🌍 Welcome to our channel dedicated to exploring the rich history and impactful contributions of the Argoba people to Islam in Ethiopia. Join us as we delve into the fascinating history of the Argoba community and uncover their role in shaping the religious landscape of the region.

🕌 In addition to exploring the history of the Argoba people, we also delve into various Islamic issues, promote peace, unity, and brotherhood within the ummah. Our goal is to foster a sense of unity and harmony among all Muslims, celebrating the diversity within our community while emphasizing the values of peace and solidarity.

🤝 Come along on this journey of discovery and enlightenment as we highlight the shared heritage and interconnectedness of the Muslim world.

Don't forget to like, subscribe, and hit the notification bell to stay updated on our latest videos. Thank you for being a part of our community and supporting our mission of knowledge, unity, and peace to keep the ummah united.


Awfat Tube

የነቢዩ ሰለሏሁ አልይሂ ወሰለም መስጂድ ኢማም ና በሳኡዲ የከፍተኛ ኡለማዎች ምክር ቤት አባል የነበሩት የታላቁ ሊቃውንትና ሼይኽ - አብዱልመጂድ ቢን ሀሰን አል-ጀባርቲ (1332-1418 ሂጅራ) አጭር ታሪክ ።

ሼክ አብዱልመጂድ አል-ጀበርቲ በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ከሚገኙ ታላላቅ ሊቃውንት መካከል አንዱ የነበሩ ሲሆኑ፣ በተቅዋቸው፣በስነ ምግባራቸው እና ዲን አገልጋይነታቸው በእጅጉ ይታወቁ ነበር ።

በሐያት በነበሩበት ወቅት በመዲና በሚገኘው የነቢዩ (ሰለሏሁ አለይሒ ወሰለም) መስጂድ ኢማም እና ዳኢ፣የከፍተኛ ምሁራን ምክር ቤት አባል ፣የላዕላይ ዳኞች ምክር ቤት አባል፣በበርካታ የሳዑዲ ከተሞች ዳኛ በሻቅራ የመጀመሪያው መደበኛ ትምህርት ቤት መስራች እና የመጀመሪያ ርእሰ መምህር ፣ የመሳሰሉትን በርካታ ቁልፍ የሚባሉ ቦታዎችንና ሐላፊነቶች የመሩ ታዋቂ የሀገር ሽማግሌ ፣ሙሑርና የተከበሩ ሰው ነበሩ። ነገር ግን ምንም እንኳን ትልቅ ስም ፣ዝናና አስተዋጾና የነበራቸው አሊም ቢሆኑም ዛሬም ብዙ ሰዎች የሳቸውን legacy አያውቁም።

ሙሉ ስማቸው አብዱልመጂድ ቢን ሀሰን ቢን አህመድ ቢን ሙስጠፋ አብዱ ቢን ከሊፋ ቢን አቡዘር ቢን ሱለይማን ቢን ሲራጅ አል-ጀባርቲ ሲሆን ከ ኣለዊ (አርጎባ) የዘርሐረግና ኣለከቢር ጎሳ የተገኙ ናቸው።

** እንደመረጃ አርጎባ (ጀበርቲ) በውስጡ ሸሪፍ፣ኣለከቢር (አደከቢር) ፣አስቃሪ ፣ዶብኣ፣ወላስማ መለሳይ፣ሹጉራ..ኣዲያ(ሐረርአርጎባ) የመሳሰሉትና.ሌሎችም በስፋት የሚጠቀሱ ጎሳዎች ይዟል **

ትውልዳቸው በ1331/ 1332 ሂጅሪያ በቀድሞ ጅማ ጠቅላይ ግዛት በጥንት ኢስላማዊ መእከል በነበረችው በጅማ አባ ጃፋር ጂሬን በተባለች መንደር ሲሆን ወላጆቻቸው ከጎንደር ወደ ዚች መንደር እንደሄዱ ተገልፇል።

**በነገራችን ላይ አባጅፋር እንደነ ሸኽ ሙሐመድ ቆራሬ የተባሉ ታላላቅ ኡለማዎችና ሸይኾች ከይፋት አስመጥተው አካባቢው ላይ እስልምናና ኢልም እንዲስፋፋ ማድረጋቸውና ከቤተሰቦቻቸውም ጋር በጋብቻ ማስተሳሰራቸው በተለያየ ግዜ በተለያዮ ሸይኾችና ሰነዶች ተገልጿል ፣ በተመሳሳይ ወደጎንደርም እስልምናን ያደረሱት የይፋት ሰዎች ጀበርቶች እንደሆኑ እስከዛሬም ድረስ ኢስላም ጌ (የሙስሊም ሐገር)፣ደረስ-ጌ (የደረሳ ሐገር) ፣ዋሰል የተባሉ የአርጎባ ስያሜዎችን የያዙ መንደሮች ላይ ከይፋት የሔዱ የአርጎባ ተወላጆች እንደሚኖሩበት ይታወቃል **

ቅድመ አያቶቻቸው፣ በ12 ክፍለ ዘመን ከሀድራመውት (የመን) ወይም ዋዲ ፋጢመት ዲን ለማስተማር በብዛት መጥተው በሓበሻ ምድር ከሰፈሩ የአረብ ጎሰዎችና በሐበሻ በሙስሊምነታቸው ከሚታወቁት ማህበረሰብ ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣ ትውልድ የተገኙ መሆናቸውም አብሮ ተጠቅሷል።

ሸይኽ አብዱልመጂድ በ13 አመታቸው ወደ መካ የሔዱ ሲሆን ሐገር ውስጥ በነበሩበት ወቅት ቁርኣንን በሉህ እና መድ እየከተቡ በሚገባ ሐፍዘዋል። ቡሓላም ፣ አረብኛ ሰዋሰው(ነህው) ፣ አል-አጁሩሚያ ፣ ሙልሃት አል-ኢራብ፣አልፊያህ ኢብኑ ማሊክ እና ሻፊዒይ ፊቅህ ሸርህና መትኖችን ሐበሻ እያሉ በሸኽ ሐሰን አቡ ኺያር ፣ ወደ መካ ከሔዱም ቡሓላ በሼክ ጀማል አልማሊኪና ሼክ አብዱል አዚዝ አልማሊኪ ላይ ቀርተዋል ። በኋላም ወደ መዲና ተዛዋውረው በነ ሸይኽ ሙሐመድ አል-ተይብ አል-አንሷሪ፣ ሼክ አሚን ሙርሺድ፣ሼክ አብዱል ራኡፍ አል-ሚስሪ አል-አዝሃሪ፣እና ሌሎች ላይ ፣ተውሒድ ፊቅህ ሐዲስና የመሳሰሉትን ተምረዋል (ቀርተዋል) ።

በ1352 ዓ.ም በመዲና ሸሪዓ ሳይንስ ትምህርት ቤት ተመዝግበውም በ1355 ሂጅራ ተመርቀዋል።

ቀጥለውም በተሰማሩበት ሸይኽነትና የኢማምነት አገልግሎት እጅግ ቡዙ ታላላቅ ኡለማዎችን፣በሐገሪቷ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ፈጣሪ ሰዎችን ማፍራት ችለዋል።

እንደነ ሼክ አብዱላህ አል-ማነአ ፣ሼክ ሳሊህ አል ሁሴን፣ሼክ አብዱራህማን አልሳድሃን አብዱላህ አል-ማኔያ በመሳሰሉት ታላላቅ ሙሁራንና ሸይኾች እንዲሁም ከፍተኛ ባለ ስልጣኖች ስለረጅም ዘመን ላበረከቱት ታላቅ አገልግሎታቸው፣ መልካም ባህሪ፣ የትልቅ እውቀት ባለቤትነታቸውና ተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው ምስክርነት ፣ምስጋናና እውቅና ተችረዋል።

እንደ አል-ሪያድ ባሉ ታዋቂ ጋዜጦች ላይ ስለ ጠንካራ ስብዕናቸው፣ ፈሪሃ አላህ ተቅዋ እና ያከናወኗቸውን ታላላቅ ተግባራት ( የትምህርት ካሪኩለምን ጭምር) አስመልክቶ ስማቸው ተጠቅሶ በቡዙ ተፅፎላቸዋል።

በሻቅራ የመሰረቱት ትምህርት ቤትና በዘረጉት ጠንካራ ሥርዓተ -ትምህርት ምክኒያት ትምህርት ቤቱ ከዛሬዎቹ ሁለተኛ ደረጃ ተቋማት ጋር በጥንካሬ ተነፃፃሪ ደረጃ የሚደርስ መሆኑ ተመስክሮለታል።

በ1371 አመተ ሂጅሪያ በመስጂደል ሐረም የነብዮ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መስጂድ በኢማምነት የተመደቡ ሲሆን ከመሞታቸው ጥቂት አመታት ቀደም ብለው በህመም ምክንያት እስካቋረጡበት ግዜ ድስ ለረጅም አመታት በኢማምነት ሲያሰግዱ ቆይተዋል።

በመጨረሻም ቅዳሜ ሸዋል 17, 1418 ሂጅራ በመዲና አርፈዋል። የቀብር ስነስረኣታቸውም በነብዩ(ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም) መስጂድ ቡዙ ሰዎች በተካፈሉበት ሽኝት ቡሓላ በበቂእ መቃብር ስፍራ ተከናውኗል ።

ሸይኽ አብዱልመጅድ የቀድሞ የንጉስ ፈይሰል ስፔሻላይዝድ ሖስፒታል ፕሬዝዳንት እንዲሁም በኑጉስ ፈህድ ኢብኑ አብዱል አዚዝ ወቅት የንጉሳውያን ክልኒኮች ጠቅላላ ተቆጣጣሪ የነበሩት ምኒስትር ዶር #አንዋር አልጀበርትይ አባት ሲሆኑ የመዲናው ሐረም መስጅድ ኢማም የሆኑትም የዶክተር #አህመድ ብን ጧሊብ ሃሚድ ቅድመ አያት(የሸህ አህመድ የናታቸው አያት) ነበሩ።

እኘህ ታላቅ የሐበሻና የመላው ሙስሊም ኩራት የሆኑትነ ሸይኽ አላህ ደረጃቸውን በጀነት ከፍ ያድርግላቸው ፣ለእስልምና ፣ለትምህርት እና ለፍትህ መስፈን ላደረጉት አገልግሎትና አበርክቶ አብዝቶ ይክፈላቸው።

ምንጭ : በ ተርኪ አደኺል በአረብኛ ቋንቋ ከቀረበው የህይወት ታሪካቸው ተቀንጭቦ ወደ አማርኛ የተተረጎመና ከጥቂት ማብራሪያ ጋር አጥሮ የቀረበ ።

https://www.facebook.com/100000118757360/posts/28931608413093066/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

#الشيخ_عبدالمجيد_الجبرتي
#الشيخ_أحمد_بن_طالب_حميد_الجبرتي
#امام_المسجدالنبوي_الشريف
#ኢማምመስጂድአነበዊ

#shaikh_Abdulmajid_bin_hasan_aljabarty
#Shaikh_Ahmed_bin_Talib_hamid_Aljabarti

7 months ago | [YT] | 0

Awfat Tube

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሙስሊም ሱልጣኔት ሸዋ መኽዙም ሱልጣኔት ታሪክ ።
The History of Argoba &Islam in Ethiopia

10 months ago | [YT] | 0

Awfat Tube

የኢማሙ ነዎዊ ሸሪካ፥ ሐበሻዊው ፈቒህ አህመድ!
ከሸዋሮቢት ከተማ(ሰሜን ሸዋ) 15 ኪ.ሜ. እርቆ የሚገኘው ጥንታዊው የጎዜ መስጅድ በ722 ዓ.ኢ. እንደተመሰረተ ይነገራል።¹

መስጅዱ በቀደሙ ዘመናት - የአምልኮ ክንውን፣ የዕውቀት ሽግግር፣ የመንፈስ እነጻ(ተርቢያ)፣ ልዩ ልዩ ማሕበራዊ ጉዳዮችም ይስተናገዱበት እንደነበር ይታመናል። ይኽ ጥንታዊና ታሪካዊ ቅርስ በአሁኑ ወቅት ሰፊ ጥገናና ድጋፍ የሚሻ ኾኖ ይገኛል። ቅርሱ ከመውሊደ-ነቢ(ﷺ) እና ከባህላዊ በጎ በዓላት ጋር ብቻ የተቆራኘበት ትርክትም የእርቃት ሚዛን ያሻዋል።

በጎዜ አካባቢ ከሚወሱ ዓሊሞች መካከል ፈቒህ አህመድ አቡበክር ስመ ትልቁ ናቸው። በታሪክ ንበራም ይጠቀሳሉ። ኾኖም በኖሩበት የዘመን እርቀት፣ ባልተገናዘበ የታሪክ ስነዳና የመረጃ ሽግግር ክፍተት ምክንያት ግን የተሟላ ታሪካቸው ለአደባባይ አልበቃም። አልተጠናም።

ከረዥም የዘመን ሽግግር በኋላ የመረጃ ክፍተቱን በሚጠግን መልኩ የወለኔው ሸህ ዑመር በሽር(ህ-1930) “አዘሀቡል ኢብሪዝ” በተሰኘ የታሪክ ኪታባቸው - ፈቒህ አህመድ የኢማሙ ነዎዊ(1233-1277) 'ሸሪካ' እንደነበሩ የሚነገር መኾኑን ጽፈዋል።(ገጽ-215)

መረጃው ከ90ዎቹ ዓመታት በፊት በታማኝና በአንጡራ ዓሊም የተጻፈ በመኾኑ ሰፊ ትኩረትና ጥናት ይፈልጋል። የሐበሻ ዑለማዎች ከምዕት ዓመታት በፊት በዒልምና በመንፈስ ትጥቅ ምሉዕ እንደነበሩም ፍንጭ ይሰጣል። እንዲህ ዓይነት ወርቃማ ታሪክና ትርክቶችን አጥንቶና አፍታትቶ - ለአዲሱ ትውልድ የመንፈስና የህሊና ስንቅ ማድረግ ያሻል!!!
(ምስል፡ ከሶሻልሚዲያ፦ የጎዜ መስጅድ ከፊል ገጽታ)

1 year ago | [YT] | 2

Awfat Tube

االجبرت في السودا نفس الجبرتي في يفات ارغوبا .
Jebrti found in many countries the one in Ethiopia called Argoba -jebrti and the village jebrta that mentioned by Historians found in Yifat too.the capital of yifat welasma sultanet .

2 years ago | [YT] | 0