ይህ ፈውስ መንፈሳዊ የተሰኘ መንፈሳዊ ጉባኤ ሲሆን በርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅ/ቂርቆስ ገዳም የ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ቤት ምሥክር መምህር በሆኑት በ ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረኪዳን ግርማ የሚሰጡ ትምህርቶች ይተላለፉበታል።
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
እንኳን ደስ አላችሁ ! “ እግዚአብሔር ገባሬ ኩሉ ወጣኔ ኩሉ ወፈጻሜ ኩሉ አኃዜ ኩሉ ወጸባጤ ኩሉ - ሁሉን የጀመረ ሁሉን የፈጸመ ሁሉን የያዘ ሁሉን የወሰነ እግዚአብሔር ” ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ፣ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ሁሉን የምትችል የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ትሁን እንደምን ሰነበታችሁ? እኛ አምላከ አበው እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ደኅና ነን። የተወደዳችሁ የቤተ ጉባኤያችን ቤተሰቦች፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት የሚገኘው የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት፣ ቀድሞ ጌታ ከመወለዱ ዘጠኝ መቶ ዓመት በፊት መጻሕፍተ ነቢያት ሲተረጎሙበት፣ ኋላም ቅዱስ ያሬድ ሲያስተምሩበት፣ መምህር ኤስድሮስ ምሥጢር ያገመሩበት ገዳም እንደመሆኑ ሰኔ ፲፱-፳፲፬ ዓም የቀደመ ታሪኩን ለመመለስ ቤተ ጉባኤው እንደገና ተመሥርቷል። በመሆኑም በነዚህ ያለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ፷፬ ደቀ መዛሙርትን ተቀብሎ አራቱን ጉባኤያት እያስተማረ ይገኛል። በተጨማሪም ለምእመናን በፈውስ መንፈሳዊ ሚዲያ ወንጌልን በአበው ቅዱሳን ሊቃውንት አስተምህሮ በማዳረስ ላይ ነው። በዓመት ውስጥ ለመነኮሳት ሥርዓተ ምንኩስናን በሚመለከት፣ለካህናት ኦርቶዶክሳዊ ኖላዊነትን በሚመለከት፣ ለምእመናን ስለ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብእና ስለ ልጅ አስተዳደግ ሥልጠናዎችን ይሰጣል።ከዚህም ጋር ደግሞ በሚከተሉት ወርቃማ ምክንያቶች ጠቅላላ ሆስፒታል በባሕር ዳር ከተማ ለመገንባት ፕሮጀክቱን ይፋ ካደረግንበት ከሰኔ ፲፱- ፳፲፯ ጀምሮ ለአንድ ዓመት ያክል በሀገረ ስብከታችንና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ፈቃድ እንቅስቃሴ ስናደርግ ከርመናል። እግዚአብሔር ያለው ነገር እርሱ በወደደው ትክክለኛው ሰዓት ይፈጽማልና ፕሮጀክቱን ይፋ ባደረግን በዓመቱ በዚያው ቀን በወላዲተ አምላክና በቅዱሳን ጸሎት፣ ቅን ልቡና ባላቸው ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ጥረት ሆስፒታሉን ለመገንባት የሚያስችል 30,000 ካሬ ቦታ በባሕር ዳር ከተማ ሰኔ ፲፱-፳፲፰ ዓም በጉባኤ ቤታችን ምሥረታ ቀን ስለተቀበልን አምላከ ቅዱስ ገብርኤልን እናመሰግነዋለን ። ሆስፒታሉን የምንገነባባቸው ዓላማዎቻችንም፦፩. ፍጥረትን ሁለ በእግዚአብሔር መንገድ ለማገልገል፦እግዚአብሔር አምላካችን ለክፉዎችና ለደጎች፣ለኃጥአና ለጻድቃን ዝናምን እንደሚያዘንብ ፣ፀሐይን እንደሚያወጣ የሆስፒታላችን ዓላማም ለሁሉም በምሕረት፡ እምነትን፣ ዘርንና ማንነትን ሳይለይ፣ ለሰው ልጅ ሁሉ የሚታዘንበት የምሕረት ማረፊያ መሆን ነው። ፪.ለጥበብና ለሳይንስ፦ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሀገራችን የነበራትን የጥበብ ታሪክ በዘመናዊ የምርምር ዐቅም ማስቀጠል።፫. ሁለንተናዊ ፈውስ ለመስጠትቤተ ጉባኤያችን የወንጌል ቤተ ጉባኤ እንደመሆኑ ወንጌል ደግሞ የፈውስ ሕግ ናት፣ ስለሆነም ቤተ ጉባኤያችን ኃጢአትን በንስሐ ፣ አለማወቅን በማስተማር እንደሚፈውስ ሁሉ የታመሙትን ደግሞ በማኅበር ጸሎት፣ በጸበል እንዲሁም እግዚአብሔር እጁ ሰፊ ነውና በሕክምና አገልግሎትና በሰብአዊነት ተግባር ለሰዎች ፈውስ ለመስጠት ይህንን ሆስፒታል ሊገነባ ዝግጅቱን እየፈጸመ ነው።፬. ወንጌል የተስፋ ሕግ ናት። ከአበው አንዱ መከራን ምን ያቀለዋል ቢሉት “ እስመ ተስፋ ያቀልሎ ለምንዳቤ - መከራን የሚያቀለው ተስፋ ነው ብሏል። በመሆኑም ተስፋችሁ አልቋል የተባሉ ወገኖቻችንን ሁሉ በመንከባከብ ልቡናቸው በሰላም እንዲያርፍና በተስፋ ምርኩዝነት ዘመናቸውን በዕረፍት እንዲፈጽሙ ማድረግ።፭.ሰው መሥራት ፦በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አረዳድ መሠረት የሰው ልጅ የፍጥረታት ዘውድ ነው። እግዚአብሔርን መስሎ የተፈጠረ እርሱ ነው፣ ከሰማይ በታች ያሉ ፍጥረታትን እንዲያስተዳደር ሥልጣን የተሰጠው ሰው ነው፣ ክርስቶስ የሞተለት የዘለዓለም ተስፋ የተሰጠውም ሰው ነው። በመሆኑም ቤተ ጉባኤያችን ክቡሩን የሰው ልጅ የቅድመ ጋብቻ ትምህርት በመስጠት፣ የባለትዳሮች እና የልጅ አስተዳደግ ሥልጠና በመስጠት፣ በሱስ የተጎዱ ወንድሞቻችንን በመንከባከብና እንደገና አዲስ ሰውንት እንዲያገኙ በማድረግ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለሀገራችን በጎና ባለ አእምሮ ትውልድ ለመፍጠር ይህንን ሆሰፒታል ልንገነባ እየተፋጠንን ነው።ይህንን ዓላማ ለመፈጸም ለምንገነባው ሆስፒታል በቂ ቦታ ለማግኘት የረዳንን እግዘብሔርን እርሱም ያከበራቸው ቅዱሳንን እያመሰገንን በእውነተኛው መድኃኒታችን በመድኃኔዓለም ቀን የሆስፒታላችን የመሠረት ድንጋይ ልናስቀምጥ መሆናችን ደግሞ ደስታችንን ዕጥፍ ድርብ ያደርገዋል። ከዚህም የደረስነው ነገም የምንደርሰው በማይናወጸው መሠረት በእርሱ ላይ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቁመን ነውና። ከመስቀሉ ሥር እናቱን “እናት ትሁናችሁ” ብሎ ባይሰጠንስ ቋጠሮ ሲጸናብን ማን ለእርሱ ነግሮ ያስፈታልን ነበር? ልጅ እያለን ወደ ወላጅ እናታችን እናለቅስ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ከመድኃኔዓለም እናት እያለቀስን የወደድነውን የምንቀበልባት እናት ድንግል ማርያምን ስለሰጠንም እናመሰግነዋለን ። ውድ ኦርቶዶክሳውያን ይህንን መሬት እንድናገኝ የረዱንን ሁሉ የጉባኤ አምላክ ይስጥልን በሰማይ ቦታ ይስጣችሁ እያላችሁ እንድትመርቁልን እየጠየቅን፤ ቀዳሚት ፳፯-፲-፳፲፰ ዓም ከጧቱ 3:00 ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በባሕርዳር የመሠረት ድንጋዩን ስለምናስቀምጥ እንኳን አደረሳችሁ፣እንኳን ደስ አላችሁ፣ አብራችሁን ለቆማችሁ ሁለ መድኃኔዓለም ከእናንተ ጋር ይሁን። እግዚአብሔር ገባሬ ኩሉ ወጣኔ ኩሉ ወፈጻሜ ኩሉ አኃዜ ኩሉ ወጸባጤ ኩሉ ሁሉን የጀመርህ ሁለን የምትፈጽም ሁሉን የያዝህ ሁሉን የወሰንህ መድኃኔዓለም ሆይ ከአንተው ተጠግተን የጀመርነውን እንደምትፈጽምልን ፈጽመን እናምናለን ።ለአንተ ለባሕርይ አባትህ ለአብ ለማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን !አባ ገብረ ኪዳን ግርማየርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር መምህር
2 days ago | [YT] | 3,353
View 105 replies
https://youtu.be/J-xKd4dsSuM?si=SoLOp...
1 week ago | [YT] | 30
View 0 replies
https://youtu.be/i8UtPfvn4rg?si=0Ijdu...
2 weeks ago | [YT] | 26
https://youtu.be/XaqPedCddbE?si=QB4SD...
1 month ago | [YT] | 60
https://youtu.be/F3ReA0Z5Rr8?si=6-czz...
1 month ago | [YT] | 43
View 1 reply
“አንዱ የደጉ ሳምራዊ ስፍራ ከአስተናገጆቹ ጋር ዛሬ ተመረቀ “ ጌታ በወንጌል መስሎ ካስተማረባቸው ምሳሌዎች ውስጥ የደጉ ሳምራዊ ታሪክ ነው። ነገሩንም ባለ መድኃኒቱ ሉቃስ እንዲህ መዝግቦታል: “ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፡— “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ። አንድ ካህን በዚያ መንገድ ወረደ አይቶትም ገለል ብሎ አለፈ።እንዲሁም ደግሞ አንድ ሌዋዊ ወደዚያ ስፍራ መጣና አይቶት ገለል ብሎ አለፈ። አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥ቀርቦም ዘይትና የወይን ጠጅ በቍስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፥ በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደርያ ወሰደው ጠበቀውም።በማግሥቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና፡— ‘ጠብቀው፥ ከዚህም በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ፡’ አለው።እንግዲህ ከነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነው ማንኛው ይመስልሃል?” እንደ አባቶቻችን ትርጓሜ ይህ ታሪክ በመጀመሪያው በአዳም ሲተረጎም በፍጻሜው ግን በሁላችን ይተረጓማል። ከኢየሩሳሌመእ መውረድ ማለትም ከነፍስ ልዕልና፣ከሃይማኖት፣ከማዕረገ ልቡና፣ ከቅድስና ሰገነት፣ከአምሳለ እግዚአብሔርነት ፣ ከመንግሥተ ሰማያት ርስት፣ከፍቅረ እግዚአብሔር መጉደልና መዋረድ ፣እግዚአብሔር እኛን ካስቀመጠበት ቦታ መታጣት ነው። የመጨረሻው ልዕልና የእግዚአብሔር እቅፍ ሲሆን የቁልቁለቱም ጉድጓድ የእርሱን ፍቅር መራቅ እንደሆነ አበው ያስረዳሉ። ራስ ራሱን የቀጠቀጡት ወንበዴዎችም የሰውን ርእሰ ልቡና በክፉ መሻት፣በትዕቢትና በፍቅረ ዓለም በሎታ የሚቀጠቅጡ ባልፈጠሩት ፍጥረት ባልዋጁት ሰውነት ሠልጥነው የሚኖሩ ሥጋ አጋንንት ናቸው። ልብሱን መግፈፍም ቀድሞ የአዳምን ልብሰ ግርማና ብርሃን ማሳጣታቸው ሲሆን በሐዲስ ኪዳን ደግሞ አዲሱን ልብሳችን ክርስቶስን ያራቁቱን ዘንድ ርእሰ ኅሊናችንን የሚቀጠቅጡ ምሕረት የለሽ ሰይጣናት ናቸው። ሁለቱ አልፈው የሄዱ ካህናትም በክህነታቸው እግዚአብሔርን ቢያገለግሉም ነገር ግን ነገደ ሰብእን ከሞት ዕዳ ከኃጢአት ፍዳ ማውጣት ያልተቻላቸው መልከ ጼዴቅና አሮን እንደሆኑ ይተረጎማል።የወደቀውን ያነሣው ደጉ ሳምራዊ ደግሞ ዘልማዱ ኂሩት - ልማዱ ቸርነት የሆነ ሰውን በመልኩ እንደገና በሐዲስ ተፈጥሮ ለማደስ የባርያን መልክ ይዞ የመጣ መድኀኒታችን ክርስቶስ ነው። እርሱ በቁስሉ ቤዛነት ታድጎ የምሕረት ዘይቱን አፍሶ የፍቅሩን ወይን ለግሶ፣ በደሙ አንጽቶ በልጅነት አክብሮ ዓለምን ታደገ።ከዚያ በኋላ የሕሙማን የድኅነት ቤት ፣የኅዙናን ምስካይ የስደተኞች ቤት አዘጋጀ። ሕሙማንና ቁስለኞቹን የሚፈውሱ አስተማሚዎቹን አሰማርቶ ፈውሱልኝ ብሎ ሁለት ዲናሮችን ሰጠ።ከላይ እንደ ተናገርነው ደጉ ሳምራዊ የተባለ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን የመጣ ጌታ ሲሆን እውነተኛይቱ ቤተ ፈውስም (ሐኪም ቤት) ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት። ሕሙማንን የምትቀልባቸው ቤቶችም የመጻሕፍት ትርጓሜ ቤቶች ናቸው። ባለንበት ዘመንም እንደ ግልም እንደ ኅብረትም ከኢየሩሳሌም በእርግጥ ከዚህ በላይ ወርደን የምናውቅ አይመስለኝም። ከጽድቅ በኃጢአት፣ ከአንድነት በመለያየት፣ ከፍቅረ ቢጽ በፍቅረ ንዋይ፣ ከትሕትና በፍቅረ ሲመት፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር በፍቅረ ዓለም፣ ከእውነት በአድርባይነት፣ ከሰማይ መንግሥት በምድራዊነት በሚያጣድፍ ቁልቁለት እየወረድን እንደሆንን ቢያንስ ሊገባን ይገባል። ወንበዴዎች አጋንንትም አእምሯችን ቀጥቅጠው እንዳንደማመጥ፣ ዓላማ የለሾች እንድንሆን፣ነገ እንዳይታየን ፣ ማሰቢያችን ነስተው ከራሳችን ጋር እንዳንሆን በማባከን፣ በማደንዘዝ፣ ጥሩ አድርገው ደብድበውናል።አልታመምኩም የሚል ካለ በእርግጥ እርሱ ከጽኑ ሕሙማን ውስጥ ነው። አንድ የሰውነት አካል ከአእምሮ ጋር መልእክት መታላለፍ ከቆመ ቢቆርጡትም አያምም ይላሉ ሐኪሞች። (በትክክል በሙያው አልገልጠው ይሆናል እታረማለሁ) አሁን ከክርስቶስ በረጅሙ ከመራቃችን የተነሣ መታመማችንም አናውቅም፣ ከሕይወታችን ራስ ከክርስቶስ ጋር የምንገናኝበት የሆነ መስመራችን ምን እየሆነ ይሆን?አሁን ሁለት እድሎች አሉን። ወደ ደጉ ሳምራዊ የእንግዶችማረፊያ መመለስ። በሰጣቸው ሁለት ዲናርም ይፈውሱናል። አንደኛው ፈውስ ንስሐ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ወንጌል ነው።የሕሙማን መታከሚያ ቤቶች ናቸው። ወንጌልም ዝገታችንን የምታርቅና ፊታችንን የምታበራ ዘይት ቁስላችንን የምታደርቅ ልቡናችንን በሐሤት ሰማያዊ የምትመላ ወይን ናት። ጥሪት ቁሪትን ዓላማ ያላደረጉ መምህራን ከንጉሥ ክርስቶስ የተሸለሟቸው ሁለቱ ዲናሮችም ብሉይና ሐዲስ ናቸው። በዚህ የሚፈውሱ የቤቱ እንግዳ ተቀባዮችም መምህራን ናቸው።ከዚህ ተነሥተን የመጻሕፍት ትርጓሜ ት/ቤቶችን የደጉ ሳምራዊ (የቸሩ መድኃኔዓለም) የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች እንላቸዋለን። በመሆኑም በዛሬው ዕለት ግንቦት ፲፮-፳፻፲፰ ዓም በደብረ ልዑላን ደብረ ታቦር መድኃኔዓለም ቤተ ጉባኤ በመመረቁ አንድ የሕሙማን ማረፊያ፣ በክሕደትም በኃጢአትም ከዓለም ፈልሰው የሚመጡት የመንግሥተ ሰማያት እንግዶች ማረፊያ ድንቅ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ቤተ ጉባኤ ተመርቆልናል። ከነ አስተናጋጆቹ ያልኩት ደግሞ የድኅነት አስተናጋጆች የወንጌል ማዕድ አቅራቢዎች፣ የመከሩ ሠራተኞች ወንድሞቻችን ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ጉባኤው ተሠርቶ ሲጠናቀቅ አብረው ስለ ተመረቁልን። የቤተ ጉባኤው የአራቱ ጉባያት ምስክር መምህር መምህረ መምህራን በጽሐ ዓለሙም ቤቱንም ሰውንም ሠርተው ስለሰጡን መምህር ሆይ እጅ ይባርክ ፣ ግሩም ሊቀ ጸረብት እንዲህ ያለም የለ ይበል ነው ብለናል! ደክሞ የተማረ ሰው ታሞ ያስተምራል ፣እየታመመ ይፈውሳል፣ እንኳን ደስ ያለዎ፣ ዓይንዎትን በዓይንዎት እንኳን አሳየዎ። ወንድሞቻችንም እንኳን ከጸጋ መንፈስ ቅዱስ ተወለዳችሁልን። የወንጌል ዘራችሁን ያብዛው። በሉ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ ወደ ተሠራልን ቤተ ጉባኤ በአህያም ቢሆን ተጭነን እንሂድ። መምህሩም በሁለቱ ዲናር ይፈውሱናል። ኧረ ትርፍ ወጭ አውጥተውም ይፈውሳሉ። እነ ታኦዶኮስ የመሰሉትንና ሌሎችን መጻሕፍትን ጽፈው ሰጥተውናልና።የመምህራን አምላክ ሲመጣ በመማር፣ በማስተማር፣ በመፈተን የከፈሉትን ሁሉ ዋጋዎን ያስረክብዎ መምህር። በተሠራልን የነፍስ የጤና ቤት ተምረን ለመፈወስ ያብቃንይቆየን !አባ ገብረ ኪዳን ግርማየርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር መምህር
1 month ago | [YT] | 3,505
View 56 replies
https://youtu.be/--9PyCp1p2g?si=uvAa_...
1 month ago | [YT] | 51
https://youtu.be/AQMoa0amHeo?si=DIJwX...
1 month ago | [YT] | 49
“መሠረተ ሕይወት ማርያም” የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ተፈጠረ የሚያሰኘው አንዱ ሕያውነት ነው።ለዚያም የሚጠበቅበት አንድ ነገር አለ። ይኸውም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር መስማማት ነው። ያንን ፈቃደ እግዚአብሔር መስማማት በተውን ጊዜ ግን መዋትያን ሆንን። በጸጋ ያገኘነውን ሕይወት ስናጣ መሬት ነበርንና ወደ መሬትነታችን ተመለስን።በዚያው ቀንበርም የአዳም ልጆች ሁሉ ተገዛን። ምድራውያን ሆነናልና ፣ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎን ነበርና ልደታችንም የተናቀ ሆነ።ሮሜ ፫:፳፪ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ አንዲት ሴት ወንድ በወለደች የመንጻት ሕግ ተሠራላት።ዘሌ፲፪፥፩ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር ግን ፍጥረታቱን እንደ ተጎዳን እንቀር ዘንድ አልተወንም። አብ ቢሉ በልጁ ፣ መንፈስ ቅዱስም በቃሉ ፣ ወልድም በአካሉ ሰው ሆኖ ይታረቀን ዘንድ ወደደ። ለዚህም መላውን ፈትኖ አንዲት ሴትን አገኘ። ይህቺውም መርገም የሌለባት፣ በምልዐተ ኃጢአት ያልተዳደፈች ፣ ክብርን የተመላች ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ሰዎች ሁሉ በመርገምና በምልዐተ ኃጢአት ክብር ሲጎድላቸው ድንግል ማርያም ግን በሦስት ምክንያት ክብርን የተመላች ነበረች።፩.ከመርገም ንጹሕ በመሆን፪.ከምልዐተ ኃጢአት ንጽሕት በመሆን፫.ከሰው ታጥተው የነበሩ የመንፈስ ቅዱስን ፍሬዎች ተምልታ በመገኘት ፡ እኒህም ትሕትና ፣ ሃይማኖት ፣ መታዘዝ ፣ ንጽሕና ናቸው።ይህ ነው “እስመ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር - በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነት አግኝተሻልና” ያሰኛት።በዚህ ባለሟልነቷም ክብርን ለብሳ ጸጋን ተመልታ ለዓለማት ፈጣሪ እናት ሆነችው። ከእርስዋ በነሣው ሥጋ በተቀበለው የቤዛነት ዋጅቶም የእርሱ ማኅበር ቤተሰብ አካል አደረገን። ቅርንጫፍ በግንዱ ሕይወትነት እንዲኖር እርሱ የሕይወት የወይን ግንድ ሆኖ በቅርንጫፍነት ተዋሕደን እንኖር ዘንድ አደለን።ስለዚህ አምላክን የወለደች ቅድሰት ድንግል ማርያም ትንሣኤና ሕይወታችን ከእርስዋ ይወለድ ዘንድ ክብርን ተጎናጽፋ ፣ ጸጋን ተመልታ የተገባች ስለሆነች የምንድንበት ቁርባን የሚሆን ሥጋውን ቤዛ የሆነባትን ነፍሱን ከእርስዋ ነስቶ ስለ ተዋሐደ መሠረተ ሕይወት እንላታለን። በእናትነቷም ፈጽመን እንወዳታለን። እንደ እናትነቷም በልጅነት ከእርስዋ ሥር እንጠጋለን። ልደቷም የፀሐዩን ልደት የሚያበሥር ጎሕ ነው። ልጅዋን ግን የማዕዘናችን ራስ ብለን እናመልከዋለን። ከዚህም የተነሣ እመቤታችን ስለ ተወለደችልን ደስታችን ዕጥፍ ነው። መሠረተ ሕይወት ከሚለው ጋር ዛሬ አንድ ነገር ላንሣ። ይህንን ቃል አንድ ደጅ ላይ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አይቼው ነበር አክሱም። ከእማሆይ ወለተ ሕይወት ቤት። እማሆይ ወለተ ሕይወት ከየኔታ ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው ቅኔን (ጨጎዴ) ፣ ከየኔታ ሄኖክ (አክሱም) መጻሕፍተ ብሉያትንና መጻሕፍተ ሐዲሳትን የተማሩ፣ ምንኩስናን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕውቀትና በኦርቶዶክሳዊ አእምሮ አካተው የያዙ ልባም እናት ናቸው። እማሆይ መጀመሪያ ሰው ከቤታቸው ሲሄድ በሌለ ቤታቸው በእናትነት ባለጸግነት በብሩህ ፊት ይቀበላሉ ሐዲሳቱን ጠንቅቀው ያወቁ ሲሆን በትሕትና ይጠይቃሉ። መምህር ከቤታቸው ከሄደ ያላቸውን በልግስና መግበው ከዚያ ወሬ የለም። መጽሐፍ ያቀርቡና ይተርጉሙልኝ ይላሉ። የጥበብ ፈላጊዋ የንግሥት ማክዳ ምልክት። እማሆይ ማንም እቤታቸው ሄዶ ሳንቲም ልስጥ ቢላቸው በጄ አይሉም። አንድ ጊዜ ካናዳ የሚኖሩ አንድ አባት ስለ እማሆይ ነግሬያቸው አስተባብረው ብር ልላክላቸው ብለው ብጠይቅ የባንክ ቁጥር አልሰጠኝ ብለው ቀርተዋል።የእናቶቻችን መናንያት የቅዱሳት ልጅ ናቸውና። እማሆይ እንግዳ መጣ ብለው ወንበር የማይፈቱ የቀለም ትግሕት የቀለም እናት ናቸው። እማሆይ የቀለም እንጅ ሥጋዊ ዘር የሌላቸው የቤተ ክርስቲያን አንድነቷ ልጅ ናቸው። የመምህር ገብረ ጊዮርጊስ ልጅ ናቸውና። መምህር ገብረ ጊዮርጊስ ትውልዳቸው አክሱም ሲሆን መምህርነታቸው ግን ደብረ ሃይማኖት መካነ ኢየሱስ ነው። ባሕታዊዉ ሊቅ የኔታ ገብረ ጊዮርጊስ በደብረ ሃይማኖት መካነ ኢየሱስ ቅኔና መጻሕፍትን ለረጅም ዓመታት አስተምረው ራሳቸውን በጸጋም በጥበብም አሳክለው መምህር ኃ/ሚካኤልን ተክተው ሊያርፉ ሲሉ አክሱም ተመልሰው መምህር ሄኖክን ለአክሱም ተክተው አረፉ። እርሳቸውም እማሆይ ወለተ ሕይወትን ተክተውልን ነበር። አክሱም ሄጄ ሳለ የየኔታ ገብረ ጊዮርጊስን ፎቶና እጅ ጽሑፍ አእማደ ምሥጢር አሳይተውኝ አብረን ተላቅሰናል። የኔታ ገብረ ጊዮርጊስ ደቀ መዛሙርትን በመንደር ለምነው መግበው ሲጨርሱ በኋላ የሚቀምሱ በመንኖ ጥሪት የታወቁ ሊቅ ናቸው። እማሆይም ይኸው የአባታቸው ልጅ ናቸውና ፍቅረ ንዋይን አሽቀንጥረው እንደጣሉት ሄዱ።እማሆይ ሰው የሚያበረቱ፣ ትምህርት በቃኝ የማይሉ እናት ናቸው። ብሉይ ኪዳን እንዳጠናቀቅሁ ነበርና መጀመሪያ የሄድኩት “ ሊቃውንቱንም ተማርና በኋላ ከአንተ እማራለሁ“ ያሉኝ እናትነታቸው ጉልበት የሚጨምር ምክር ነበር። እማሆይ ለዕቅበተ እምነት ካላቸው ፍቅር የተነሣ “ለምን እንደ አባቶቻችን ጉባኤ እየተደረገ የሚጠራጠሩ ሁሉ በጉባኤ አይጠየቁም“ እያሉ በልባቸው የሃይማኖት እሳት የሚነድባቸው እናት ነበሩ። ከእማሆይ ከቤታቸው ከበሩ ከሳንቃው ላይ “ መሠረተ ሕይወት ማርያም “ የሚል ጽሑፍ አለና፣ ለምንድን ነው ብየ ስጠይቃቸው: የቅኔ መምህርት ስለሆኑ እንዲህ ብለው መልሰውልኝ ነበር።“አንደኛ በእመቤታችን ምክንያት ጌታ ተወልዶልናል። ሁለተኛ የእኔም (ስማቸው ሕይወት ስለሆነ) መነሻየና መድረሻየ ከልጇ የምታደርሰኝ እርስዋ ናት” አሉኝ።ክብርት እናታችን እነ የኔታ እርስዎን እንዳስገኙ እርስዎስ ማንን ተክተውልን ይሆን? የእነ የኔታን መጽሐፍ ከእርስዎ አገኘነው የእርስዎንስ ጨምሮ ደግሞ ማን ያሳየን ይሆን? እናቴ:ብዙ ስለ ቤተ ክርሰቲያን ተነጋግረን የጦርነት ጨለማ ሳያስተያየን ሄዱ? እናታችን የምርም በእመቤታችን ፍቅር መቆምዎትን በልደቷ አርፈው መሰከሩ። እውነትም መሠረተ ሕይወት ማርያም አባ ገብረ ኪዳንየርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር መምህር
1 month ago | [YT] | 3,524
View 66 replies
https://youtu.be/3PwPN2pvSv0?si=9xHuU...
1 month ago | [YT] | 26
Load more
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
እንኳን ደስ አላችሁ !
“ እግዚአብሔር ገባሬ ኩሉ ወጣኔ ኩሉ ወፈጻሜ ኩሉ አኃዜ ኩሉ ወጸባጤ ኩሉ - ሁሉን የጀመረ ሁሉን የፈጸመ ሁሉን የያዘ ሁሉን የወሰነ እግዚአብሔር ”
ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ፣ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ሁሉን የምትችል የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ትሁን እንደምን ሰነበታችሁ? እኛ አምላከ አበው እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ደኅና ነን።
የተወደዳችሁ የቤተ ጉባኤያችን ቤተሰቦች፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት የሚገኘው የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት፣ ቀድሞ ጌታ ከመወለዱ ዘጠኝ መቶ ዓመት በፊት መጻሕፍተ ነቢያት ሲተረጎሙበት፣ ኋላም ቅዱስ ያሬድ ሲያስተምሩበት፣ መምህር ኤስድሮስ ምሥጢር ያገመሩበት ገዳም እንደመሆኑ ሰኔ ፲፱-፳፲፬ ዓም የቀደመ ታሪኩን ለመመለስ ቤተ ጉባኤው እንደገና ተመሥርቷል።
በመሆኑም በነዚህ ያለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ፷፬ ደቀ መዛሙርትን ተቀብሎ አራቱን ጉባኤያት እያስተማረ ይገኛል። በተጨማሪም ለምእመናን በፈውስ መንፈሳዊ ሚዲያ ወንጌልን በአበው ቅዱሳን ሊቃውንት አስተምህሮ በማዳረስ ላይ ነው። በዓመት ውስጥ ለመነኮሳት ሥርዓተ ምንኩስናን በሚመለከት፣ለካህናት ኦርቶዶክሳዊ ኖላዊነትን በሚመለከት፣ ለምእመናን ስለ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብእና ስለ ልጅ አስተዳደግ ሥልጠናዎችን ይሰጣል።
ከዚህም ጋር ደግሞ በሚከተሉት ወርቃማ ምክንያቶች ጠቅላላ ሆስፒታል በባሕር ዳር ከተማ ለመገንባት ፕሮጀክቱን ይፋ ካደረግንበት ከሰኔ ፲፱- ፳፲፯ ጀምሮ ለአንድ ዓመት ያክል በሀገረ ስብከታችንና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ፈቃድ እንቅስቃሴ ስናደርግ ከርመናል።
እግዚአብሔር ያለው ነገር እርሱ በወደደው ትክክለኛው ሰዓት ይፈጽማልና ፕሮጀክቱን ይፋ ባደረግን በዓመቱ በዚያው ቀን በወላዲተ አምላክና በቅዱሳን ጸሎት፣ ቅን ልቡና ባላቸው ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ጥረት ሆስፒታሉን ለመገንባት የሚያስችል 30,000 ካሬ ቦታ በባሕር ዳር ከተማ ሰኔ ፲፱-፳፲፰ ዓም በጉባኤ ቤታችን ምሥረታ ቀን ስለተቀበልን አምላከ ቅዱስ ገብርኤልን እናመሰግነዋለን ። ሆስፒታሉን የምንገነባባቸው ዓላማዎቻችንም፦
፩. ፍጥረትን ሁለ በእግዚአብሔር መንገድ ለማገልገል፦
እግዚአብሔር አምላካችን ለክፉዎችና ለደጎች፣ለኃጥአና ለጻድቃን ዝናምን እንደሚያዘንብ ፣ፀሐይን እንደሚያወጣ የሆስፒታላችን ዓላማም ለሁሉም በምሕረት፡ እምነትን፣ ዘርንና ማንነትን ሳይለይ፣ ለሰው ልጅ ሁሉ የሚታዘንበት የምሕረት ማረፊያ መሆን ነው።
፪.ለጥበብና ለሳይንስ፦
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሀገራችን የነበራትን የጥበብ ታሪክ በዘመናዊ የምርምር ዐቅም ማስቀጠል።
፫. ሁለንተናዊ ፈውስ ለመስጠት
ቤተ ጉባኤያችን የወንጌል ቤተ ጉባኤ እንደመሆኑ ወንጌል ደግሞ የፈውስ ሕግ ናት፣ ስለሆነም ቤተ ጉባኤያችን ኃጢአትን በንስሐ ፣ አለማወቅን በማስተማር እንደሚፈውስ ሁሉ የታመሙትን ደግሞ በማኅበር ጸሎት፣ በጸበል እንዲሁም እግዚአብሔር እጁ ሰፊ ነውና በሕክምና አገልግሎትና በሰብአዊነት ተግባር ለሰዎች ፈውስ ለመስጠት ይህንን ሆስፒታል ሊገነባ ዝግጅቱን እየፈጸመ ነው።
፬. ወንጌል የተስፋ ሕግ ናት። ከአበው አንዱ መከራን ምን ያቀለዋል ቢሉት “ እስመ ተስፋ ያቀልሎ ለምንዳቤ - መከራን የሚያቀለው ተስፋ ነው ብሏል። በመሆኑም ተስፋችሁ አልቋል የተባሉ ወገኖቻችንን ሁሉ በመንከባከብ ልቡናቸው በሰላም እንዲያርፍና በተስፋ ምርኩዝነት ዘመናቸውን በዕረፍት እንዲፈጽሙ ማድረግ።
፭.ሰው መሥራት ፦
በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አረዳድ መሠረት የሰው ልጅ የፍጥረታት ዘውድ ነው። እግዚአብሔርን መስሎ የተፈጠረ እርሱ ነው፣ ከሰማይ በታች ያሉ ፍጥረታትን እንዲያስተዳደር ሥልጣን የተሰጠው ሰው ነው፣ ክርስቶስ የሞተለት የዘለዓለም ተስፋ የተሰጠውም ሰው ነው። በመሆኑም ቤተ ጉባኤያችን ክቡሩን የሰው ልጅ የቅድመ ጋብቻ ትምህርት በመስጠት፣ የባለትዳሮች እና የልጅ አስተዳደግ ሥልጠና በመስጠት፣ በሱስ የተጎዱ ወንድሞቻችንን በመንከባከብና እንደገና አዲስ ሰውንት እንዲያገኙ በማድረግ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለሀገራችን በጎና ባለ አእምሮ ትውልድ ለመፍጠር ይህንን ሆሰፒታል ልንገነባ እየተፋጠንን ነው።
ይህንን ዓላማ ለመፈጸም ለምንገነባው ሆስፒታል በቂ ቦታ ለማግኘት የረዳንን እግዘብሔርን እርሱም ያከበራቸው ቅዱሳንን እያመሰገንን በእውነተኛው መድኃኒታችን በመድኃኔዓለም ቀን የሆስፒታላችን የመሠረት ድንጋይ ልናስቀምጥ መሆናችን ደግሞ ደስታችንን ዕጥፍ ድርብ ያደርገዋል። ከዚህም የደረስነው ነገም የምንደርሰው በማይናወጸው መሠረት በእርሱ ላይ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቁመን ነውና። ከመስቀሉ ሥር እናቱን “እናት ትሁናችሁ” ብሎ ባይሰጠንስ ቋጠሮ ሲጸናብን ማን ለእርሱ ነግሮ ያስፈታልን ነበር? ልጅ እያለን ወደ ወላጅ እናታችን እናለቅስ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ከመድኃኔዓለም እናት እያለቀስን የወደድነውን የምንቀበልባት እናት ድንግል ማርያምን ስለሰጠንም እናመሰግነዋለን ።
ውድ ኦርቶዶክሳውያን ይህንን መሬት እንድናገኝ የረዱንን ሁሉ የጉባኤ አምላክ ይስጥልን በሰማይ ቦታ ይስጣችሁ እያላችሁ እንድትመርቁልን እየጠየቅን፤ ቀዳሚት ፳፯-፲-፳፲፰ ዓም ከጧቱ 3:00 ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በባሕርዳር የመሠረት ድንጋዩን ስለምናስቀምጥ እንኳን አደረሳችሁ፣እንኳን ደስ አላችሁ፣ አብራችሁን ለቆማችሁ ሁለ መድኃኔዓለም ከእናንተ ጋር ይሁን።
እግዚአብሔር ገባሬ ኩሉ ወጣኔ ኩሉ ወፈጻሜ ኩሉ አኃዜ ኩሉ ወጸባጤ ኩሉ
ሁሉን የጀመርህ ሁለን የምትፈጽም ሁሉን የያዝህ ሁሉን የወሰንህ መድኃኔዓለም ሆይ ከአንተው ተጠግተን የጀመርነውን እንደምትፈጽምልን ፈጽመን እናምናለን ።
ለአንተ ለባሕርይ አባትህ ለአብ ለማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን !
አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር መምህር
2 days ago | [YT] | 3,353
View 105 replies
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
https://youtu.be/J-xKd4dsSuM?si=SoLOp...
1 week ago | [YT] | 30
View 0 replies
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
https://youtu.be/i8UtPfvn4rg?si=0Ijdu...
2 weeks ago | [YT] | 26
View 0 replies
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
https://youtu.be/XaqPedCddbE?si=QB4SD...
1 month ago | [YT] | 60
View 0 replies
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
https://youtu.be/F3ReA0Z5Rr8?si=6-czz...
1 month ago | [YT] | 43
View 1 reply
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
“አንዱ የደጉ ሳምራዊ ስፍራ ከአስተናገጆቹ ጋር ዛሬ ተመረቀ “
ጌታ በወንጌል መስሎ ካስተማረባቸው ምሳሌዎች ውስጥ የደጉ ሳምራዊ ታሪክ ነው። ነገሩንም ባለ መድኃኒቱ ሉቃስ እንዲህ መዝግቦታል:
“ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፡— “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ። አንድ ካህን በዚያ መንገድ ወረደ አይቶትም ገለል ብሎ አለፈ።
እንዲሁም ደግሞ አንድ ሌዋዊ ወደዚያ ስፍራ መጣና አይቶት ገለል ብሎ አለፈ። አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥
ቀርቦም ዘይትና የወይን ጠጅ በቍስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፥ በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደርያ ወሰደው ጠበቀውም።
በማግሥቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና፡— ‘ጠብቀው፥ ከዚህም በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሃለሁ፡’ አለው።እንግዲህ ከነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነው ማንኛው ይመስልሃል?”
እንደ አባቶቻችን ትርጓሜ ይህ ታሪክ በመጀመሪያው በአዳም ሲተረጎም በፍጻሜው ግን በሁላችን ይተረጓማል። ከኢየሩሳሌመእ መውረድ ማለትም ከነፍስ ልዕልና፣ከሃይማኖት፣ከማዕረገ ልቡና፣ ከቅድስና ሰገነት፣ከአምሳለ እግዚአብሔርነት ፣ ከመንግሥተ ሰማያት ርስት፣ከፍቅረ እግዚአብሔር መጉደልና መዋረድ ፣እግዚአብሔር እኛን ካስቀመጠበት ቦታ መታጣት ነው። የመጨረሻው ልዕልና የእግዚአብሔር እቅፍ ሲሆን የቁልቁለቱም ጉድጓድ የእርሱን ፍቅር መራቅ እንደሆነ አበው ያስረዳሉ።
ራስ ራሱን የቀጠቀጡት ወንበዴዎችም የሰውን ርእሰ ልቡና በክፉ መሻት፣በትዕቢትና በፍቅረ ዓለም በሎታ የሚቀጠቅጡ ባልፈጠሩት ፍጥረት ባልዋጁት ሰውነት ሠልጥነው የሚኖሩ ሥጋ አጋንንት ናቸው። ልብሱን መግፈፍም ቀድሞ የአዳምን ልብሰ ግርማና ብርሃን ማሳጣታቸው ሲሆን በሐዲስ ኪዳን ደግሞ አዲሱን ልብሳችን ክርስቶስን ያራቁቱን ዘንድ ርእሰ ኅሊናችንን የሚቀጠቅጡ ምሕረት የለሽ ሰይጣናት ናቸው። ሁለቱ አልፈው የሄዱ ካህናትም በክህነታቸው እግዚአብሔርን ቢያገለግሉም ነገር ግን ነገደ ሰብእን ከሞት ዕዳ ከኃጢአት ፍዳ ማውጣት ያልተቻላቸው መልከ ጼዴቅና አሮን እንደሆኑ ይተረጎማል።
የወደቀውን ያነሣው ደጉ ሳምራዊ ደግሞ ዘልማዱ ኂሩት - ልማዱ ቸርነት የሆነ ሰውን በመልኩ እንደገና በሐዲስ ተፈጥሮ ለማደስ የባርያን መልክ ይዞ የመጣ መድኀኒታችን ክርስቶስ ነው። እርሱ በቁስሉ ቤዛነት ታድጎ የምሕረት ዘይቱን አፍሶ የፍቅሩን ወይን ለግሶ፣ በደሙ አንጽቶ በልጅነት አክብሮ ዓለምን ታደገ።
ከዚያ በኋላ የሕሙማን የድኅነት ቤት ፣የኅዙናን ምስካይ የስደተኞች ቤት አዘጋጀ። ሕሙማንና ቁስለኞቹን የሚፈውሱ አስተማሚዎቹን አሰማርቶ ፈውሱልኝ ብሎ ሁለት ዲናሮችን ሰጠ።
ከላይ እንደ ተናገርነው ደጉ ሳምራዊ የተባለ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን የመጣ ጌታ ሲሆን እውነተኛይቱ ቤተ ፈውስም (ሐኪም ቤት) ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት። ሕሙማንን የምትቀልባቸው ቤቶችም የመጻሕፍት ትርጓሜ ቤቶች ናቸው።
ባለንበት ዘመንም እንደ ግልም እንደ ኅብረትም ከኢየሩሳሌም በእርግጥ ከዚህ በላይ ወርደን የምናውቅ አይመስለኝም። ከጽድቅ በኃጢአት፣ ከአንድነት በመለያየት፣ ከፍቅረ ቢጽ በፍቅረ ንዋይ፣ ከትሕትና በፍቅረ ሲመት፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር በፍቅረ ዓለም፣ ከእውነት በአድርባይነት፣ ከሰማይ መንግሥት በምድራዊነት በሚያጣድፍ ቁልቁለት እየወረድን እንደሆንን ቢያንስ ሊገባን ይገባል። ወንበዴዎች አጋንንትም አእምሯችን ቀጥቅጠው እንዳንደማመጥ፣ ዓላማ የለሾች እንድንሆን፣ነገ እንዳይታየን ፣ ማሰቢያችን ነስተው ከራሳችን ጋር እንዳንሆን በማባከን፣ በማደንዘዝ፣ ጥሩ አድርገው ደብድበውናል።
አልታመምኩም የሚል ካለ በእርግጥ እርሱ ከጽኑ ሕሙማን ውስጥ ነው። አንድ የሰውነት አካል ከአእምሮ ጋር መልእክት መታላለፍ ከቆመ ቢቆርጡትም አያምም ይላሉ ሐኪሞች። (በትክክል በሙያው አልገልጠው ይሆናል እታረማለሁ) አሁን ከክርስቶስ በረጅሙ ከመራቃችን የተነሣ መታመማችንም አናውቅም፣ ከሕይወታችን ራስ ከክርስቶስ ጋር የምንገናኝበት የሆነ መስመራችን ምን እየሆነ ይሆን?
አሁን ሁለት እድሎች አሉን። ወደ ደጉ ሳምራዊ የእንግዶችማረፊያ መመለስ። በሰጣቸው ሁለት ዲናርም ይፈውሱናል። አንደኛው ፈውስ ንስሐ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ወንጌል ነው።
የሕሙማን መታከሚያ ቤቶች ናቸው። ወንጌልም ዝገታችንን የምታርቅና ፊታችንን የምታበራ ዘይት ቁስላችንን የምታደርቅ ልቡናችንን በሐሤት ሰማያዊ የምትመላ ወይን ናት። ጥሪት ቁሪትን ዓላማ ያላደረጉ መምህራን ከንጉሥ ክርስቶስ የተሸለሟቸው ሁለቱ ዲናሮችም ብሉይና ሐዲስ ናቸው። በዚህ የሚፈውሱ የቤቱ እንግዳ ተቀባዮችም መምህራን ናቸው።
ከዚህ ተነሥተን የመጻሕፍት ትርጓሜ ት/ቤቶችን የደጉ ሳምራዊ (የቸሩ መድኃኔዓለም) የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች እንላቸዋለን።
በመሆኑም በዛሬው ዕለት ግንቦት ፲፮-፳፻፲፰ ዓም በደብረ ልዑላን ደብረ ታቦር መድኃኔዓለም ቤተ ጉባኤ በመመረቁ አንድ የሕሙማን ማረፊያ፣ በክሕደትም በኃጢአትም ከዓለም ፈልሰው የሚመጡት የመንግሥተ ሰማያት እንግዶች ማረፊያ ድንቅ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ቤተ ጉባኤ ተመርቆልናል። ከነ አስተናጋጆቹ ያልኩት ደግሞ የድኅነት አስተናጋጆች የወንጌል ማዕድ አቅራቢዎች፣ የመከሩ ሠራተኞች ወንድሞቻችን ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ጉባኤው ተሠርቶ ሲጠናቀቅ አብረው ስለ ተመረቁልን። የቤተ ጉባኤው የአራቱ ጉባያት ምስክር መምህር መምህረ መምህራን በጽሐ ዓለሙም ቤቱንም ሰውንም ሠርተው ስለሰጡን መምህር ሆይ እጅ ይባርክ ፣ ግሩም ሊቀ ጸረብት እንዲህ ያለም የለ ይበል ነው ብለናል!
ደክሞ የተማረ ሰው ታሞ ያስተምራል ፣እየታመመ ይፈውሳል፣ እንኳን ደስ ያለዎ፣ ዓይንዎትን በዓይንዎት እንኳን አሳየዎ። ወንድሞቻችንም እንኳን ከጸጋ መንፈስ ቅዱስ ተወለዳችሁልን። የወንጌል ዘራችሁን ያብዛው።
በሉ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ ወደ ተሠራልን ቤተ ጉባኤ በአህያም ቢሆን ተጭነን እንሂድ። መምህሩም በሁለቱ ዲናር ይፈውሱናል። ኧረ ትርፍ ወጭ አውጥተውም ይፈውሳሉ። እነ ታኦዶኮስ የመሰሉትንና ሌሎችን መጻሕፍትን ጽፈው ሰጥተውናልና።
የመምህራን አምላክ ሲመጣ በመማር፣ በማስተማር፣ በመፈተን የከፈሉትን ሁሉ ዋጋዎን ያስረክብዎ መምህር።
በተሠራልን የነፍስ የጤና ቤት ተምረን ለመፈወስ ያብቃን
ይቆየን !
አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር መምህር
1 month ago | [YT] | 3,505
View 56 replies
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
https://youtu.be/--9PyCp1p2g?si=uvAa_...
1 month ago | [YT] | 51
View 1 reply
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
https://youtu.be/AQMoa0amHeo?si=DIJwX...
1 month ago | [YT] | 49
View 1 reply
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
“መሠረተ ሕይወት ማርያም”
የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ተፈጠረ የሚያሰኘው አንዱ ሕያውነት ነው።ለዚያም የሚጠበቅበት አንድ ነገር አለ። ይኸውም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር መስማማት ነው። ያንን ፈቃደ እግዚአብሔር መስማማት በተውን ጊዜ ግን መዋትያን ሆንን። በጸጋ ያገኘነውን ሕይወት ስናጣ መሬት ነበርንና ወደ መሬትነታችን ተመለስን።በዚያው ቀንበርም የአዳም ልጆች ሁሉ ተገዛን። ምድራውያን ሆነናልና ፣ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎን ነበርና ልደታችንም የተናቀ ሆነ።ሮሜ ፫:፳፪ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ አንዲት ሴት ወንድ በወለደች የመንጻት ሕግ ተሠራላት።ዘሌ፲፪፥፩
ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር ግን ፍጥረታቱን እንደ ተጎዳን እንቀር ዘንድ አልተወንም። አብ ቢሉ በልጁ ፣ መንፈስ ቅዱስም በቃሉ ፣ ወልድም በአካሉ ሰው ሆኖ ይታረቀን ዘንድ ወደደ።
ለዚህም መላውን ፈትኖ አንዲት ሴትን አገኘ። ይህቺውም መርገም የሌለባት፣ በምልዐተ ኃጢአት ያልተዳደፈች ፣ ክብርን የተመላች ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ሰዎች ሁሉ በመርገምና በምልዐተ ኃጢአት ክብር ሲጎድላቸው ድንግል ማርያም ግን በሦስት ምክንያት ክብርን የተመላች ነበረች።
፩.ከመርገም ንጹሕ በመሆን
፪.ከምልዐተ ኃጢአት ንጽሕት በመሆን
፫.ከሰው ታጥተው የነበሩ የመንፈስ ቅዱስን ፍሬዎች ተምልታ በመገኘት ፡ እኒህም ትሕትና ፣ ሃይማኖት ፣ መታዘዝ ፣ ንጽሕና ናቸው።
ይህ ነው “እስመ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር - በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነት አግኝተሻልና” ያሰኛት።
በዚህ ባለሟልነቷም ክብርን ለብሳ ጸጋን ተመልታ ለዓለማት ፈጣሪ እናት ሆነችው። ከእርስዋ በነሣው ሥጋ በተቀበለው የቤዛነት ዋጅቶም የእርሱ ማኅበር ቤተሰብ አካል አደረገን።
ቅርንጫፍ በግንዱ ሕይወትነት እንዲኖር እርሱ የሕይወት የወይን ግንድ ሆኖ በቅርንጫፍነት ተዋሕደን እንኖር ዘንድ አደለን።
ስለዚህ አምላክን የወለደች ቅድሰት ድንግል ማርያም ትንሣኤና ሕይወታችን ከእርስዋ ይወለድ ዘንድ ክብርን ተጎናጽፋ ፣ ጸጋን ተመልታ የተገባች ስለሆነች የምንድንበት ቁርባን የሚሆን ሥጋውን ቤዛ የሆነባትን ነፍሱን ከእርስዋ ነስቶ ስለ ተዋሐደ መሠረተ ሕይወት እንላታለን። በእናትነቷም ፈጽመን እንወዳታለን። እንደ እናትነቷም በልጅነት ከእርስዋ ሥር እንጠጋለን። ልደቷም የፀሐዩን ልደት የሚያበሥር ጎሕ ነው። ልጅዋን ግን የማዕዘናችን ራስ ብለን እናመልከዋለን። ከዚህም የተነሣ እመቤታችን ስለ ተወለደችልን ደስታችን ዕጥፍ ነው።
መሠረተ ሕይወት ከሚለው ጋር ዛሬ አንድ ነገር ላንሣ። ይህንን ቃል አንድ ደጅ ላይ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አይቼው ነበር አክሱም። ከእማሆይ ወለተ ሕይወት ቤት። እማሆይ ወለተ ሕይወት ከየኔታ ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው ቅኔን (ጨጎዴ) ፣ ከየኔታ ሄኖክ (አክሱም) መጻሕፍተ ብሉያትንና መጻሕፍተ ሐዲሳትን የተማሩ፣ ምንኩስናን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕውቀትና በኦርቶዶክሳዊ አእምሮ አካተው የያዙ ልባም እናት ናቸው። እማሆይ መጀመሪያ ሰው ከቤታቸው ሲሄድ በሌለ ቤታቸው በእናትነት ባለጸግነት በብሩህ ፊት ይቀበላሉ ሐዲሳቱን ጠንቅቀው ያወቁ ሲሆን በትሕትና ይጠይቃሉ። መምህር ከቤታቸው ከሄደ ያላቸውን በልግስና መግበው ከዚያ ወሬ የለም። መጽሐፍ ያቀርቡና ይተርጉሙልኝ ይላሉ። የጥበብ ፈላጊዋ የንግሥት ማክዳ ምልክት። እማሆይ ማንም እቤታቸው ሄዶ ሳንቲም ልስጥ ቢላቸው በጄ አይሉም። አንድ ጊዜ ካናዳ የሚኖሩ አንድ አባት ስለ እማሆይ ነግሬያቸው አስተባብረው ብር ልላክላቸው ብለው ብጠይቅ የባንክ ቁጥር አልሰጠኝ ብለው ቀርተዋል።
የእናቶቻችን መናንያት የቅዱሳት ልጅ ናቸውና።
እማሆይ እንግዳ መጣ ብለው ወንበር የማይፈቱ የቀለም ትግሕት የቀለም እናት ናቸው። እማሆይ የቀለም እንጅ ሥጋዊ ዘር የሌላቸው የቤተ ክርስቲያን አንድነቷ ልጅ ናቸው። የመምህር ገብረ ጊዮርጊስ ልጅ ናቸውና።
መምህር ገብረ ጊዮርጊስ ትውልዳቸው አክሱም ሲሆን መምህርነታቸው ግን ደብረ ሃይማኖት መካነ ኢየሱስ ነው። ባሕታዊዉ ሊቅ የኔታ ገብረ ጊዮርጊስ በደብረ ሃይማኖት መካነ ኢየሱስ ቅኔና መጻሕፍትን ለረጅም ዓመታት አስተምረው ራሳቸውን በጸጋም በጥበብም አሳክለው መምህር ኃ/ሚካኤልን ተክተው ሊያርፉ ሲሉ አክሱም ተመልሰው መምህር ሄኖክን ለአክሱም ተክተው አረፉ። እርሳቸውም እማሆይ ወለተ ሕይወትን ተክተውልን ነበር። አክሱም ሄጄ ሳለ የየኔታ ገብረ ጊዮርጊስን ፎቶና እጅ ጽሑፍ አእማደ ምሥጢር አሳይተውኝ አብረን ተላቅሰናል። የኔታ ገብረ ጊዮርጊስ ደቀ መዛሙርትን በመንደር ለምነው መግበው ሲጨርሱ በኋላ የሚቀምሱ በመንኖ ጥሪት የታወቁ ሊቅ ናቸው። እማሆይም ይኸው የአባታቸው ልጅ ናቸውና ፍቅረ ንዋይን አሽቀንጥረው እንደጣሉት ሄዱ።
እማሆይ ሰው የሚያበረቱ፣ ትምህርት በቃኝ የማይሉ እናት ናቸው። ብሉይ ኪዳን እንዳጠናቀቅሁ ነበርና መጀመሪያ የሄድኩት “ ሊቃውንቱንም ተማርና በኋላ ከአንተ እማራለሁ“ ያሉኝ እናትነታቸው ጉልበት የሚጨምር ምክር ነበር። እማሆይ ለዕቅበተ እምነት ካላቸው ፍቅር የተነሣ “ለምን እንደ አባቶቻችን ጉባኤ እየተደረገ የሚጠራጠሩ ሁሉ በጉባኤ አይጠየቁም“ እያሉ በልባቸው የሃይማኖት እሳት የሚነድባቸው እናት ነበሩ።
ከእማሆይ ከቤታቸው ከበሩ ከሳንቃው ላይ “ መሠረተ ሕይወት ማርያም “ የሚል ጽሑፍ አለና፣ ለምንድን ነው ብየ ስጠይቃቸው: የቅኔ መምህርት ስለሆኑ እንዲህ ብለው መልሰውልኝ ነበር።
“አንደኛ በእመቤታችን ምክንያት ጌታ ተወልዶልናል። ሁለተኛ የእኔም (ስማቸው ሕይወት ስለሆነ) መነሻየና መድረሻየ ከልጇ የምታደርሰኝ እርስዋ ናት” አሉኝ።
ክብርት እናታችን እነ የኔታ እርስዎን እንዳስገኙ እርስዎስ ማንን ተክተውልን ይሆን? የእነ የኔታን መጽሐፍ ከእርስዎ አገኘነው የእርስዎንስ ጨምሮ ደግሞ ማን ያሳየን ይሆን?
እናቴ:ብዙ ስለ ቤተ ክርሰቲያን ተነጋግረን የጦርነት ጨለማ ሳያስተያየን ሄዱ?
እናታችን የምርም በእመቤታችን ፍቅር መቆምዎትን በልደቷ አርፈው መሰከሩ።
እውነትም መሠረተ ሕይወት ማርያም
አባ ገብረ ኪዳን
የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር መምህር
1 month ago | [YT] | 3,524
View 66 replies
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
https://youtu.be/3PwPN2pvSv0?si=9xHuU...
1 month ago | [YT] | 26
View 0 replies
Load more