ወልደ ፋሲለደስ ቲዩብ - Woldefasiledes Tube

“ ወንጌልን ባልሰብክ ወዮልኝ ” 1ኛ.ቆሮ.9፡16
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን የእግዚአብሔር ልጆች፤ በዚህ የዩቲብ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ስርዓት፣ዶግማና ቀኖናን በጠበቀ መልኩ ፦ የቤተክርስቲያን ታሪክ፣አዕማደ ምስጢራት፣ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን፣ ነገረ እግዚአብሔር፣ ነገረ ክርስቶስ፣ ነገረ ማርያም፣ ነገረ ቅዱሳን፣ ነገረ መላዕት፣...እና ሌሎችም መሰረታዊ ትምህርት ይሰጥበታል፡፡
ስለዚህ(Subscribe) ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ቃል ለሌሎች እንዲዳረስ(Share) ሼር በማድረግ ያዳርሱ፡፡



ወልደ ፋሲለደስ ቲዩብ - Woldefasiledes Tube

“በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥
ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።”
መዝሙር ዳዊት፦65፥11

3 months ago | [YT] | 2

ወልደ ፋሲለደስ ቲዩብ - Woldefasiledes Tube

ሉቃስ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።
²⁹ ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ።
³⁰ እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤
³¹ በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር።
³² ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።
³³ ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን፦ አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር።
³⁴ ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።
³⁵ ከደመናውም፦ የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
³⁶ ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም።
³⁷ በነገውም ከተራራ ሲወርዱ ብዙ ሕዝብ ተገናኙት።
³⁸ እነሆም፥ ከሕዝቡ አንድ ሰው እንዲህ እያለ ጮኸ፦ መምህር ሆይ፥ ለእኔ አንድ ልጅ ነውና ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ።

4 months ago | [YT] | 3

ወልደ ፋሲለደስ ቲዩብ - Woldefasiledes Tube

“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”
— ኢሳይያስ 53፥5

8 months ago | [YT] | 8

ወልደ ፋሲለደስ ቲዩብ - Woldefasiledes Tube

“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”ሉቃስ፦2፥11

11 months ago | [YT] | 12

ወልደ ፋሲለደስ ቲዩብ - Woldefasiledes Tube

“ይህ ወገን በጸሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም አላቸው።”ማርቆስ፦9፥29

እንዳለ አምላካችን በወንጌሉ በሀገራችን ላይ የሚታየው ክፉ ነገር ሁሉ በጾምና በጸሎት ካልሆነ ከሀገራችን ሊወጣ አይችልምና በጾም በጸሎት እንበርታ በፊቱ እንበርከክ።
እግዚአብሔር ስለ ቅዱሳኑ ሲል ሀገራችንን ይጠብቅልን።
መልካም ሱባዔ።

1 year ago | [YT] | 12

ወልደ ፋሲለደስ ቲዩብ - Woldefasiledes Tube

ንስሐ ክፍል-2 ዛሬ ምሽት ይጠብቁን።

“ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ።” — የሉቃስ ወንጌል፦13፥5

1 year ago (edited) | [YT] | 18

ወልደ ፋሲለደስ ቲዩብ - Woldefasiledes Tube

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ።

1 year ago (edited) | [YT] | 12

ወልደ ፋሲለደስ ቲዩብ - Woldefasiledes Tube

Happy Birth Day
Mother God
'' Theotokos "

1 year ago | [YT] | 13