ኬር ቲዩብ / kare tube



ኬር ቲዩብ / kare tube

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን
ኬር ቲዩብ በዓሉ የሰላም የአንድነት እንዲወንልን ከልብ ይመኛል 🙏🙏🙏

11 months ago | [YT] | 3

ኬር ቲዩብ / kare tube

አምላካችን እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ አውርዶ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል።( ኢያ)5:13
፡፡እንኳን ለሊቀ መላህክ ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ
ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳቹ።
ኬር ቲዩብ 🙏🙏🙏

1 year ago | [YT] | 1

ኬር ቲዩብ / kare tube

እንኳን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ዝክረ ጥንተ ስቅለት አደረሳችሁ አደረሰን

መጋቢት ፳፯  በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  የተሠቀለበት ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ቀን ነው ፡፡  ይሁን እንጂ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሣኤ በዓል በፊት ያለውን አርብ “ስቅለት” ተብሎ እንዲከበር ሥርአት ሠርተዋል፡፡መጋቢት ፳፯ ቀን በዓቢይ ጾም ስለሚውል በዓቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በዓል ማክበርም ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት ፳፯ ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተክርስቲያን ሥርዓት ሰርታለች ።
 

1 year ago | [YT] | 2

ኬር ቲዩብ / kare tube

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ። አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው።

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ፣ ልብስ ያልለበሱ (ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና) ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ፤ ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም የተቀበሉ አባት ናቸው።

ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ። በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም ለአእላፍ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል።

የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቀር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።

በ8ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው፤ ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው። ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላልና ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር እና ፍትሃ ነገስት

1 year ago (edited) | [YT] | 2