"እንኳን ወደ 'አማርኛ ዳዕዋ' የዩቲዩብ ቻናል በሰላም መጣችሁ! በዚህ ቻናል ላይ ስለ እስልምና እምነት ትክክለኛ ግንዛቤን የሚያሰጡ ዳዕዋዎችን፣ ትምህርቶችን፣ እና ምክሮችን በአማርኛ ቋንቋ እናቀርባለን። የቁርአንን ትርጉም፣ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች፣ የእስልምና ታሪክ፣ እና ዘመናዊ የእስልምና ጉዳዮችን በግልጽ እና በቀላሉ በሚገባ መንገድ እናቀርባለን። አላማችን የእስልምናን ውበት እና እሴቶች ለሁሉም ማድረስ፣ እና ለሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲሁም ለሌሎችም ጠቃሚ ይዘቶችን ማቅረብ ነው። ጥያቄዎችን ለመጠየቅ እና ሃሳቦችን ለመለዋወጥ ክፍት ነን። ለተጨማሪ ትምህርቶች ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰባችንን ይቀላቀሉ። ጀዛከላሁ ኸይር!"

"In this YouTube channel, we will learn about the teachings, stories, and values of the Islamic faith. We will present the Quran, Hadith, stories of the Prophets, and various Islamic topics in the Amharic language. Our goal is to promote a true understanding of Islam and provide valuable content to our Muslim brothers and sisters, as well as others. Subscribe to join our family for more educational content. Jazak Allah Khair!"
#QuranRecitation
#SurahMaryam
#DrMisbahSani
#EthiopianQuranReciter
#BeautifulQuran
#Tilawat
#IslamicContent
#QuranTilawat
#EmotionalRecitation
#QuranAfrica



AMHARIC DAWA

3 months ago | [YT] | 79

AMHARIC DAWA

እውነተኝነት የእውነተኛ ኢማን ምልክት ነው! !!

3 months ago | [YT] | 58

AMHARIC DAWA

ፈጅርን የወደደ...
አላህ ይበልጥ ይወደዋል !!

3 months ago | [YT] | 129

AMHARIC DAWA

قُل لَّوْ كَانَ الْبَحْرُ مِدَادًا لِّكَلِمَاتِ رَبِّي لَنَفِدَ الْبَحْرُ قَبْلَ أَن تَنفَدَ كَلِمَاتُ رَبِّي وَلَوْ جِئْنَا بِمِثْلِهِ مَدَدًا

«ባሕሩ ለጌታዬ ቃላት (መጻፊያ) ቀለሞችን በሆነ ኖሮ ብጤውን ጭማሪ ብናመጣም እንኳን የጌታዬ ቃላት ከማለቋ በፊት ባሕሩ ባለቀ ነበር» በላቸው፡፡(ሱረቱል ካህፍ 109)

ጌታችን ሆይ በቃልህ የምንፀና፣
በቃልህ የምንታከም ፣ የልባችን ሸክም የሚጠፋበት፣ ኸይር ከተፃፈላቸው ባሮችህ አድርገን


❤️❤️❤️اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين ❤️❤️❤️

በጌታችን ቃል የምንደምቅበት ኸይር የተባለን በሙሉ የምናገኝበት ለመልካም የምንሽቀዳደምበት ፣ በዛች በሩቋ ሀገር ያሉትም ከአላህ የሆነ ራህመት የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣ ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት፣ በሰለዋት፣ በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ እና የፈካ ጁምዓ ይሁንልን💚💚💚

4 months ago | [YT] | 75

AMHARIC DAWA

#ኢድ_ጁመዓ ላይ ከዋለ … #ጁመዓ ሰላት እንዴት ይደረግ ብዙ ሰዎች ግራ ይጋባሉ 🤔

ቀላል ማብራሪያ 👇

ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡- “በዚህ ቀን ሁለት ኢዶች ከተገጣጠሙ። የፈለገ ሁሉ የጁመዓ ሰላትን ከመስገድ ይልቅ የዒድ ሰላት ይበቃዋል፣ እኛ ግን የጁመዓ ሰላትን እንሰግዳለን።” በአቡ ዳውድ (1073) እና ኢብኑ ማጃህ (1311) እና በአል-አልባኒ የተረጋገጡ።

በሌላ ሐዲስ፡- “የዒድ ሰላትን የሰገደ ማንኛውም ሰው የጁመኣ ሰላትን የመስገድ ግዴታ የለበትም።” በአቡ ዳውድ (1070) እና በአል-አልባኒ የተረጋገጠ።

ታዲያ ከዚህ ምን እንረዳለን? ‼️🤔

የዒድ ሰላትን የምትሰግድ ከሆነ 🎉
✔ ወደ ጁመዓ ሰላት ✔ አለመሄድ ተፈቅዶልሃል፣ ነገር ግን በምትኩ #ዙህርን መስገድ አለብህ‼

ሆኖም፣ የዒድ ሰላት የማትሰግድ ከሆነ፡ እንደተለመደው ሄደህ #የጁመዓ_ሰላትን መስገድ አለብህ‼

ታዲያ ኢማሙ ምን ማድረግ አለበት?

የጁመዓ ሰላት ለመገኘት ለሚፈልጉ የጁመዓ ሰላትን መምራት አለበት (ነቢዩ ﷺ እንደተናገሩት፡- “ እኛ ግን የጁመዓ ሰላት እንሰግዳለን”)። ብለዋል

እና የትኛውን እንምረጥ? ♥

#የዒድን እና #የጁመአ ሰላትን #ሰግደህ #እጥፍ_ምንዳ ብታገኝ አይሻልም‼

ዲናችን ገር ነው… ነገር ግን ሱናን መከተል አለብን 👌 ስለዚህ ሁልጊዜ ማስረጃዎችን መመሪያችን እናድርግ

ኢድኩም ሙባረክ ተቀበለላህ ሚና ወሚንኩም ሷሊሃል አዕማል♥

4 months ago | [YT] | 31

AMHARIC DAWA

🌙⭐️ عيد مبارك 🌙⭐️
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال 🤲✨

🌷 كل عام وأنتم بخير، أعاده الله عليكم بالخير واليمن والبركات 🌷

አላህ መልካም ሥራችንን ይቀበል፣ ይቅር ይበለን፣ ከእሳት ነፃ ከሚሆኑ ሙእሚኖች ያድርገን 🤲🌷 አሚን

🕋🕌⭐️🌙 Eid Mubarak 🌙⭐️🕌🕋
May Allah fill your days with happiness, your heart with peace, and your life with barakah. ✨🎉

4 months ago | [YT] | 41

AMHARIC DAWA

የ ኢድ ሶላት አሰጋገድ ...ለ ሁሉም እንዲደርስ ሸር አድርጉት
#ኢድ
#ኢድሶላት
#share

4 months ago | [YT] | 150

AMHARIC DAWA

ረመዳን 26

የረመዳን 27ተኛ ለሊት ለይለቱል ቀድር ይበልጥ የሚከጀልባት ለሊት

በለይለተል-ቀድር የሚሰራ ዒባዳ ከ1 ሺህ ወራቶች (83 ዓመት) ዒባዳ የሚበልጥ ሲሆን ከነቢዩ (ሰዓወ) ሰሀባዎች ውስጥ፥ ሰይዱና ዑመር(ረዓ)፣ ኢብኑ ዐባስ ፣ኡበይ ኢብኑ ከዕብ፣ ሙዓዊያ፣ ሁዘይፋና ሌሎችም( አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) ለይለተል-ቀድር 27 ሌሊት ላይ ናት ይሉ ነበር!

ይህች የረመዳን 27ተኛ ለሊት ዛሬ እሁድ ምሽት ላይ ናት፡:

የአላህ መልእክተኛ ﷺ ይህን ብለዋል

"ለይለተል ቀድርን በኢማንና ከአላህ አጅር በመፈለግ የቆመ ከዚህ በፊት የሰራው ወንጀል በሙሉ ይማርለታል። "

በዚህች ለሊት ሁላችንም ለዱኒያችንም ለአኼራችንም ዱዓ ልናደርግ፣ ለሀገራችንም ሆነ ለመላው አለም የሰው ልጆች ዱዓ የምናደርግበት ሊሆን ይገባል::

ለሊቱን በኢባዳ ማሳለፍ ፣ይበልጥ ወደ አላህ ተናንሰን መቃረብ እና ማሃርታውን መጠየቅ ፤ከአሳማማሚው የጀሀነም እሳትም እንዲታደገን ጌታችንን መማፀን አንዘንጋ

አላህ ለይለቱል ቀድርን ይወፍቀን

ወንጀላችንም ይማረን

4 months ago | [YT] | 228