያታቸውን ውርስ ይዘው ቤቶቻቸውን እያስተማሩ ነው። "አሕመድ የሚባል ነብይ ይመጣል" እያሉ። አፍታ ቆይቶ ንፋሱ ሽው እያለ ደረሰ። የኑሩ ሽታ ዘልቆ አፍንጫቸውን ነዘነዘው። ዓቅላቸውን ኸመረው። የአሕመድን ስም ሲያወሱ የልጃቸው ዩሱፍ ሽታ እያወዳቸው ነበር።
إِنِّي لَأَجِدُ رِيحَ يُوسُفَ
ሲሉ ያመናቸው ባይኖርም እሳቸው ግን አውቀውት ነበር። መልእክተኞቹ የዩሱፍን ቀሚስ አምጥተው ከፊታቸው ሲጥሉት ዓይናቸው በራ። የኔ ነቢ እርሱ ቁርዓን ሥሙ ፉርቃን!
#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሠይዲና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚
2 years ago | [YT] | 20
View 2 replies
ሐድራ-ቲዩብ Hadra-tube
የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል ስለ መብቃቃት
youtube.com/@-hadra-tube4213
2 years ago | [YT] | 19
View 0 replies
ሐድራ-ቲዩብ Hadra-tube
ሺህ አህመድ አምረው ተፈጠሩ በመስህብነት ተዋቀሩ ተሠሩ አማሩ እረቀቁ ፣ ተነጠሩ ። የፈሰሰላቸውን ጸጋ ፣ የተረሰረሰባቸውን ስጦታ አዳበሩ ማንንም ሲማርኩ መልካቹን ሁላ አንደጣሉ ኖሩ ትውልድ ማነን ፈቅደውታል በአደባባይ ተሰጥተው ማስተማሩን መርጠውታል ግርዶ አልጣሉም ገዳም አልገደሙም ኸልዋ አልገቡም ሽሽጉኝ ብለው አልተደበቁም ከመታየት አልራቁም የቀረበ የተጠጋ ሁሉ ያያቸዋል ህልቆ መሳፍርት ተማሪና ተከታዮቻቼው ተማርከው ቀርተዋል ( ያለፉ ሀተታዎችን ይመልከቱ ) እርሳቸው ካዩ ደግሞ እንኳን ሰው አውሬ ያለምዳሉ ማልመድ ብቻም ሳይሆን የግል ሀብታቸው ያደርጋሉ ሼህ ሚስባህ አጠቃልለው ይናገራሉ ፦
በመልክም በጠባይ ነበር የተለየ
ምን አየሁኝ ይላል ኩሌውን ያላየ
በጧትም በማታ በአንድ የነበራችሁ
እሱን ያላያችሁ ምንም አላያችሁ ይላሉ
ወዲህም እራሳቸውም ምርኮኛ መሆናቸውን ይገልጻሉ አብረው እየኖሩ የዓለሙ መብራት የየጁ ሲራጅ
በኩሌው ማረከኝ የራቢዓ ልጅ
እኔም እንደገና ልቤን አፈረሰው
አብሬ እንዳልኖርኩ እንዳላየሁት ሰው ሲሉ ይብሰከሰካሉ
2 years ago | [YT] | 23
View 0 replies
ሐድራ-ቲዩብ Hadra-tube
የነቢ መኝታ ( በሶለዋት)
የአሏህ ሶላት እና ሰላም
በዘንባባው ፍራሽ - በሰሌኑ አልጋ - በገላጣው መሬት ይተኝኛ ለነበረው . ...ግንስ አረፍ ካለው ንጉስ የላቀው! በእንቅልፍ ዐለም ህይወትን ለቀጠለው! ጌታውን በንቃት በእንቅልፉ ለሚያነጋግረው የሃዩል ቀዩም ባሪያ!......ሰይድ ኡመር የሰሌሉን ሰንበር በወጅሁ ሰሌዳ ቢያየው መንታ መንታው ባለቀሰለት < <አብሽር እኛ የአኺራ ሰዎች ልንሆን አትወድም እንዴ ?>> ሲል ወዳጁን ባጽናናው የናፋቂ እንባ
ሰላም ከመኝታው ቀድሞ በርቂይ ጥርሶቹን ለሚፍቀው - ከራሱ ዘንድ ሲዋኩን ወታደር መሳሪያውን እንደሚያኖር በሚያኖረው
ተኩሎ ተዘይኖ ተወልዶም ለኡመቱ ምሪት ሁር አይኑን 3 3 ግዜ ለሚኳለው - መኳሉ በአንዳድን ሌሊቶች 2ቴ ለሚሆነውም,.........ከተሰወከው ሁላ አይንን ኸጣፊው- ከተኳለው ሁላ ልብን ቀጣፊው!.....ከኢሻእ በኋላ ወሬ እና የተወጠረ ሆድን በሚጠላው ዙሁዱን በዙህዱ ውስጥ የረሳው ሰይድ!
ሰላም ከመተኛቱ በፊት ሆዱን በመሙላት ለማይታወቀው! በቀኝ ጎኑ ጋደም ሲል የጁድ ቀኝ እጁን ከቀኝ ጃስሚን ጉንጩ ሥር ለሚያስደግፈው. ........ጌታውን በመሃባ ሳያወሳ አንድም ምሽት አይኑን ያልከደነው- እየዘከረ በሚያሸልበው! በነቃ ግዜም ሲዋኩን አስጠግቶ በአዝካር ሹክሹክታ የለይል ሶላቱን ለሚጀምረው።
ሰላም አይኑ እንጂ ቀልቡ ለማይተኛው..በእንቅልፍ ዐለም መስሎ ሓድረተሏህ ላይ በሯህማን ረውዷ የጀማላትን ሴማ የሚያረቅሰው ጧውስ! እንቅልፉ ከአንቢያእ ወህይ -ከሙሳ ተክሊም በጅጉ ለላቀው - ጋደም ብሎ ኩመል አውሊያኡን ቢነቁ እሚሾመው . ....<የነቁ ይመስልሃል በርግጥም ተኝተዋል- የተኙም ይመስልሃል በርግጥም ነቅተዋል> የተባለው ረምዝ ሚስጥር ! የአውራዱ መርከዝ !
ሰላም ሶሃባው እንቅልፉን ተኝቶ ሲያየው ሊቀሰቅሰው በሚፈራው የጦይባ መሊክ....< ወህይ ላይ ነው ብለን እጠረጥራለን> ሲሉ አይን አይኑን እያዩ በሚጠብቁት...........ኡሙ ሰለማ ሲተኛ ጠብቃ ከግንባሩ ላበት ላይ የመዲናን ሚስክ እና የአዘል አዝሙዱን ከቀዳችበት ኢላሂይ ሺፋ.....ነቅቶባት ቢጠይቃትም < ላበትሁ ሚስካችንን ማጣፈጪያ ነውና ነው> ስትል በሃያእ በመለሰችለት !
ሰላም ዛቱን ቢጫጫነው እንጂ በትግል በማይተኛው - በሌት ሶላቱም ከ11 ረከዐ በማይጨምረው ! ሱረቱል ሙልክን በጌታው ሙልክ ላይ ከቀራው ሁላ ያማረው ! ኢኽላስና ተእዊዙ በምላሱ ላይ አምሮ በተነበበው ! ሰላም በምሽቱ ሱረቱ በኒ ኢስራኢይልን <ሱብሃነለዚ አስራ ቢአብዲሂ> እያለ በውብ ነገሙ ነቢ ዳውድን ሚዝማር ባስተማረው የኢስማኢሉ ቀስተኛ!.........ሰላም የእንቅልፉን ኸበር ሙላው ሪጃል ነቅቶ የኑህን ኡምር ቢዋኘው ጫፉን ለማይደርሰው የአሏህ ቤት ንጣፍ!
ሰላም ይድረሶት ሆዴ
2 years ago | [YT] | 26
View 0 replies
ሐድራ-ቲዩብ Hadra-tube
እንደው ለመሆኑ በሐበሻ ምድር ያሉ የነቢ ወዳጆችን የትኛው ቃል ይገልፃቸው ይሆን? እጃቸው እያጨበጨበ አንጀታቸው ሲቃ፣አይናቸው እንባን ያጎርፋልኮ እናንተዬ።
ከቶ ይሄን "እምቅ ስሜት" ምን ብለን ብንገልፀው ይሻል ይሆን? ያረቢ!!
3 years ago | [YT] | 17
View 0 replies
Load more