➽ Dear students my name is EndgenaYabsera Girma, This Channel gives online education as much as i can with in a detail explanation you can see and use for improve your knowledge.If you have any question ,comments and any other suggestion write down here under a video comment section i give repose rapidly.Education for Computer knowledge & All Exam
Center
📌 እነዚህ ከዚህ በታች የምትመለከቷቸው የእኔ የ Social media linkዎች ናቸው ;Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ !
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
ETHIO2792
ETHIO2792
ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የ11 የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ አይነቶችን ዝርዝር አሳውቋል።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁለተኛው ዙር ተግባራዊ የሚደረጉ 11 የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ ዓይነቶችን ለመተግበር እየተደረገ ያለውን ዝግጅት የተመለከተ መመሪያ አስተላልፏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፓሊሲ ላይ "የሙያና ቴክኖሎጅ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከእድሜያቸው ጋር የተመጣጠነ ሆኖ እንዲሰጥ ይደረጋል" በሚል አቅጣጫ መቀመጡን ያመለክታል።
በዚህ መሰረት በየደረጃው የሥራና ተግባር ትምህርት ከሌሎች ትምህርቶች ጋር ተቀናጅቶ እንዲሁም 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ራሱን ችሎ ተማሪዎች በቀጣይ የሚፈልጉትን ሙያ እንዲመርጡ በሚያስችል መልኩ እየተሰጠ ይገኛል ብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በ11ኛ እና 12ኛ ክፍል በተለያዩ የሙያ አይነቶች ከቀለም ትምህርታቸው ጎን ለጎን ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ12 የሙያ አይነቶች እየተሰጠ እንደሚገኝም ሰርኩላሩ ያትታል።
ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ደግሞ በሁለተኛው ዙር እንዲተገበሩ ለተለዩት 11 የሙያ አይነቶች ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል መርሐ ትምህርቶች እንዲሁም ለ11ኛ ክፍል የተማሪ ሞጁሎችና የመምህር መምሪያዎች ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።
በመሆኑም እነዚህን ተጨማሪ የሙያ አይነቶች ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ11ኛ ክፍል ለማስጀመር :-
• የክልሉ/የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ዝርዝር እቅድ በማዘጋጀት እና እቅዱን ለማከናወን በጀት በመያዝ የሙያ አይነቶችን በትምህርት ቤት እና በተማሪዎች ደረጃ በማስመረጥ፣
• የየሙያ አይነቱ መምህራንን በመቅጠር፣
• የመማሪያ ማስተማሪያ ግብዓት በሂደት በማሟላት፣
• መምህራንን እና የትምህርት አመራሮችን በማሰልጠን እና የህዝብ ንቅናቄ ስራዎችን በማከናወን ትምህርቱን ለማስጀመር ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የ11 የሙያ አይነቶችን ዝርዝር አሳውቋል።
የሙያ አይነቶቹ ፦
- ብረታ ብረት ሥራ ቴክኖሎጂ፣
- አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣
- አልባሳት ቴክኖሎጂ፣
- ህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋት፣
- ቧንቧ ስራ፣
- ሶፍትዌር ማበልጸግ፣
- ሰብል አመራረት፣
- ጤና ክብካቤ አገልግሎት፣
- ሆቴል አገልግሎት፣
- ፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት እንዲሁም ምግብ ዝግጅት ናቸው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ/ም
2 days ago | [YT] | 9
View 0 replies
ETHIO2792
ሰበር ዜና ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም.
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም. የ8ኛ ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ !
ተፈታኝ ተማሪዎች በኮምፒውተር ወይም በስልካቸው የድር መፈለጊያ (Web browser) በመጠቀም፡-
👉 ለ 8ኛ ክፍል amhara.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመክፈት፣
👉 ፊት ለፊት በሚታየው ቅጽ (form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) በማስገባት እና First name የሚለው ላይ የመጀመሪያ ስም በአማርኛ በማስገባት “ውጤት ይመልከቱ (Check Your Result)” የሚለውን ቁልፍ በመጫን ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።
በቴሌግራም ቦት አማካኝነት በቀላሉ ለማየት የሚከተሉትን ሂደቶችን ይከተሉ፦
👉ወደ @MinistryResultQMTBOT በመሄድ ቦቱን ያስጀምሩ።
👉ቦቱን ከከፈቱ በኋላ /start የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ።
👉ክልላችሁን ምረጡ
👉ክፍላችሁን ምረጡ፡ የሚሰጡትን አማራጮች በመጠቀም “Grade 8” የሚለውን ምረጡ።
👉የሰባት ዲጂት (7-digit) የምዝገባ ቁጥርዎን በመጻፍ ውጤታሁን ማየት ትችላላችሁ።
1 week ago | [YT] | 1
View 0 replies
ETHIO2792
ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም.የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም. የ6ኛ ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ !
👉 ለ6ኛ ክፍል oromia6.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመክፈት፣
👉 ፊት ለፊት በሚታየው ቅጽ (form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና የመጀመሪያ ስም በማስገባት
“ውጤት ይመልከቱ (Check Your Result)” የሚለውን ቁልፍ በመጫን ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።
በቴሌግራም ቦት አማካኝነት በቀላሉ ለማየት የሚከተሉትን ሂደቶችን ይከተሉ፦
👉ወደ @MinistryResultQMTBOT በመሄድ ቦቱን ያስጀምሩ።
👉ቦቱን ከከፈቱ በኋላ /start የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ።
👉ክፍልዎን ይምረጡ፡ የሚሰጡትን አማራጮች በመጠቀም “Grade 6” የሚለውን ይምረጡ።
👉የሰባት ዲጂት (7-digit) የምዝገባ ቁጥርዎን ያስገቡ።
👉የመጀመሪያ ስምን (First Name) በትክክል በመጻፍ ውጤታሁን ማየት ትችላላችሁ።
1 week ago | [YT] | 0
View 0 replies
ETHIO2792
.
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም. የ6ኛ ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ !
ስለሆነም ተፈታኝ ተማሪዎች በኮምፒውተር ወይም በስልካቸው የድር መፈለጊያ (Web browser) በመጠቀም፡-
👉 ለ6ኛ ክፍል ce6.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመክፈት፣
👉 ፊት ለፊት በሚታየው ቅጽ (form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና የመጀመሪያ ስም በማስገባት
“ውጤት ይመልከቱ (Check Your Result)” የሚለውን ቁልፍ በመጫን ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።
በቴሌግራም ቦት አማካኝነት በቀላሉ ለማየት የሚከተሉትን ሂደቶችን ይከተሉ፦
👉ወደ @MinistryResultQMTBOT በመሄድ ቦቱን ያስጀምሩ።
👉ቦቱን ከከፈቱ በኋላ /start የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ።
👉ክፍልዎን ይምረጡ፡ የሚሰጡትን አማራጮች በመጠቀም “Grade 8” የሚለውን ይምረጡ።
👉የሰባት ዲጂት (7-digit) የምዝገባ ቁጥርዎን ያስገቡ።
👉የመጀመሪያ ስምን (First Name) በትክክል በመጻፍ ውጤታሁን ማየት ትችላላችሁ።
2 weeks ago | [YT] | 1
View 0 replies
ETHIO2792
#NGAT የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ብቻ የሚከናወን መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡
የመመዝገቢያ ሊንክ 👇
ngat.ethernet.edu.et/
ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ ያስፈልጋል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር ሲሆን፤ በምዝገባ ወቅት በቴሌብር በኩል መክፈል ይጠበቅባችኋል።
ምዝገባው በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚከናወን መሆኑን የገለፀው አገልግሎቱ፤ የፈተና ጣቢያዎች ከምዝገባ በኋላ የተመዝጋቢ ቁጥሩ ታይቶ የሚወሰን መሆኑን ጠቁሟል፡፡
የፈተና መስጫ ጊዜው ወደፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡
2 weeks ago | [YT] | 0
View 0 replies
ETHIO2792
እስከ ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም ተራዝሟል!
የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ መረጃ በማስተሳሰር ላይ የምትገኙ የጤና ሙያ ተመራቂዎች፣ የመረጃ ማስተሳሰሪያ ጊዜ-ገደቡ እስከ ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።
ቀነ-ገደቡ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ያበቃል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፤ በተለያዩ ምክንያቶች መረጃ ማስተሳሰር ያላጠናቀቁ ተመራቂዎች በመኖራቸው ቀነ-ገደቡ እስከ ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑ ተገልጿል።
በመሆኑም በ hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የብሔራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥር (16 Digit FAN) በማስገባት አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት ለምዝገባ እንድትዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
🔔 መረጃ የማስተሳሰር ሒደት እንዳለቀ የፈተና ጣቢያ መረጣ ሒደት ይቀጥላል ተብሏል፡፡
2 weeks ago | [YT] | 0
View 0 replies
ETHIO2792
በሲዳማ ክልል የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።
በክልሉ ፈተናውን ከወሰዱ 45,034 ተማሪዎች መካከል 29,466 ተማሪዎች ወይም 65.43% ወደ ቀጣይ ክፍል ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።
ዘንድሮ በክልሉ የማለፊያ መቁረጫ ነጥብ ለመደበኛ ተማሪዎች 50% እና ከዚያ በላይ፣ ለአካል ጉዳተኞች ደግሞ 45% እና ከዚያ በላይ እንዲሆን መወሰኑን የክልሉ ምክትል ርዕሠ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ በየነ ባራሳ ተናግረዋል።
ፈተናውን ከሰጡ 790 ትምህርት ቤቶች መካከል 111 ወይም 14% የሚሆኑት ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ማሳለፋቸውን የገለፁት ኃላፊው፤ 15 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች አለማሳለፋቸውን ጠቁመዋል።
⏩ sidama.ministry.et/ አድራሻ ላይ በመግባትና የተማሪውን የመለያ ቁጥር እንዲሁም የመጀመሪያ ስም በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ።
2 weeks ago | [YT] | 0
View 0 replies
ETHIO2792
6ኛው ዙር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዛሬ መሠጠት ጀምሯል።
በዚህ የመጨረሻው ዙር ፈተና፣ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከዛሬ ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ፈተናቸውን በኦንላይን የሚወስዱ ይሆናል። ምስል፦ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ
3 weeks ago | [YT] | 1
View 0 replies
ETHIO2792
በ2019 የትምህርት ዘመን ወደ ሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (SIT) ለመግባት ያመልክቱ!
የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው 👇
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም
የትምህርት መስኮች
● Electrical Engineering
● Biotechnology
● Space Science
● Mechanical Engineering
● AI
● Nuclear engineering
መስፈርቶች
● የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል አማካኝ ውጤት 90%
● የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት 95 ፐርሰንታይል
● ከ500-700 ቃላት የግል መግለጫ መጻፍ ይኖርብዎታል
● የድጋፍ ደብዳቤ ከ2ኛ ደረጃ መምህርዎ/ሜንተርዎ ማጻፍ
● የማኅበረሰብ በጎ አገልግሎት የሰጡት ካለ ቢያይዙ ጥሩ ነው
ያመልክቱ 👉 sitedu.info/
የማመልከቻ ሒደቱን የሚያስረዳ ቪዲዮ ለመመልከት 👇
web.facebook.com/share/v/1Bg5mV7Kur/
3 weeks ago | [YT] | 2
View 0 replies
ETHIO2792
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ውጤትን ይፋ አድርጓል።
በአስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዳችሁ ተፈታኞች ውጤታችሁን ከታች ያለውን ሊንክ በመጫንና የመለያ ቁጥራችሁን በማስገባት መመልከት ትችላላችሁ።
ውጤት ለማየት 👇
www.geight.diresrms.org/View_Result/get_result
1 month ago | [YT] | 5
View 1 reply
Load more