ልደትዬ እናቴ

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር


ልደትዬ እናቴ

አባ መፍቀሬ ሰብእ ወመፍቀሬ አምላክ

የደሴ ማኅቶት ፤ የላሊበላው መብራት ፤ የግሸኑ ድምቀት

እንኳን ለሰው ይቅርና ለዕፅዋትም አባት መሆን የቻሉ ዋርካ

የቅጽረ ቤተ ክርስቲያን አበቦችን በፍቅር የሚንከባከቡት እኚህ መናኝ በዘመነ ጽጌ (በአበባ ወራት) ወደሰማያዊው ቤታቸው ተጠርተዋል::

ሳር ቅጠሉ የሚያከብራቸው ሃይማኖታቸውን ባይከተል እንኳን አባትነታቸውን የሚወድላቸው የምናኔ ምሳሌ የብሕትውና ጥግ በረከታቸው ይደርብን:: ለአባ መፍቀሬ ሰብእ በሕይወታቸው ሳሉ የሚገባቸውን ክብር ለሠጣችሁ የደሴ ምእመናን እግዚአብሔር ያጽናችሁ::

አባ ጸሊ በእንቲኣነ

"መፍቀሬ ነግድ፣ ዘሠናይ ምግባሩ ዘአንጽሐ ርእሶ ጻድቅ፣ ወኄር፣ ወየዋህ፣ ወመስተዓግሥ" ቲቶ 1:8

1 year ago | [YT] | 0

ልደትዬ እናቴ

✞ እንኳን አደረሰን !

" ... ዓቢየ እግዚእ ነዓ ምስለ ገብርኤል መልአከ ዳኅና፤
ታብዕለኒ በንዋዮሙ ውዱሰ ነገር ወዜና፤
ለኢየሉጣ ሰማዕት ወቂርቆስ ሕጻና!"
                           (መልክዐ አቡነ ዓቢየ እግዚእ)

" ... ገብርኤል ውኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ፤
አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ፤
ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ!"
                            (መልክዐ ቅዱስ ገብርኤል)

" ሰላም ለክሙ ጥቡዓነ ልብ ወሕሊና፤
ሰማዕታተ ክርስቶስ ዘሃገረ እስና፤
ምስለ አብ ወእም ወምስለ ሕጻና፤
ዘቀተሉክሙ ወዓልተ መኮንን አርያና፤
እንበለ ያትርፉ አሐደ ለዜና!"
                             (አርኬ)

❖እኅተ መላእክት ፥ እመ ሰማዕታት ፥ ተስፋ መነኮሳት ፥ አክሊል ንጹሕ ለካህናት የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም በረድኤት አትለየን!

ከበረከታቸውም ይክፈለን!

✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት

🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል)
🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)

1 year ago | [YT] | 0

ልደትዬ እናቴ

የካቲት 16
ኪዳነ ምህረት

‹ ኪዳን › የሚለው ቃል ‹‹ ተካየደ – ተዋዋለ ፤ ቃል ኪዳን ተጋባ ፤ ተማማለ ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ፣ ትርጕሙም ኪዳን፣ ውል ፣ መሐላ ፣ ቃል ኪዳን ፣ የውል ቃል ማለት ነው /ዘዳ.፳፱፥፩፤ ኤር.፴፩፥፴፩-፴፫፤ መዝ.፹ ፰፥፫/፡፡ በሌላ በኩል ኪዳን የጸሎት ስም ሲኾን፣ ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ፣ ከማረጉ በፊት ለሐዋርያት ያስተማራቸው ጸሎት ኪዳን ይባላል፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳን (ውል ፣ ስምምነት) የተቀበለችበት ዕለት (የክብረ በዓል ስም) ደግሞ ኪዳነ ምሕረት ይባላል፡፡

በየዓመቱ የካቲት ፲፮ ቀን የምናከብረው ይህ በዓል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጎልጎታ በልጇ በመቃብር ላይ ኾና ‹‹ ኦ ወልድየ ወፍቁርየ እስእለከ በእንተ ዘተሰባእከ እምኔየ ወበማኅፀንየ ዘጾረተከ፤ ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ ፤ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ ፤ ከአንተ ጋር ከአገር ወደ አገር ስለመሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ ›› እያለች ስትጸልይ ጌታ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ ወደእርሷ መጥቶ ‹‹ ሰላም ለኪ ማርያም እምየ ፤ እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው? ›› አላት፡፡

እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትንና መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን ፤ ዕጣን ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን ፤ ለእመቤታችንና ለሃይማኖታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ልጆቻቸውን በስሟ የሰየሙትን ዅሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡

ጌታችንም ‹‹ ይህን ዅሉ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበአቡየ ወበመንፈስ ቅዱስ ሕያው፤ በራሴ፣ በአባቴ እና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ›› ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በቅዳሴው ‹‹ … ዳግመኛም በእናትህ በማርያም ተማፅነናል፤ ይህችውም አንተን በመውለድ እመቤታችንና የባሕርያችን መመኪያ ናት፡፡ አንተ ‹ መታሰቢያሽን ያደረገ ፣ ስምሽንም የጠራ ፣ የዘለዓለም ድኅነትን ይድናል› ብለሃታልና …፤›› በማለት የሚማጸነው፡፡

በተአምረ ማርያም መጽሐፍ እንደተመዘገበው በዚህ ዕለት የሚታሰቡ ሁለት ተአምራት አሉ፤ ከእነዚህም አንደኛው የስምዖን ታሪክ ነው፡፡ ስምዖን የሚባል እንግዳ ተቀባይ ደግ ሰው ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያፍርምና ከዕለታት አንድ ቀን በእንግድነት ከቤቱ ገብቶ ‹‹ልጅህን አርደህ ካላበላኸኝ ሌላ ምግብ አልበላም›› አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ስምዖን ሲያወጣና ሲያወርድ ቆየና ‹‹አብርሃም ልጁን ሰውቶ ነው የእግዚአብሔር ሰው የተባለው ›› በማለት፣ ‹‹ የእግዚአብሔርን እንግዳ›› ላለማሳዘን ሲል ልጁን አርዶ አቀረበለት፡፡

እንግዳ መሰሉ ሰይጣንም ሥጋውን ቅመስልኝ ብሎ ግድ አለው፡፡ ስምዖንም (በላዔ ሰብእ) አርዶ ያዘጋጀውን የልጁን ሥጋ በቀምሰ ጊዜ ሰይጣን ስላደረበት (ስለተዋሐደው) ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ቤተሰቦቹን፣ ጎረቤቶቹንና መንገደኛውን ዅሉ ይበላ ጀመር፡፡ በአጠቃላይ ፸፰ ሰዎችን ከበላ በኋላ አንድ በቍስል የተመታ ሰው አገኘና ሊበላው ሲል ‹‹ውኃ አጠጣኝ›› ብሎ በሥላሴ፣ በቅዱስ ሚካኤል፣ በቅዱስ ገብርኤል ስም ለመነው፤ እርሱም ዝም አለው፡፡

በመጨረሻም ‹‹ በድንግል ማርያም ስም ›› አለው፡፡ ስምዖን የእመቤታችንን ስም በሰማ ጊዜም ወደ ልቡናው ተመልሶ ‹‹እስኪ ቃሉን ድገመው ›› አለው ፤ በሽተኛውም መልሶ ‹‹ ስለ ድንግል ማርያም ውኃ አጠጣኝ›› ብሎ ለመነው፡፡ ያን ጊዜ ‹‹ይህችስ እንደምታስምር በልጅነቴ ሰምቻለሁ ›› ብሎ ጥቂት ውኃ ሰጠው ፤ ውኃው ጕሮሮውን እንኳን ሳያርስለት ‹‹ ጨረስህብኝ ›› ብሎ ነጥቆት ሔደ፡፡

በሌላ ቦታም አንድ ገበሬ አግኝቶ ሊበላ ሲል ገበሬው ‹‹በላዔ ሰብ የምትባል አንተ ነህ? ›› ባለው ጊዜ ‹‹ ለካስ አመሌን ሰው ዅሉ አውቆብኛል ›› ብሎ ዋሻ ገብቶ በመጸጸት በዚያው ሞተ፡፡ ነፍሱንም መላእክተ ጽልመት መጥተው ሲወስዷት እመቤታችን ‹‹ልጄ በማይታበል ቃልህ ይህችን ነፍስ ማርልኝ? ›› አለችው፡፡

ጌታችንም ‹‹ ሰባ ስምንት ነፍስ ያጠፋ፣ ፈጣሪውን የካደ ሰው ይማራልን? ›› አላት፡፡ እመቤታችንም ‹‹በስሜ የተጠማውን ውኃ አጥጥቶ የለምን?›› ብላ ስምዖንን (በላዔ ሰብእን) አስምራዋለች፡፡ ነፍሱንም መላእክተ ብርሃን መጥተው ወደ ገነት አስገብተዋታል፡፡

ሁለተኛው ተአምር ደግሞ ከብሮ ከኖረ በኋላ ለድህነት በተጋለጠ አንድ ምእመን ላይ የተደረገ ነው ፤ ከክርስቲያን ወገን የኾነ ሀብት አግኝቶ ያጣ አንድ ሰው ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ‹‹ ከብሬ በኖርኹበት አገር ተዋርጄ አልኖርም ›› ብሎ ጓዙን ጠቅልሎ ከአገሩ ወጥቶ ሲሔድ ሰይጣን ያዘነ ሰው መስሎ ደንጊያውን በምትሐት ወርቅ አስመስሎ ‹‹ ሥላሴን ፣ ጻድቃንን ፣ ሰማዕታትንን ፣ መላእክትን ካድልኝና ይህን ወርቅ እሰጥሃለሁ ›› አለው፡፡ ዅሉንም ካደለትና ወርቁን ተቀብሎ ዞር ሲል ‹‹ ምእመናን የሚመኩባት ድንግል ማርያም ‹ የአምላክ እናት አይደለችም› ብለህ ካድልኝ ›› አለው፡፡

ሰወየውም ‹‹ እርሷንስ አልክድም ›› ስላው በደንጊያ ቀጥቅጦ ገደለው፡፡ መላእክተ ጽልመት የሟቹን ነፍስ ሊወስዱ ሲሉ መላእክተ ብርሃንም አብረው ቀረቡ፡፡ እመቤታችንም ጌታችንን ‹‹ ልጄ ይህችን ነፍስ ማርልኝ?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ከልብኑ ይትመሐር እምየ፤ እናቴ፣ ውሻ ይማራልን?›› አላት፡፡ እመቤታችንም፡- ‹‹‹ ስምሽን የጠራውን፣ መታሰቢያሽን ያደረገውን እምርልሻለሁ › ያልኸው ቃል ይታበላልን? ›› አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ ‹‹ምሬልሻለሁ›› አላት፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ‹‹ ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ ›› ባለው መሠረት ከቅዱሳን ጋር ያደረጋቸው ቃል ኪዳኖች ብዙዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል ከላይ በተአምራቱ እንደተመለከትነው አንዱ ለእመቤታችን የሰጠው የአማላጅነት ኪዳን ነው፡፡ ማማለድ ማለት ስለሌላው መጸለይ፣ መለመን ፣ የደረሰውን ችግር እንዲወገድ ማድረግ ፣ ማስማር ( ይቅርታ ማሰጠት ) ማለት ነው፡፡

በዚሁ መሠረት ከእግዚአብሔር በታች ከቅዱሳን ዅሉ በላይ ከፍ ከፍ ያለችና የከበረች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር በተሰጣት የማማለድ ሥልጣን ‹‹ ሰአሊ ለነ ቅድስት ፤ ቅድስት ሆይ ለምኚልን ›› እያሉ ለሚለምኗት ዅሉ ከእግዚአብሔር እያማለደችና እየለመነች ምሕረትን እንደምታሰጥ ቀናውንና የተመሰገነውን ሃይማኖት የምንከተል ምእመናን ዅሉ እናምናለን፡፡ ምክንያቱም ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር እናትና አገልጋይ እንደመኾኗ ከዅሉም ቅዱሳን በበለጠ ለእግዚአብሔር ቅርብ ናትና፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድም ኾነ በሰው ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘት ወይም ቅርብ መኾን ደግሞ አንድን ጉዳይ በቀላሉ ለማስፈጸም ይጠቅማል፡፡ ለምሳሌ፡-

👉 መልአኩ ቅዱስ ገብርአል በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ባለሟል በመኾኑ የድኅነትን ምሥጢር አብሣሪ ኾኗል /ሉቃ. ፩፥፲፱-፳፮/፡፡
👉 አስቴር የንጉሡ አርጤክስስ ሚስት በመኾኗ በወገኖቿ አይሁድ የታወጀውን የሞት አዋጅ አስለውጣለች /መጽሐፈ አስቴር ፫፥፲/፡፡
👉 ነቢዩ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ባለሟል በመኾኑ ‹‹ይህንን ኀጢአታቸውን ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን እኔን ከጻፍከው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ?›› በማለት ለእስራኤላውያን ምሕረትን አሰጥቷል /ዘፀ.፴፪፥፲፬/፡፡

2 years ago | [YT] | 3

ልደትዬ እናቴ

"በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በፍፁም መንፈሳዊ መሪነትና ክብር ሄደናል፤ እግዚአብሔር ሰምቶናል፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩም ለጥያቄዎቻችን መልስ ተሰጥቶናል::" ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የነበረውን ውይይት አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ብፁዕነታቸው እንደገለጹት ትናንት በሰጠነው መግለጫ “በአስቀመጥነው ቅድመ ሁኔታ መሠረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠርተን ጥያቄያችንን አቅርበናል፡፡ ጥያቄያችንም አንድ ነው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይከበር፤ በሀገሪቱ ያለው ኦርቶዶክሳውያን መብት ይጠበቅ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብትና ንብረት በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ንብረቷ ይጠበቅ፤ እነዚህ ካልሆኑ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ እንሄዳለን ማለታችን ይታወሳል፡፡ በዚህም በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በፍፁም መንፈሳዊ መሪነትና ክብር ሄደናል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበረን ቆይታ በደንብ ተወያይተንበት ለጥያቄዎቻችንም መልስ ተሰጥቶናል ብለዋል ብፁዕነታቸው፡፡ እንዲሁም ዝርዝር መግለጫውን ነገ የምንሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

2 years ago | [YT] | 1

ልደትዬ እናቴ

ከቅዱስ ሲኖዶስ ጎን እንቁም!
ዲን. ሄኖክ ሃይሌ
እምነ በሃ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን - ቤተ ክርስቲያን እንደምን አለሽ?

ከማሃ ኀዘን ወተሰዶ ሶበ በኩለሄ ረከቦ
ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ::
እንደ እርስዋ ኀዘንና ስደት የደረሰበት ሰው
የልብ ዓይን ያለው አይቶ ያልቅስ::

"የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል?" ኢሳ 53:1

ያልተቀደደችውና ከላይ ጀምሮ ወጥ የሆነችው የክርስቶስ ቀሚስ ከዚህ ዓለም ያልሆነችው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ ለአራት የተከፈለው ደግሞ የምታስተምረው ወንጌል ነው፡፡ ወንጌል ሊከፋፈልና ለዓለም ሁሉ ሊዳረስ ይችላል፡፡ ወንጌል በዘር በቋንቋ በሀገር አይገደብምና የክርስቶስ ወታደሮች የሆኑ ካህናትና መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን ተከፋፍለው ለዓለም ማከፋፈል አለባቸው፡፡

አብያተ ክርስቲያናት በየሀገራቱ ቢቋቋሙ ፣ አህጉረ ስብከቶች ቢስፋፉ ፣ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ ሊቃውንት ፣ ሰባክያን በቁጥር በዝተው ፣ በቦታም ተከፋፍለው ቢያገለግሉ እጅግ መልካም ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በሁሉ ጎዳና … ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል›› እንዳለ የመምህራን መብዛት የወንጌል መስፋፋት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ (ፊል. ፩፥፲፰)

ቀሚሱ የተባለችን ቤተ ክርስቲያንን ከተቃደዷት ግን አደጋ አለው ፤ ‹የሐዋርያት በሆነች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን› ብለን የምንናገርላት ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ቀሚሱ ናት፡፡ በሰው እጅ ያልተሰፋች ፣ ማንምም ሊሠፋት የማይችል ቀሚስ ናት ፤ ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆና በመሠራቷም አትከፋፈልም፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሊከፋፍሏት የሚፈልጉ ሰዎችን አውግስጢኖስ እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል ፡- ‹‹ሮማውያን እንኳን ያልቀደዱትን የክርስቶስን ልብስ እናንተ ስለምን ትቀድዱታላችሁ?››

"ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቡአት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን"

ከቅዱስ ሲኖዶስ ጎን እንቁም!

2 years ago | [YT] | 2

ልደትዬ እናቴ

​​#ቃና_ዘገሊላ

በዛሬው ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከሐዋርያቱ ጋር የገሊላ ክፍል በሆነችው በቃና በሰርግ ቤት ተገኝቶ ውሃውን ወይን ጠጅ ያደረገበት ነው። ሰርግ ደግሶ የነበረው ዶኪማስ አዘጋጅቶት የነበረው ወይን ጠጅ አልቆ በተጨነቀ ጊዜ ችግሩን ቀርቦ ሳይነግራት ማለቁን አውቃ ልጄ ሆይ ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል በማለት ተናግራ ውሃው ወደ ወይን ጠጅ እንዲለወጥ የማማለድ ተግባር የፈጸመችበት ዕለት ነው።

አምላካችን ጋብቻ ክቡር መሆኑን ዓለም እንዲረዳ ያደረገበት፣ ሰዎች ያዘጋጁት ነገር ተንጠፍጥፎ አልቆ በተጨነቁ ጊዜ እመቤታችን ለልጇ አሳስባ ጎደሏቸው እንዲሞላ ፣ጭንቀታቸው እንዲወገድ የምታደርግበት በዓል ነው።

ጥንቱ ዕለቱ የካቲት 23 ቀን ቢሆንም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የውሃን በዓል ከውሃ በዓል ጋር ማክበር ይገባል ብለው የሚጠጡት አልቆባቸው ተጨንቀው የነበሩበት ቃና ዘገሊላ የውሃ በዓል በመሆኑ ከውሃ በዓል ከሆነውና የእዳ ደብዳቤያችን ከተደመሰሰበት ከጥምቀት ጋር እንዲከበር በማድረጋቸው በዛሬው ዕለት እናከብረዋለን።

ዛሬ የዶኪማስ ጭንቀት ብቻ ሳይሆን በጋብቻ ምክንያት የሚከሠት የክርስቲያኖች ሁሉ ጭንቀት የተቃለልበት ዕለት ነው። እመቤታችን ዶኪማስ ሳይለምናት ጭንቀቱን እንዳቃለለችለት ለልጅሽ አሳስቢልን ብለን ብንማጸናት የማይፈጸምልን ነገር፣ የማይወገድልን ጭንቀት አለመሆኑን የተረዳበት ዕለት ነው። በዓሉን ማክበር የሚገባንም ይህን እያሰብን ነው። አምላካችን ከበዓሉ በረከት ይክፈለን።

2 years ago | [YT] | 2

ልደትዬ እናቴ

✞ እንኩዋን ለጽዮን "ማርያም ማሕደረ አምላክ" እና ለቅዱሳኑ "ጐርጐርዮስ ወዮሐንስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞


🕊   †   ጽዮን ማርያም   †   🕊

"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል::

እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር: ሞገስ: አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል:: [ዘጸ.፴፩፥፲፰] ከዚያም ለ፭ መቶዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች::

ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ: በቀዳማዊ ምኒልክ [እብነ መለክ-እብነ ሐኪም] አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች:: እነሆ በሃገራችን የ፫ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው:: ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን::

ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን:: ግን አንጨነቅም:: ምክንያቱም የመጣችውም: የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም:: በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም:: ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም::

ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን: ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች:: "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው:: "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው::

"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው:: ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል:: ጽላት [ታቦትን] ያመጣ ፈጣሪ ነው:: በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም ፪ ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን:: [፪ቆሮ.፮፥፲፮ , ራዕይ.፲፩፥፲፱]

በመጨረሻም ኅዳር ፳፩ [ 21 ] ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን:: በዚህች ቀን :-

፩. ታቦተ ጽዮን [ጽላተ ኪዳን] ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን:: ይሕ ሲሆንም ቅዱስ ሙሴ ፵ መዓልት: ፵ ሌሊት ጾሞ እንደ ተቀበለ ሳንዘነጋ ማለት ነው:: [ዘጸ.፴፩፥፲፰ , ዘዳ.፱፥፲፱]

፪. በዘመነ ኤሊ ሊቀ ካህናት ታቦተ ጽዮን በታሪኩዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ [ኢሎፍላውያን] እጅ ተማርካለች:: ግን ደግሞ ዳጐንን ቀጥቅጣዋለች:: [፩ሳሙ.፭፥፩]

፫. በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና: ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ: አገለገለ:: ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ ተቀኘላት:: በዚህም ሜልኮል ንቃው ማሕጸኗ ተዘግቷል:: [፩ዜና.፲፭፥፳፭] ሊቃውንትም "ድንግል እመቤታችን ማርያም በትንቢት መነጽር ተመልክቷል" ብለውናል::

"ሰላም ለኪ ማርያም እምነ::
ዘሰመይናኪ ጸወነ::
ሶበ እምርሑቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ::
ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየኀይድ ዓይነ::
ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ::" እንዲል:: [አርኬ ዘኅዳር ፳፩]

፬. በዘመነ ንጉሥ ሰሎሞን [መፍቀሬ ጥበብ] ግሩም የሆነ ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት ስትገባ ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: እግዚአብሔርም በደመና ወርዶ ንጉሡን አነጋግሯል:: [፪ዜና.፭፥፩ , ፩ነገ.፰፥፩]

፭. በዚያው ዘመንም በፈጣሪ ፈቃድ ንጉሥ ምኒልክ ቀዳማዊ [ዕብነ ሐኪም] ታቦተ ጽዮንን ይዞ ወደ ኢትዮዽያ ገብቷል::

፮. በዘመነ አፄ ባዜን [በ፬ ዓ/ም አካባቢ] አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች:: በዚህ ጊዜም ፪ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታል::

፯. በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመንም ነገሥት ጻድቃን አብርሐ ወአጽብሐ ፲፪ መቅደሶች ያሏትን ግሩም ቤተ ክርስቲያን ለእመ ብርሃን ሠርተው በዚሁ ቀን በጌታችን ተቀድሷል::

፰. በተጨማሪም በየጊዜው: ማለትም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ ወደ ዝዋይ ትሰደድ ነበር:: ተመልሳ ስትታነጽም ቅዳሴ ቤቷ የሚከበረው ኅዳር ፳፩ ቀን ነው:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህ በዓል ልዩ ነው::

" አማናዊት ጽዮን እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን እንዲህ እንላታለን "

"ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ "ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን" ናትና::

ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና::

እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው::

፩. "ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ቅዱሳን ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት::

"ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: [ተአምረ ማርያም]

፪. "ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በሁዋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና::

- "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: [ቅዱስ ያሬድ]
- ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: [መጽሐፈ ቅዳሴ]

፫. ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና::

፬. እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን [ሐሊበ ድንግልናዌን] ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና::


🕊  †   ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘሮም  †   🕊

በቤተ ክርስቲያን እጅግ ስመ ጥር ከሆኑት ሊቃውንት አንዱ ሲሆን ብዙ ጊዜ የሚታወቀው "ገባሬ መንክራት" በሚለው ስሙ ነው:: ገባሬ መንክራት የተባለውም እጅግ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በመሥራቱ ነው::

በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር ተወልዶ ያደገው ቅዱስ ጐርጐርዮስ ከመመነኑ በፊት ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል:: እርሱ በበርሃ እያለም ከሮም ዻዻሳት የአንዱ በማረፉ ተሿሚ ፍለጋ አበው ሱባኤ ገቡ:: እግዚአብሔርም "የበረሃውን ጐርጐርዮስን ፈልጉት" አላቸው::

"እሺ!" ብለው ፍለጋ በርሃ ቢሔዱ ውዳሴ ከንቱን ይጠላልና ተሰወረባቸው:: እነርሱም እያዘኑ ተመልሰው በመንበረ ዽዽስናው ላይ ወንጌልን አኖሩና ተለያዩ:: በዚህ ጊዜ ቅዱስ መልአክ ወርዶ "ጐርጐርዮስ ሆይ! ልትሔድ ይገባሃል" አለው::

3 years ago | [YT] | 0

ልደትዬ እናቴ

💚💛❤️ ኅዳር ፮ ደብረ ቊስቋም #እንኳን #አደረሳችሁ

#እመቤታችን_ከልጇ_ጋር_ስደትን_የጀመረችበት_ዕለት_ነው፡፡

🌹 ድንግል ማርያም ከልጇና ከአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ጋርለ3 ዓመታት ከ6 ወራት (ወይም ለ42 ወራት) (1275 ቀናት) ከተሰደደች በኋላ 🌹 ግንቦት_24_ደግሞ_በዓተ_ግብጽ_ (ወደ ግብጽ ወደ ደብረ ቊስቊም ገብታ ያረፈችበት ቀን ነው፡፡
ዖፍኒ ረከበት ላቲ ቤተ፤ ወፍም ቤቷን ሰራች፡፡ መዝ. ፹፫፥፫
ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማው ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አንድ አምላክ ልጇን አዝላ፤ በአንዲት አህያ ላይ ተቀምጣ፤ ጥቂት ስንቅ ቋጥራ፤ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች፡፡ ከገሊላ ተነሥታ በጭንቅ፣ በመከራ፣ በረሃብና በጥም፣ በሐዘንና በድካም፣ በእንባ ተጕዛ በዚህች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታ በሥደት እጅግ ብዙ መከራ ተቀብላለች::
† የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
† ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
† የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
† የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
† የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
† እመ አምላክ ተራበች፣ ተጠማች፣ ታረዘች፣ ደከመች፣አዘነች፣ አለቀሰች፣ እግሯ ደማ፣ ተንገላታች::
ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኳን ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ:: አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና::
#መድኃኔ_ዓለም_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ለምን_ተሰደደ? #ለምን_ስደቱን_ወደ_ግብፅና_ኢትዮዽያ_አደረገ?
1. ፠ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና(ኢሳ 19፥1፣ ዕን. 3፥7)
2. ፠ምሳሌውን ለመፈጸም፤ የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም፥ ያዕቆብ (እሥራኤል):፥ ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::
3. ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19፥1)
4. የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::
5. ሰው መሆኑ በአማን (በእውነት) እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: (ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበር:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና::
6. ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና
7. የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::
እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት (ወይም ለ42 ወራት) (1275 ቀናት) በስደት የቆየችባቸው ቦታዎች አሉ::
፠ በመጀመርያ ድንግል ማርያም ከርጕም ሔሮድስ ስትሸሽ መጀመሪያ የሔደችው ከገሊላ ወደ ሶርያ ደንበር (ደብረ ሊባኖስ) ነበር:: በዚያም የሸሸጋት ቅዱስ ጊጋር መስፍኑ በሔሮድስ ሲገደል ወደ ምድረ ግብጽ ወረደች፡፡
፠ በግብጽም ለብዙ ጊዜ ከአንዱ ወደ ሌላው ስትሸሽ ቆየች:: ‹‹እንዘ ከመ በግዕት ግድፍት አመ ሳኮይኪ ውስተ ምድረ በዳ፡፡›› እንዲል:: (እሴብሕ ጸጋኪ)
፠ ቀጥላም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ገብታ ደብረ ቢዘን ላይ (አሁን ኤርትራ ውስጥ ነው) ዐረፈች፤
፠ ከደብረ ቢዘን ደብረ ሐዊ፣ በደብረ ዳሞ፣ አኵሱም፣ ደብር ዐባይ፣ ዋልድባ አድርጋ እየባረከች ቆይታለች፤
፠ በዋልባም ቆይታቸው ልጇ ገዳሙን በኢትዮጵያ በብጨኝነት ራሱ የገደመውን ገዳም መሥርቶ እየባረከ ወደ ጣና ሄደዋል፡፡
፠ በጣና ገዳማትም፤ በተለይ በጣና ቂርቆስ ለ100 ቀናት ቆይታ ቀጥታ በጐጃም ወደ ሸዋ ሔዳ ደብረ ሊባኖስን ቀድሳለች::
፠ ቀጥላም እስከ ደብረ ወገግና ደብረ ሐዘሎ ደርሳለች፤ በእግሯ ያልደረሰችባቸውን የሀገራችን ክፍሎች በደመና ተጭና ዐይታ ባርካቸዋለች፡፡
፠ በደብረ ኤረር ተራራ ላይም ከልጇ ኢትዮጵያን በዐሥራትነት ተቀብላለች፡፡
ሔሮድስ መሞቱን መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የነገራትም እዚሁ ኢትደዮዽያ ውስጥ መሆኑን ትውፊት ያሳያል::
እመቤታችን የሄሮድስን ሞት ከሰማች በኋላ ቊስቋም ከሚባል ተራራ ላይ ሆና ደስታዋን አብረዋት መከራን ከተቀበሉት ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር አከበረች፡፡ ከሃገራችን ሰዎች (ከሰብአ ኦፌር) የተቀበለችውን ስንቅና ስጦታ በ5 ግመሎች ጭና ከቅዱሳኑ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ኅዳር 6 ቀን ቊስቋም ውስጥ ገብተው ከድካም ዐርፈዋል፤ ሐሴትንም አድርገዋል::
#ግብጽ_ደብረ_ቊስቋም_
ከክርስቶስ ስደት 400 ዓመታት በኋላ በዚህች ቀን የግብጿ ደብረ ቊስቋም ታንጻ ተቀድሳለች፤ የቅዱሳን ማደሪያም ሆናለች፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፤ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ390ዎቹ አካባቢ ድንግል እናቱን፣ ቅዱሳን ሐዋርያትን፣ አእላፍ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን፣ አስከትሎ ወረደ፡፡ የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ቤተ ክርስቲያኑን አንጸው፤ ሕዝቡን ሰብስበው ይጠብቁት ነበርና ወርዶ ቀድሶላቸው ታላቅ ደስታ ኾኗል::
ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ፤ የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ ኅዳር 6 ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና:: ‹‹አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ፤ ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ›› ልንልም ይገባል፡፡

3 years ago | [YT] | 0

ልደትዬ እናቴ

አድዋ የእሳት ልሣን

የጀግናዎች የወኔ ቅስም
የጨቋኞች የውርደት ስም
የጭቆና አርካሽ መድኅን
የባርነት ቁስል እንዲድን
አድዋ የነፃነት አፍ!
የሰውነት ልኬት አጥናፍ!!..

#አድዋ_የእሳት_ልሣን.
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
📚የፍቅ ቀን 📚
📖📖📖📖📖📖
🌷 #መልካም_ውሎ 🌷

✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯

4 years ago | [YT] | 6

ልደትዬ እናቴ

✟እንኳን አደረሳችኹ✟

🌿💖 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ኪዳነምሕረት ዓመታዊ ክብረ በዓል (ቃልኪዳን ለተቀበለችበት) በሰላምና በጤና አደረሳችኹ፡፡ 🌿💖

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

"ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ፤
ፈለገ እሳት ወደይን እምአስጠመ ኵሎ"
(ድንግል ኾይ ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የሲዖል እሳት ባሰጠመን
ነበር፡፡)

ድንግል ማርያም ሲዖልን ካየች በኋላ ስለኃጥኣን እጅግ እያዘነች ኖረች። የካቲት አሥራ ስድስት ቀንም በጎልጎታ ቦታ ቆማ ወደ ልጇ እንዲኽ ብላ ለመነች፡፡

"ጸሎትና ልመናዬን ስማኝ ቃሌንም አድምጥ!
እኔ እናትኽ አገልጋይኽ የምለምንኽ ይኽን ነው፡፡
👉 መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ፣
አብያተ ክርስቲያኔን ለሚሠሩ፣ ወይም ለታረዙ ለሚያለብሱ፣
ለተራቡ ለሚያጠግቡ፣ የተጠማውንም የሚያጠጡ (በስሜ ለድኆችና ለችግረኞች ቀዝቃዛ ውኃ ለሚሰጡ)፣ የታመመውንም የሚጎበኝ፣ ያዘነውንም የሚያረጋጉ፣ የተከዘውንም ደስ የሚያሰኙ
ወይም ምስጋናዬን ለሚጽፉ፣ ልጆቹንም በስሜ ለሚሰይም፣
በበዓሌም ቀን በማኅሌት ለሚያመሰግን አቤቱ በዓይን
ያልታየውን በጆሮ ያልተሰማውን በጎ ዋጋ ስጣቸው፡፡ 🙏
በአማላጅነቴም የሚተማመኑትን ኹሉ ከሲዖል 🔥 ነፃ አድርጋቸው
ከአንተ ጋር የደረሰብኝን ረኃብና ጥማቱን መከራውን ኹሉ አስብ!"

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም
👉 "እንዳልሽው ይኹንልሽ
የሰጠኹሽን ቃልኪዳን እንዳይታበይ በራሴ በባሕርይ አባቴ በአብ በባሕርይ ሕይወቴ በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ" ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣት፡፡

✟የእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ረድኤት በረከቷ ይደርብን✟ አሜን👏👏

🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

4 years ago | [YT] | 9