የድፍረት ሀጢያት እንዳይገዛኝ መንፈስ ቅዱስ ጠብቀኝ
wendmieneh
👉🌹🌹 ሰኔ ፳፮ [26] ቀን 🌹🌹†#እንኳን_ለታላቁ_ነቢይ_ቅዱስ_ኢያሱ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። †† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! † † #ቅዱስ_ኢያሱ_ነቢይ_ወመስፍን † † ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ "አውሴ" ይባላል:: ዘመኑ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ፪፻፲፭ [215] ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ ፹ [80] ዓመቱ : ኢያሱ ደግሞ ፵ [40] ዓመቱ ነበር::ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ፵ [40] ቀን የታሠበላቸውን መንገድ ፵ [40] ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም::አውሴን "ኢያሱ" ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው:: ኢያሱ ማለት "መድኃኒት" ማለት ነው:: ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:- ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል:: ምድረ ርስትን አውርሷል:: ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ [ጥላ] እንዲሆን ነው::ቅዱስ ኢያሱ በበርሃ ለ፵ [40] ዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዝዞታል [አገልግሎታል]:: እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአህብ እጅ አድኗቸዋል::በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ ደብረ ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን : ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው ፹ [80] እየሆነ ነበር::† እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን [አስተዳዳሪ] እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ:¤ ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ¤ ሕዝቡን አሻግሮ¤ የኢያሪኮን ቅጥር ፯ [ 7 ] ጊዜ ዙሮ¤ በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ¤ የኢያን ነገሥታት አጥፍቶ ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ::የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዚያን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል : በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚያች ዕለትም ለ፲፪ [12] ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም [በኤሎም ሸለቆ] አቆመ::ሰባት አሕጉራተ ምስካይ [የመማጸኛ ከተሞችን] ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ፵ [40] ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ አላቸው :-"እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: [ኢያ.፳፬] (24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ ፫ [3] ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ::ይህችውም የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ ፫ [3] ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ፫ [3] ወገን [በነፍስ: በሥጋ: በልቡና] ድንግል ናት:: አንድም በ፫ [3] ወገን [ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት] ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው አባ ሕርያቆስ "ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" [የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ] ሲል ያመሰገናት::ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ፹ [80] ዓመት: በተወለደ በ፻፳ [120] ዓመቱ [ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ፻፲ [110] ዓመቱ ይላል] በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ፴ [30] ቀናት አለቀሱለት::† በወዳጁ በኢያሱ እጅ የአሕብን ቅጥር ያፈረሰ እግዚአብሔር የእኛንም የኃጢአታችንን ግንብ በወዳጆቹ ምልጃ ያፍርስልን:: ከቅዱሱ ነቢይም በረከትን ያሳትፈን::† ሰኔ ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፩. ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን፪. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት [ቅዳሴ ቤቱ]† ወርሐዊ በዓላት፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ፪. አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ፫. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ፬. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን፭. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን† "አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ:: በእውነተኛም ልብ አምልኩት . . . እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ . . . የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ: የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን::" † [ኢያሱ.፳፬፥፲፬] (24:14)† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †† ወለወላዲቱ ድንግል †† ወለመስቀሉ ክብር † † † †
5 months ago | [YT] | 11
View 0 replies
👉✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞✞✞✞ ✝እንኩዋን ከዘመነ ጸደይ ወደ ዘመነ ክረምት መሸጋገሪያ ለሆነችው ዕለትና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞✝=>ስንዱ እመቤት ቤተ ክርስቲያን (ሃገራችን) ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች:: እሊሕም ዘመናት መጸው (ጽጌ): ሐጋይ (በጋ): ጸደይ (በልግ)ና ክረምት ናቸው:: ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል::+በተለይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና "ሽሽታችሁ (ስደታችሁ) በክረምትና በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ" ብሎናልና (ማቴ. 24:20) ልንጸልይ ይገባናል:: በዘመነ ክረምት ቅጠል እንጂ ፍሬ የለበትምና ፍሬ ምግባር ሣናፈራ ሞት እንዳይመጣ: አንድም ክረምት የዝናብና የጭቃ ጊዜ በመሆኑ እንኩዋንስ ለስደት ለኑሮም አይመችምና እንደ ሊቃውንት እንዲህ ብለን እንጸልይ:-"በዝንቱ ክረምት በመዋዕሊነ:እንበለ ፍሬ እንዘ በቆጽል ኀሎነ:ናስተበቁዐከ እግዚኦ ኢይኩን ጉያነ::"(ክረምት በተባለ በእኛ እድሜ:ፍሬ ሳናፈራ በቅጠል /ያለ መልካም ሥራ/ ሳለን:አቤቱ ጌታ ሆይ ስደትን አታምጣብን)=>ቸሩ አምላካችን ከዘመነ መጸው በሰላም ያድርሰን:: ተረፈ ዘመኑንም የንስሃ: የፍሬና የበረከት ያድርግልን::=>በዚሕች ዕለት እነዚህ ቅዱሳን ይከበራሉ:-+" ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ "++በዘመነ ሐዋርያት ይሁዳ ተብለው ይጠሩ ከነበሩት አንዱ የሆነው ቅዱሱ የአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ልጅ ሲሆን እናቱ ማርያም ትባል ነበር:: እናቱ ስትሞትበት ተጎድቶ የነበረ ቢሆንም ገና በልጅነቱ ድንግል ማርያም አግኝታው በፍጹም ጸጋ አሳድጋዋለች:: አስተዳደጉም ከጌታችን ጋር በአንድ ቤት ነበር::ጌታችን እርሱንና ወንድሞቹን (ያዕቆብና ስምዖንን) ከ72ቱ አርድእት ቆጥሯቸዋል:: ቅዱስ ይሁዳ ወንጌል ላይ ከጌታችን ጋር መነጋገሩን ዮሐንስ ወንጌላዊ መዝግቧል:: (ዮሐ. 14:22) +ቅዱስ ይሁዳ ከጌታችን እግር 3 ዓመት ተምሮ: መንፈስ ቅዱስንም ተቀብሎ ብዙ አሕጉራትን ዙሯል:: አይሁድንም አረማውያንንም ወደ ክርስቶስ ይመልስ ዘንድ ብዙ ድካምና ስቃይን በአኮቴት ተቀብሏል:: አንዲት አጭር (ባለ አንድ ምዕራፍ) መልእክትም ጽፏል:: አጭር ትምሰል እንጂ ምሥጢሯ እጅግ የሠፋ ነው:: ቅዱስ ይሁዳን በዚህች ቀን አረማውያን ገድለውት በሐዋርያነቱ ላይ የሰማዕትነትን ካባ ደርቧል::+" ቅዱሳን ዺላጦስና አብሮቅላ "+=>ብዙዎቻችን መስፍኑን ዺላጦስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን እንዳይሰቀል ከአይሁድ ጋር ሲከራከር እናውቀዋለን:: የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ ነበርና አይሁድ እንቢ ሲሉት የክርስቶስን ንጽሕና መስክሮ: እጁንም ታጥቦ ሰጥቷቸዋል:: የዺላጦስ ታሪክ ግን እዚህ ላይ አያበቃም::+ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ከተነሳ በሁዋላ ትንሳኤውን በራዕይ ገልጦለት አይሁድን ተከራክሯቸዋል:: ውሸታም ወታደሮችንም ቀጥቷል:: በመጨረሻ ግን በሮም ቄሳር ተጠርቶ ከእሥራኤል እስከ ሮም ድረስ ሰብኮ በሮም አደባባይ አንገቱ ተሠይፏል::+ቅድስት እናታችን አብሮቅላም የዺላጦስ ሚስት ስትሆን ቁጥሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ነው:: ጌታችንን ተከትላ: ቤቷን ለሐዋርያት አስረክባ: ቤተ ክርስቲያንንም በዘመኗ አገልግላ ዐርፏለች:: ዛሬ ሁለቱም ቅዱሳን ይታሠባሉ::=>ጌታችን ከሐዋርያው ይሁዳ: ከዺላጦስና አብሮቅላም ጸጋ በረከትን ያድለን::=>ሰኔ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=1.ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)2.ሰማዕቱ ዺላጦስ መስፍን3.ቅድስት አብሮቅላ (ሚስቱ)4.አባ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት5.የጸደይ መውጫ / የክረምትመግቢያ=>ወርሐዊ በዓላት1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ5.አቡነ አቢብ /አባ ቡላ/6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ=>+"+ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ: የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ በእግዚአብሔር አብ ተወደው: ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ:ምሕረትና ሰላም: ፍቅርም ይብዛላችሁ::ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩዋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ:: +"+ (ይሁዳ. 1:1)✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞
5 months ago | [YT] | 14
👉✞✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞❖ ✝እንኳን አደረሳችሁ ✝❖❖ ሰኔ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት+"+ ✝ቅዱስ_ሙሴ_ጸሊም (ጥቁሩ ሙሴ) ✝+"+=>ግብጻውያን ስማቸውን ጠርተው ከማይጠግቧቸውቅዱሳን መካከል አንዱ ኢትዮዽያዊው አባ ሙሴ ጸሊምነው:: በእኛኢትዮዽያውያን ግን ይቅርና በወርኀዊ በዓሉ (በ24)በዓመታዊ በዓሉ እንኩዋ ሲከበር ብዙም አይታይም::=>ቅዱሱ ሰው በትውልዱ ኢትዮዽያዊሲሆን ያደገውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ እንደሆነይታመናል:: ገና በወጣትነቱ አገር የሚያሸብር ሽፍታ ነበር::ሙሴ ጸሊምወደ ግብጽ የሔደበት ምክንያት በግልጽ ባይታወቅምመምለክያነ ጣዖት (ፀሐይን ከሚያመልኩ ሰዎች) ጋርይኖር ስለ ነበርምናልባት እነርሱ ወስደውት ሊሆን ይችላል::+ቅዱስ_ሙሴ በምድረ ግብጽም በኃይለኝነቱ ምክንያት የሚደፍረውአልነበረም:: ፀሐይን ያመልካል: እንደ ፈለገ ቀምቶይበላል: ያሻውንሰው ይደበድባል:: ነገር ግን በኅሊናው ስለ እውነተኛውአምላክ ይመራመር ነበርና አንድ ቀን ፀሐይን "አምላክከሆንሽአናግሪኝ?" አላት:: እርሷ ፍጡር ናትና ዝም አለችው::+ቅዱስ ሙሴ ምንም አስቸጋሪ ሰው ቢሆንም ፈጣሪንመፈለጉን ግን ቀጥሏልና አንድ ቀን ተሳካለት:: መልካምክርስቲያኖችንአግኝቶ . . . ወደ ገዳመ_አስቄጥስ ቢሔድ በዛ ያሉ መነኮሳት ወደ እውነት እንደሚመሩትነገሩት:: እርሱም ሰይፉን እንደታጠቀ ወደ ገዳም ገባ::መነኮሳቱፈርተውት ሲሸሹ ታላቁ አባ_ኤስድሮስ ግን ተቀብለው አሳረፉት::+"ምን ፈለግህ ልጄ?" አሉት:: "እውነተኛውን አምላክ ፊትለፊት ማየት እፈልጋለሁ" የሙሴ ጸሊም መልስ ነበር:: አባኤስድሮስም "የማዝህን ሁሉ ካደረግህ ታየዋለህ" ብለውወደ መነኮሳት አለቃ ቅዱስ_መቃርስ_ታላቁ ወሰዱት:: መቃሬም ክርስትናን አስተምረው አጠመቁትናለአባ ኤስድሮስ መለሱላቸው::+ከዚህ ሰዓት በሁዋላ ነበር የአባ ሙሴ ጸሊም ሕይወትፍጹም የተለወጠው:: በጻድቁ እጅ ምንኩስናን ተቀብሎይጋደልጀመር:: በጠባቧ በር ይገባ ዘንድ ወዷልና ያ በሽፍትነትየሞላ አካሉን በገድል አረገፈው:: ከቁመቱ በቀር ከአካሉአልተረፈለትም:: ወገቡን በአጭር ታጥቆ መነኮሳትንአገለገለ:: አጋንንት በቀደመ ሕይወቱ በሕልም: አንዳንዴምበአካልእየመጡ ይፈትኑት ነበር::+እንዳልቻሉት ሲረዱ ተሰብስበው መጥተው በእሳትአለንጋ ገርፈው አቆሳስለውት ሔዱ:: እርሱ ግን ታገሰ::በበርሃ ለሚኖሩአበው መነኮሳት ሁሉ ብርሃን በሆነ ሕይወቱ ሞገስ ሆነላቸው:: ለኃጥአን ደግሞ መጽናኛሆነ::<< በተራራ ላይ ያለች ሃገር ልትሠወር አይቻላትምና ስምአጠራሩ በመላው ዓለም ተሰማ:: ሁሉም "ሙሴ_ጸሊም ይል ጀመር ፡፡ >>+በየበርሃው ያሉ አበው ብቻ ሳይሆነ ዓለማውያንመኩዋንንት ሳይቀሩ ሊያዩት ይመኙ ነበር:: እርሱ ግንራሱን "አንተጥቁር ባሪያ ስለ ኃጢአትህ አልቅስ" እያለ ይገስጽ:ከውዳሴ ከንቱም ይርቅ ነበር:: ከቆይታ በኋላምበመነኮሳት ላይእረኛ (አበ ምኔት) ሆኖ ተሾመ:: እንደሚገባም አገለገለ::የበርካቶችን ሕይወት ጨው በሆነ ሕይወቱና ምክሩአጣፍጦ:ድርሳናትንም ደርሶ እያረጀ ሔደ::+ከቁመቱ መርዘም የጽሕሙ ነጭነትና አወራረዱን ያዩሁሉ ሲያዩት ያደንቁት ነበር:: በመጨረሻም በ375 ዓ/ምበርበረሮች(አሕዛብ) ገዳመ አስቄጥስን ሲያጠፉ ሌሎች መነኮሳትሸሹ:: እርሱ ግን አልሸሽም ብሎ ከ7 ደቀ መዛሙርቱ ጋርበዚሕችቀን ተሰይፎ በሰማዕትነት አልፏል::=>ቅዱስ ሙሴ ጸሊምን ለርስቱ ያበቃ ጌታ ለእኛም ዕድሜለንስሃ: ለዘመን ለፍስሃን አይንሳን:: ከበረከቱም ፈጣሪውያድለን::=>ሰኔ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=1.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮዽያዊ)2."7ቱ" ቅዱሳን መነኮሳት (ደቀ መዛሙርቱ)3.አባ ኤስድሮስ ታላቁ❖ወርኃዊ በዓላት1፡ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት 2፡ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ3፡ ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ4፡ ቅዱስ አጋቢጦስ5፡ ቅዱስ አብላርዮስ6፡ አቡነ ዘዮሐንስ ዘክብራን7፡ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ =>+"+ መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠናዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስሊፈልገውየማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎትበጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜወዳጆቹንናጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ "የጠፋውን በጌንአግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ" ይላቸዋል::እላችሁአለሁ:እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃንይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታይሆናል:: +"+ (ሉቃ. 15:3-7)<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
5 months ago | [YT] | 9
👉✞✞✝ የሰኔ 23 ✝✞✞✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞❖✝ እንኳን አደረሳችሁ✝ ❖❖ ✝ሰኔ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት+"+ ✝ቅዱስ_ሰሎሞን ንጉሠ እሥራኤል✝ +"+=>መፍቀሬ ጥበብ:¤ጠቢበ ጠቢባን:¤ንጉሠ እሥራኤል:¤ነቢየ ጽድቅ:¤መስተሣልም (ሰላማዊ) . . . እየተባለ የሚጠራውቅዱስ ሰሎሞን የታላቁ ነቢይና ንጉሥ ልበአምላክ ቅዱስ_ዳዊትና የቅድስት ቤርሳቤህ (ቤትስባ) ልጅ ነው:: ከ3ሺ ዓመታት በፊት የተወለደው ቅዱስሰሎሞን እስከ 12 ዓመቱ ድረስ በቤተ መንግሥት ከአባቱጋርአድጉዋል::+ቅዱስ ዳዊት 70 ዘመን በሞላው ጊዜ የአካሉንመድከም አይቶ አዶንያስ በጉልበት እነግሣለሁ ቢልምአልተሳካለትም::እግዚአብሔር ሰሎሞንን መርጧልና ገና በ12 ዓመቱነገሠ:: ልበ_አምላክ አባቱ ዳዊት ነፍሱ ከሥጋው ከመለየቷ በፊት መከረው::"ልጄ ሆይ! ልብህን ስጠኝ:: ፈጣሪህንም አምልክ"አለው::+ቅዱስ ሰሎሞን እንደ ነገሠ በገባዖን ለእግዚአብሔርመስዋዕትን አቀረበ:: ጌታም ተገልጾ "ምን ትፈልጋለህ?"አለው::ሰሎሞንም ልክ እንደ አባቱ ማስተዋልን: ልቡናን ለመነ::በዚህም ጌታ ደስ ስለተሰኘ "አልቦ እምቅድሜከ: ወአልቦእምድኅሬከ - ከአንተም በፊት: ከአንተም በኋላ እንዳንተያለ ጠቢብና ባለጠጋ ሰው የለም: አይኖርም" ብሎትተሠወረ::ቅዱስ ሰሎሞን ለ40 ዓመታት በእሥራኤል ላይ ነገሠ::+ግሩም በሆነ ፍትሑ: በልዩ ጥበቡ ዓለም ተገዛለት::እግዚአብሔር የመረጣት የእኛዋ ንግስተ_ሳባ /አዜብ/ማክዳም ትፈትነው ዘንድ ሒዳ ምኒልክን (እብነ_መለክን) ጸነሰች:: በኋላም ታቦተ_ጽዮንና ሥርዓተ ኦሪት መጣልን:: ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን ድንግል_ማርያም ከእነሱ ዘር እንደምትወለድ ነግሮት ነበርና ያበጀሁ መስሎትሴቶችን አብዝቶ ነበር::+ነገር ግን:-¤አንደኛ ሰው (ሥጋ ለባሽ) ነውና:¤ሁለተኛ ደግሞ ከብዙ ሴቶች መካከልከአንዷ እመ_ብርሃን ትገኛለች መስሎት ነበር:: ነገሩ መንገድ ስቶበት ከአሕዛብ(ከፈርዖን ልጅ) ጋር በመወዳጀቱ ለጣዖት አሰገደችው::እግዚአብሔር እጅግ አዘነ::+በራዕይ ተገልጦ "ስለ ወዳጄ ስለ ዳዊት ስል በአንተ ላይ ክፉን አላደርግም" አለው:: ታላቁ ነቢይሰሎሞን ይህንን ሲሰማ ወደ ልቡ ተመለሰ:: ማቅ ለብሶ:አመድነስንሶ በፍጹም ልቡ አለቀሰ:: ንስሃ ገባ:: መፍቀሬ ንስሃጌታችንም ንስሃውን ተቀበለው::+የይቅርታው መገለጫም ተወዳዳሪ የሌላቸውን 5መጻሕፍት ገለጠለት:: ተናገራቸው:: ጻፋቸው:: እሊሕም:-1.መጽሐፈ ጥበብ2.መጽሐፈ ተግሣጽ3.መጽሐፈ መክብብ4.መጽሐፈ ምሳሌ5.መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ናቸው::+ቅዱስ ሰሎሞን ልዩ የሆነውን ቤተ_መቅደስ በመስራቱም ይደነቃል:: ደጉ ንጉሥ: ጠቢብና ነቢይሰሎሞን በዚህች ዕለት በ52 ዓመቱ ዐርፎ ወደ ፈጣሪውሔዷል::+"+ አባ_ኖብ +"+=>ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ሰማዕት አባ ኖብ አርፏል::በዚሕ ስም የሚጠሩ ብዙ ቅዱሳን ቢኖሩም ዋናው ይኼውቅዱስነው::+አባ ኖብ እንደ ገዳማውያን በበርሃ የተጋደለ: እንደሊቃውንት መጻሕፍትን ያመሰጠረ: በተለይ ደግሞ በዘመነሰማዕታትጭንቅ ጭንቅ መከራዎችን የተቀበለ አባት ነው:: ስለገድሉ ብዛት "ኃያል ሰማዕት": አንገቱን ስላልተቆረጠም"ሰማዕትዘእንበለ ደም" ይባላል:: ዘመነ ሰማዕታትን ካለፉ 72ቱከዋክብትም አንዱ ነው::=>ከመፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን: ከኃያሉ ሰማዕት አባኖብ በረከትን አምላካችን ይክፈለን::=>ሰኔ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=1.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)2.ቅዱስ አባ ኖብ (ሰማዕት ወጻድቅ)3.ቅዱሳን መርቆሬዎስ: ፊልዾስና ቶማስ (ሰማዕታት)❖ወርኃዊ በዓላት1፡ ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ 2፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት 3፡ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ 4፡ አባ ሳሙኤል 5፡ አባ ስምዖን 6፡ አባ ገብርኤል 7፡ ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ=>+"+ የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራትፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታትሳይደርሱ:ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርምወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደእግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ::ሰባኪው:- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል:: +"+(መክ. 12:1-9)<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
👉†††✝ እንኳን ለቅዱሱ አባታችን የዋህ ዻውሊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። ††††††✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††††† ✝ቅዱስ ዻውሎስ የዋህ ✝†††††† በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ግብፅ ውስጥ ተወልዶ ያደገው ቅዱሱ ስሙ ዻውሎስ ቢሆንም ብዙ ጊዜ የሚጠራው "የዋህ ዻውሊ" በሚል ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-የዋህ ዻውሊ ከሕጻንነቱ ጀምሮ መጻሕፍትን የተማረ: ግን ደግሞ ትዕቢት: ቁጣና ቂምን የማያውቅ ገራገር ሰው ነው:: እድሜው ለአካለ መጠን ሲደርስ ቤተሰቦቹ ሚስት አግባ አሉት:: እርሱ ባያስብበትም ወገኖቹን ላለማሳዘን አገባ:: እንዳለመታደል ሆኖ ግን ያገባት ሴት በጣም ቆንጆ በዚያም ላይ ክፉ ነበረች:: የዋህ ዻውሊ ክፋቷን ሁሉ ታግሶ ለበርካታ ዓመታት አብሮ ኖረ:: ልጆችንም አፈሩ::አሁንም ግን እርሷ ከክፋቷ ልትታገስ አልቻለችም:: ይባስ ብሎ ዻውሊ በሌለበት ከሌሎች ወንዶች ጋር ትዘሙት ያዘች:: የዋሁ ሰው ይሕንኑ ያውቃል ግን የእግዚአብሔርን ሥራ ዝም ብሎ በተስፋ ይጠብቅ ነበር:: ለነገሩስ እሱ ያርሳል: ይቆፍራል: ነዳያንን ያበላል: እንግዳ ይቀበላል እንጂ ክፋትን ለማሰብ ጊዜ አልነበረውም::አንድ ቀን ግን ለሥራ ወደ በርሃ ወጥቶ አንድ ግሩም ዜና ሰማ:: "አባ እንጦንስ ምንኩስና የሚባል ሕይወተ መላእክትን ጀምሯል: ደቀ መዛሙርትንም ይቀበላል" አሉት:: ግን ሚስትና ልጆች አሉትና ምን ያደርጋል?የዋህ ዻውሊ ሙሉ ቀን ሢሠራ ውሎ ወደ ቤቱ ሲመለስ ግን የጠበቀው ሌላ ነው:: ሚስቱ በራሱ መኝታ ላይ ከአገልጋይ እረኛው ጋር ራቁታቸውን አገኛቸው:: ልብ በሉልኝ በትክሻው ሞፈርና ምሳር: መጥረቢያም ይዟል:: እርሱ ግን ክፉን አላሰበም:: ጥሩ ልብስ አንስቶ ሁለቱንም አለበሳቸው::እንዲሕም አላቸው:- "ከዚሕ በሁዋላ እኔ አልመለስም:: ሀብት ንብረቴን ውረሱ: በደስታም ኑሩ:: የልጆቼን ነገር ግን አደራ" ብሏቸው ተነሳ::በእጁ ምንም አልያዘም:: በትከሻው ያለችውን ብጣሽ ጨርቅ ይዞ ወደ በርሀ ተጉዋዘ:: አባ እንጦንስም ተቀብለው አስተምረው አመነኮሱት:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ራስን ዝቅ በማድረግ: በመታዘዝ አገለገለ:: ጾም: ጸሎትና ስግደቱንማ ማን ቆጥሮት::እያለ እያለ ከብቅዐት ማዕርግ ደረሰ:: ምዕመናንም ሆነ መነኮሳት ሊጠይቁት ሲመጡ የእያንዳንዱ ኃጢአት በግንባራቸው ተጽፎ ይመለከት ነበርና ስለነሱ ሲያለቅስ ቅንድቡ ተላጠ:: ሰውነቱም አለቀ:: አንድ ቀን ጋኔን የያዘውን ሰው ፈውስ ብለው አመጡለት:: እርሱ ግን በአጋንንት ላይ ሥልጣን እያለው በትሕትና ተጠግቶ ጋኔኑን "አባ እንጦንስን ከምጠራብህ ቀስ ብለህ ውጣ" አለው:: ጋኔኑ ግን የፈራው መስሎት በትዕቢት "እንጦንስ ማነው?"አለው::ያን ጊዜ የዋህ ዻውሊ እንደ እሳት ከጋለ ድንጋይ ላይ ቁሞ "ሕያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው:: ይሕ ጋኔን ካልወጣ አልወርድም" አለ:: ወዲያው በዘንዶ አምሳል ከሴትዮዋ ወጥቶ እየጮኸ ወደ ቀይ ባሕር ገባ::ቅዱስ ዻውሊ የዋሕም እንዲሕ በቅድስና ተመላልሶ በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፏል::" የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር: ደስታ: ሰላም: ትእግስት: ቸርነት: በጐነት: እምነት: የውሃት: ራስን መግዛት ነው:: እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም:: የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ::" (ገላ. 5:22)††† ሰኔ 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=1.ቅዱስ አባ ዻውሊ የዋሕ2.ቅዱሳን ወክቡራን ቆዝሞስና ድምያኖስ (ሰማዕታት)3.ቅድስት ቴዎዳዳ ሰማዕት (እናታቸው)4.አንቲቆስ: ዮንዲኖስና አብራንዮስ (ሰማዕታት)††† ወርኀዊ በዓላት1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)4.አባ እንጦንዮስ (አበ መነኮሳት)††† አምላካችን ከቅዱስ ዻውሊ የውሃትን: ትእግስትን: በጐነትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን:: አሜን:: †††††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
5 months ago | [YT] | 13
#✞✞✞✝🌹 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✝🌹✞✞✞❖✝🌹 እንኳን አደረሳችሁ ✝🌹❖❖✝🌹 ሰኔ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት✝🌹=>ትናንት ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንናመድኃኒታችን ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ ሐዋርያት ወረደ:: ፊልዽስዩስ በምትባል ሃገር በዼጥሮስ እጅየመጀመሪያዋን ቤተ_ክርስቲያን አነጸ ብለን ነበር:: በዚህች ዕለት ደግሞ አእላፍመላዕክትን: ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስትድንግልማርያምን ይዟት ወረደ::+ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችንከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ:-1.አስቀድሞ ቤተ ክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮሥርዓተ ቤተ ክርረስቲያንን አሳየ::2.ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ_ዼጥሮስን ከመካከል አቁሞ "አርሳይሮስ" ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት(ፓትርያርክ) ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት"አክዮስ" እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: አክዮስ ማለት በግዕዙ"ይደልዎ": በዐማርኛው ደግሞ "ይገባዋል: ያሥምርለት"እንደማለት ነው::+ጌታችን ይሕን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ::¤አማናዊት ማሕደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ:¤ቅዱስ ዼጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ:¤ቅዱስ_እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ሆኖ:¤ሐዋርያት ድንግልን ከበው:¤መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቁመው ጌታችን ቀድሶቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ::+በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገርየማይችል ደስታ ተደረገ:: ከቅዳሴ በኋላ ጌታችንሐዋርያትንአዘዛቸው::"ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስምአብያተ ክርስቲያናትን እነጹ:: ይህችን ዕለት የሚያከብራትንአከብረዋለሁ::" ብሏቸው ከድንግል እናቱ ከመላዕክቱ ጋርዐረገ::+"+ ሰኔ_ጐልጐታ +"+=>ዳግመኛ በዚህ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስይታሰባል::ይኸውም ከሕንድ አውራጃዎች በአንዱ ወንጌልን ሰብኮእኩሎቹ ሲያምኑ እኩሎቹ እንቢ አሉ:: ቅዱስ ቶማስምያመኑትን"ከጣዖት አምልኮና ከዝሙት ሸሹ" ብሎ መከራቸው::+ምክሩን ከሰሙት አንዱ በዚያው ምሽት ሊጠጣ ወደመሸታ ቤት ይገባል:: ሰው ሁሉ ከወጣ በኋላ ባለመሸተኛዋ ሴትእንደለመደችው አብረው እንዲተኙ ስትጠይቀው "እንዴትሐዋርያው ከዝሙት ሽሹ እያለ እንዲህ ትይኛለሽ?" በሚልሰይፍአውጥቶ አንገቷን ቆረጣት::+እርሱ መልካም ያደረገ መስሎታል:: የሠራው ሥራ(መግደሉ) ግን አሕዛባዊ ግብር ነው:: በማግስቱ ቅዱስቶማስ ነገሩንሰምቶ ሰዎችን ሰበሰበና "ይህንን የአውሬ ድርጊት የፈጸመማነው?" ሲል ጠየቀ:: ፈጻሚው ግን አልታወቅም በሚልዝምአለ:: ወዲያው ቅዱሱ ሐዋርያ ዳቦ አንስቶ ቆረሰና"ለበረከት እያነሳችሁ ውሰዱ" አለ:: ሰውየው ተራውንጠብቆ ሊያነሳሲል እጁ ሰለለች::+ሐዋርያው "ምነው ልጄ! ምን ሆንክ?" አለው:: እሱምእንዳላመለጠ ሲያውቅ እውነቱን ተናዘዘ:: ቅዱስ ቶማስግን ሕዝቡሁሉ እንደተሰበሰበ ያን ወጣት ገስጾ "አስከሬኑንአምጡልኝ" አለ:: የወጣቱን እጅ ፈውሶ "በል . . .የገደልኩሽእኔ: የሚያስነሳሽ ግን ጌታየ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው . . . ብለህ አንገቷን ቀጥለው" አለው::+እንዳለው ቢያደርግ የሞተችው አፈፍ ብላ ተነሳች::ይህንን ተአምር ያዩ አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል::=>ከሐዋርያው በረከት ይክፈለን::=>ሰኔ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም2.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን3.ቅዱሳን ሐዋርያት4.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት5.ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ6.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ7.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ8.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘምስር (ሰማዕት)9.አባ ከላድያኖስ ሊቀ ዻዻሳት❖ወርኃዊ በዓላት1፡ አበው ጎርጎርዮሳት2፡ አባ ምዕመነ ድንግል3፡ አባ ዓምደ ሥላሴ 4፡ አባ አሮን ሶርያዊ5፡ አባ መርትያኖስ6፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል =>+"+ ስለ ጽዮን ዝም አልልም . . .አሕዛብም ጽድቅሽን: ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ::የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስምትጠሪያለሽ::በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል በአምላክሽም እጅየመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ:: +"+ (ኢሳ. 62:1-3)<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር>>>
5 months ago | [YT] | 12
👉👉🌹🌹 ሰኔ ፳ [20] ቀን 🌹🌹†#እንኳን_ለእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ ሕንጸተ ቤታ (ሕንጸታ) በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † † #በዓለ_ሕንጸታ † † በዚሕች ቀን : በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በአምላክ እናት ስም ታንጻለች::ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን "ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕበ" [አሕብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ] [ማቴ.፳፰፥፲፱] (28:19) ባላቸው ቃል መሠረት ዓለምን በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል::የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና [ዮሐ.፮፥፶፮] (6:56) አበው ሐዋርያት ቁርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር::በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን: ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲሕ ይከናወን ነበር:: ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኩራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአብ ያመኑ ሰዎች ቁጥር እጅጉን በዛ::በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ:: በዚሕ ምክንያት መምሕራን ሕዝቡን "ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?" ቢሏቸው "እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት እንደሆን የለን" ሲሉ መለሱላቸው::ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ጳውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች "ለምን አናንጽም" ብለው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ግን "ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም" አለ:: [ለዚሕ ነው ዛሬም ሊቀ ጳጳስ ካልፈቀደ ቤተ ክርስቲያን የማይታነጸው::]ከዚያ ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ጴጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱም "የጌታችን ፈቃዱ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ" ብሎ አዋጅ ነገረ::በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔአቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ::ሁሉንም ሐዋርያት በደመና ጭኖ ፊልጵስዩስ አደረሳቸው:: ከከተማ ወጣ ብሎ ባለ መሬት ላይም "ቤተ ክርስቲያንን በእናቴ ስም አንጹ" ብሎ አዘዛቸው:: ለቅዱስ ጴጥሮስም ሦስት ዓለቶችን ሰጠው::እነዚያን መሬት ላይ ተክሎ : ጌታችን ቆሞለት : ሐዋርያቱ እየተራዱት : ግርምት የምትሆን ሦስት ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን በ52 ዓ/ም በዚህች ቀን አንጿል::ቤተ ክርስቲያኗን ነገ ጌታችን ቀደሳት የምንል ነንና ይቆየን::† አምላካችን የድንግል እናቱን ፍቅር : የተቀደሰች ቤቱን ጸጋ : የቡሩካን ሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን::† ሰኔ ፳ [ 20 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፩. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፫. ቅዱሳን ሐዋርያት፬. ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ [ዕረፍቱ]† ወርኀዊ በዓላት፩. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት [ሰማዕት]፪. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር፫. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ፬. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)፭. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና፮. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት† "በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" † [፪ቆሮ. ፲፩፥፳፫-፳፰]† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †† ወለወላዲቱ ድንግል †† ወለመስቀሉ ክብር † † † †
5 months ago | [YT] | 10
👉🌹🌹 ሰኔ ፲፱ [19] ቀን 🌹🌹†#እንኳን_ለሐዲስ_ሰማዕት_ቅዱስ_ጊዮርጊስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † † #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሐዲስ † ሰማዕቱ የተወለደው በምድረ ግብጽ አሕ [ተንት] በሰለጠኑበት የመጀመሪያው ዘመን ነበር:: በተለይ ተንቱ ግብፅና ሶርያን ከያዙ በሁዋላ ባልተጠበቀ ፍጥነት በኃይልም በሰውም ተደራጅተው ነበር:: ቅዱስ ጊዮርጊስ [ልብ በሉልኝ ሊቀ ሰማዕታት አይደለም] የተወለደው በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር::እናቱ የተመሠከረላት ክርስቲያን ብትሆንም እንዳለመታደል አባቱ ተንባላታዊ [አ] ነበር:: ስሙንም መዛሕዝም ይሉታል:: ሕጻኑ እንደተወለደ ያወጡለት ስም አባዊ ከመሆኑ ባለፈ በሰዓቱ መጠመቅ አልቻለም:: የወቅቱ ሕግ ከወላጆቹ አንዱ አዊ ከሆነና አጠምቃለሁ ቢባል የሚከተለው ሰይፍ ነበር:: በዚሕ ምክንያት ሳይጠመቅ ፯ [7] ዓመት ሞላው::እናቱ ግን ሕጻን ቢሆንም ፍቅረ ክርስትናን ታስተምረው ነበር:: ባይጠመቅም ጸበሉን: እመቱን ትቀባው ነበር:: ደብቃ ቅዳሴ ታሰማውም ነበር:: አንድ ቀን ግን ሕጻናት ሲቆርቡ አይቶ ካልቆረብኩ ብሎ አለቀሰ:: ምን ታድርገው? ወደ ውጪ አውጥታ ከአውሎግያ [የሰንበት በረከት] አበላችው:: "ጌታየ! ልጄን እርዳው" አለች::ልክ በአፉ ሲቀምሳት መዓዛ መንፈስ ቅዱስ አደረበትና ፍጹም ተደሰተ:: ትንሽ ከፍ ሲል ለምን እንደማይጠመቅና እንደማይቆርብ እናቱን ጠየቃት:: "ልጄ ሆይ! ይገድሉሃል" አለችው:: ከዚህች ቀን ጀምሮ የሚጠመቅበትን ዘዴ ይፈልግ ጀመር::አስቀድሞ ትምሕርተ ክርስትናን ተማረ:: ለአካለ መጠን ሲደርስ አፈላልጐ ጠንካራ ክርስቲያን የሆነች ሴት አገባ:: ጥቂት ጊዜ ከቆየ በሁዋላ ሚስቱን ስለ መጠመቅ አማከራት:: "ሌላ ሃገር ሒደህ ተጠመቅ" አለችው:: ከግብፅ ተነስቶ ሶርያ ገባ:: አባቶችን አፈላልጎ ተጠመቀ:: ቀጥሎም መንገዱን ወደ ልዳ አደረገ::ወደ ደብሩ ተጠግቶ አባቶችን "ስም አውጡልኝ" ቢላቸው መንፈስ ቅዱስ አናግሯቸው "ጊዮርጊስ" አሉት:: እሱም ደስ እያለው: ባጭር ታጥቆ የልዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያገለግለው ገባ:: ትንሽ ቆይቶ ሁከት መንፈሳዊ ተሰማው:: ማለትም ስለ ሃይማኖቱ ደሙን ማፍሰስ ፈለገና ወደ ግብፅ ተመለሰ::በዚያ ያሉ አ በክርስትና ስም: ልብስና ሞገስ ሲመለከቱት ተበሳጩ:: ዕለቱኑ አሠሩት:: ሌሊት እናቱና ሚስቱ መጥተው አሉት:- "አደራ! ፍቅረ ዓለም እንዳያታልልህ:: ሰማዕት ብትሆን ላንተም ክብር: ለእኛም ሞገስ ነው" ብለውም አጽናኑት:: [እንዲሕ ያሉ እናትና ሚስት ማግኘትም ታላቅ እድል ነው!!!]ሐዲስ ጊዮርጊስም ጸና:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ደበደቡት: አካሉን ቆራረጡት: ደሙንም መሬት ላይ አንጠፈጠፉት:: በየመንገዱ እየጎተቱ ተሳለቁበት:: እርሱ ግን ክርስቶስን ወዷልና ሁሉን ታገሰ:: ሌሊት በሆነ ጊዜም ጌታችን ተገልጦ "ከሰማዕታት ተቆጠርህ" አለው::በማግስቱ በአደባባይ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት:: ክፋታቸው የጸና ነውና ሥጋውን በእሳት አቃጠሉት:: ወደ ባሕርም ጣሉት:: እናቱ ከባሕር ስታወጣው ግን ምንም አላገኘውም ነበር:: በዚሕች ቀን እናቱና ሚስቱ በክብር ቀብረውታል::ቸሩ አምላክ ከሰማዕቱ ጽናትን: ትእግስትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን::† ሰኔ ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፩. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ ሰማዕት፪. አባ ብሶይ አኖብ ሰማዕት [በአንበሳ ጀርባ ላይ የተቀመጠ አባት]፫. ቅዱሳን ፭ቱ "5ቱ" ጭፍሮች [በብዙ ስቃይ ሰማዕት የሆኑ ባልንጀሮች]፬. አባቶቻችን የደብረ ቁዋዐት ጻድቃን† ወርሐዊ በዓላት፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት፫. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም"ስለዚሕ ወንድሞቼ_ሆይ! ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና::" [፩ቆሮ.፲፥፲፬-፲፰] (10:14-18)† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †† ወለወላዲቱ ድንግል †† ወለመስቀሉ ክብር † † † †#ፐጁን #subscribers_like_share_copylink እያደረጋቹኝ አበረታቱኝ 💕🙏💕
5 months ago (edited) | [YT] | 12
👉👉🌹🌹 ሰኔ ፲፰ [18] ቀን 🌹🌹† #እንኳን_ለጻድቅ_ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_ድምያኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! † † #አባ_ድምያኖስ † † አባ ድምያኖስ ተወልደው ያደጉት ግብጽ ውስጥ ነው:: ቤተሰቦቻቸው ክርስቲያኖች በመሆናቸው ገና በልጅነት ዕድሜአቸው ቅዱሳት መጻሕፍትንና በጐ ምግባራትን ተምረዋል:: ዕድሜአቸው ወደ ወጣትነቱ ሲጠጋ ሥርዓተ መነኮሳትን ለማጥናት ወደ ገዳመ አባ ዮሐንስ ሔዱ:: በዘመኑ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ፈተና ሳያልፍ እንዲመነኩስ አይፈቀድለትም ነበር::አንድ ሰው ሊመነኩስ ካሰበ በትክክል መናኝ መሆኑ ቢያንስ ለሦስት ቢበዛ ደግሞ ለአሥራ ሁለት ዓመታት እንዲፈተን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታዝዛለች:: ይኸውም "ሥርዓተ አመክሮ" ይባላል:: ከአሥራ ሁለት ዓመታት በላይ መቆየት ከፈለገ ግን ይፈቀድለታል::በዚህም መሠረት አባ ድምያኖስ ለአሥራ ሰባት ዓመታት በአጭር ታጥቀው ገዳሙን አገልግለዋል:: ገዳሙም ይገባሃል በሚል ዲቁና እንዲሾሙ አድርጓል:: ከዚህ በኋላ ከአባቶች ተባርከው: ገዳሙንም ተሰናብተው ወጡ:: ነገር ግን የወጡት ወደ ዓለም ሳይሆን ራቅ ወዳለ ገዳም ነው::የረድዕነት ዘመናቸውን ጨርሰዋልና አዲስ በሔዱበት ገዳም ወደ መደበኛው ገድል ተሸጋገሩ:: ያም ማለት በጾም: በጸሎት: በስግደት: በትሕርምት: በትሕትናና በፍቅር ሙሉ ጊዜአቸውን ማሳለፍ ጀመሩ:: በእንዲሕ ያለ ግብርም ዘመናት አለፉ::የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ አባ ጴጥሮስ በእረኝነት ሥራ የሚያግዛቸው ሰው እንዲፈለግላቸው በጠየቁት መሠረት ትምሕርትም: ጽሕፈትም: በጐ ምግባራትም የተሟላለት ሰው እንደ አባ ድምያኖስ አልተገኘምና ያለፈቃዳቸው ወደ እስክንድርያ ተወስደው የፓትርያርኩ ረዳት ሆነው ተሾሙ:: በረዳትነት በቆዩበት ጊዜ በወንጌል አገልግሎትና በመንኖ ጥሪት ሕዝቡንና ሊቀ ጳጳሳቱን አስደስተዋል::ልክ አባ ጴጥሮስ ሲያርፉ ሕዝቡና ሊቃውንቱ በአንድ ድምጽ አባ ድምያኖስን ለፓትርያርክነት መርጧቸዋል::ጻድቁ ሊቀ ጳጳሳት በዘመነ ፕትርክናቸው ከግል የቅድስና ሕይወታቸው ባለፈ እነዚህን ፈተናዎች በመወጣታቸው ይመሰገናሉ::፩. ሕዝቡ ከሃይማኖታቸው እንዳይወጡና በምግባር እንዳይዝሉ ተግተው አስተምረዋል::፪. በአካል ያልደረሱባቸውን በጦማር [በመልዕክት] አስተምረዋል::፫. በዘመናቸው የተነሱትን መ ተከራክረው : የተመለሰውን ተቀብለው : እንቢ ያሉትን አውግዘዋል::፬. ከአንጾኪያ ፓትርያርክ የመጣውን የኑ ጦ [መልዕክት] በይፋ ተቃውመው አውግዘዋል::ለአርባ ሦስት ዓመታት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ሆነው ያገለገሉት አባ ድምያኖስ ከብዙ ትጋት በኋላ በመልካም ሽምግልና በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: ከግብጽ አበው ሊቃነ ጳጳሳት ዝርዝር ውስጥም አርባ አምስተኛ ሆነው ተመዝግበዋል::† ልመናቸው : ክብራቸው : ጸጋ ረድኤታቸው አይለየን::† ሰኔ ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፩. አባ ድምያኖስ ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት† ወርኀዊ በዓላት፩. ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ፪. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት [ረባን]፫. አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ፬. ማር ያዕቆብ ግብጻዊ† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት : ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" † [ሐዋ. ፳፥፳፰]† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †† ወለወላዲቱ ድንግል †† ወለመስቀሉ ክብር † † † †
👉🌹🌹 ሰኔ ፲፯ [17] ቀን 🌹🌹#እንኳን_ለአባ_ገሪማ_ይስሐቅ_መደራ_ለአባ_ለትጹን_የዋህ_እና_ለአባ_ዸላሞን_ፈላሲ የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት አደረሳችሁ።በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ✞ #አባ_ገሪማ_ይስሐቅ_መደራ ✞ አቡነ ገሪማ የተወለዱት በ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን ሮም ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸው መስፍንያኖስና ሰፍንግያ እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ:: ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑ፡፡እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን ይስሐቅ ብለው አሳደጉት:: ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ:: ለ፯ [7] ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ: መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል::አንድ ቀን ግን ከግብፅ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው:: ላኪው አባ ዸንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና" የሚል ነበር::ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ:: ድንገት ግን ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ ዸንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው::እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው አመነኮሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ ኢትዮዽያ መጡ:: ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና ታላቁ አባ ይስሐቅ [ገሪማ] ናቸው:: ሰውነታቸውን በገድል ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር::አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው አባ ዸንጠሌዎን አዘኑ:: ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ የሰማውብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ" አሉ:: አባ ይስሐቅ ግን "ሰዎች ብቻ አይደሉም: ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ ፰ መቶ ሜትር [800 ሜትር] ተጠራርጎ ሸሸ::ይሕንን የተመለከቱት አባ ዸንጠሌዎን "ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ [ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ] አሏቸው:: ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "አቡነ_ገሪማ" ተብለው ቀሩ፡፡አቡነ ገሪማ ወደ መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ" እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል::ጻድቁ ወንጌልን: ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል :-፩. ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር "በጽባሕይዘርዕ: ወበሠርክ የአርር" እንዲል::፪. ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር::፫. አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ::፬. ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች::፭. አንድ ቀን ድርሳን እየደረሱ ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይንአቁመዋታል::ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በኋላ ጌታችን ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው:: "ስምሕን የጠራ: መታሰቢያህን ያደረገ: እስከ ፲፪ [12] ትውልድ እምርልሃለሁ:: አንተ ግን ሞትን አትቀምስም" ብሏቸው ተሰወረ:: ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ ብሔረ ሕያዋን አድርሰዋቸዋል፡፡ ✞ #አባ_ለትጹን_የዋህ ✞ ስመ ጥሩ ጻድቅ አባ ለትጹን በ፬ [4] ኛው መቶ ክ/ዘመን በግብጽ የተወለዱ:- በፍጹም ተግሣጽ ያደጉ:- ከልጅነታቸው ጀምሮ ራሳቸውን በሕገ ወንጌል የመሩ:- አንድ ቀን በሰሟት የወንጌል ቃል የመነኑ:- ገዳም ገብተው በትሕትና ለዘመናት ያገለገሉ:- በመጨረሻም ወደ ትልቅ ተራራ ወጥተው ተጋድሏቸውንየፈጸሙ ታላቅ አባት ናቸው::ከየዋሕነታቸው የተነሳ ኃጢአተኛ ሰው ሲያገኙ ራሳቸው ንስሃ ይገቡ ነበር:: አንዴ ግን እናቱን ፲ [10] ጊዜ በዝሙት ያረከሰ: ስትጸንስም መርዝ አጠጥቶ ጽንሱን በማሕጸኗ የገደለና በሥጋ ወደሙ ላይ የተዘባበተ ሰው ሊሞት ሲል ደረሱ::አጋንንት ሲዖል ታች ሲጥሉትም ተመለከቱ:: ኃጢአቱ ጭንቅ ቢሆንም የእርሱን ንስሃ ሊቀበሉ ጀመሩ: ከንስሃቸው ጽናት የተነሳ ሞቱ:: ጌታችን ከሞት አስነስቶ "አትለምነኝ: አልምረውም" አላቸው::ጻድቁ ተስፋ አልቆረጡምና ቀጠሉ:: ለ፪ [2] ኛ ጊዜ ሞቱ:: አሁንም ቀጠሉ: ፫ [3] ኛ: ፬ [4] ኛ: ፭ [5] ኛ ጊዜም ሞቱ:: በ፮ [6] ኛው ግን መፍትሔ መጣ:: ጌታችን አእላፍ መላእክትን አስከትሎ: ያችንም ኃጥእ ነፍስ ይዞ መጣ:: "ፍርዴ አይታጠፍምና ወደ ገነት አላስገባትም:: ስለ አንተ ጽድቅና የዋሕነት ደግሞ ሲዖል አልጥላትም:: ስለዚሕም እንዳልተፈጠረች ትሁን" ብሎ እፍ አለባት:: ፈጥና ወደ ትቢያነት ተቀየረች::ጻድቁም የፈጣሪያቸውን ቸርነት አድንቀው ሰገዱ:: ከብዙ ዘመናት ተጋድሎ በኋላም በዚህች ቀን ዐረፉ:: ✞ #አባ_ዸላሞን_ፈላሲ ✞ ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው ታላላቅ ገዳማውያን አንዱ አባ ዸላሞን የአባ ለትጹን ወዳጅ ነበር:: ይሕ ቅዱስ ከአጋንንት ጋር በገጠመው ጦርነት ምክንያት ለየት ይላል:: ከ፷ [60] ዓመታት በላይ እንኳን ሳቅና ደስታ ቀና ብሎም ሰው አላየም::በነዚሁ ዘመናት ሁሉ ቅንድቡ እስኪላጥ አልቅሷል:: በዓለም ያሉ አጋንንት ሁሉ ተሰብስበው አሰቃይተውታል:: እርሱ ግን በእግዚአብሔር ቸርነት: በወዳጁ በአባ ለትጹን ጸሎትና በትጋት አሸንፏቸው ዛሬ ዐርፏል::ቸሩ አምላካችን ከታላላቁ ቅዱሳን ጸጋ በረከት ይክፈለን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን::† ሰኔ ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፩. ብጹዕ አባ ገሪማ [ይስሐቅ] ዘመደራ፪. አባ ለትጹን ዐቢይ ወየዋሕ፫. አባ ዸላሞን ፈላሲ፬. ቅድስት አርሴማ ጻድቅት፭. ሰማዕታት እለ አኮራን፮. ፯፼ ፹፻ ሰማዕታት ማኅበረ ቅዱስ ተክለሃ ይማኖት † ወርኃዊ በዓላት ፩ ፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት፪ ፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ዘቆጵሮስ፫ ፡ ቅዱሳን መክሲሞስ ወደማቴዎስ፬ ፡ ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ" እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል. . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም:: " [መዝ. ፴፮፥፳፰-፴፩] (36:28-31)† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †† ወለወላዲቱ ድንግል †† ወለመስቀሉ ክብር † † † †
5 months ago | [YT] | 22
Load more
wendmieneh
👉🌹🌹 ሰኔ ፳፮ [26] ቀን 🌹🌹
†#እንኳን_ለታላቁ_ነቢይ_ቅዱስ_ኢያሱ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። †
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
† #ቅዱስ_ኢያሱ_ነቢይ_ወመስፍን †
† ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ "አውሴ" ይባላል:: ዘመኑ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ፪፻፲፭ [215] ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ ፹ [80] ዓመቱ : ኢያሱ ደግሞ ፵ [40] ዓመቱ ነበር::
ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ፵ [40] ቀን የታሠበላቸውን መንገድ ፵ [40] ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም::
አውሴን "ኢያሱ" ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው:: ኢያሱ ማለት "መድኃኒት" ማለት ነው:: ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:- ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል:: ምድረ ርስትን አውርሷል:: ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ [ጥላ] እንዲሆን ነው::
ቅዱስ ኢያሱ በበርሃ ለ፵ [40] ዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዝዞታል [አገልግሎታል]:: እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአህብ እጅ አድኗቸዋል::
በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ ደብረ ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን : ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው ፹ [80] እየሆነ ነበር::
† እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን [አስተዳዳሪ] እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ:
¤ ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ
¤ ሕዝቡን አሻግሮ
¤ የኢያሪኮን ቅጥር ፯ [ 7 ] ጊዜ ዙሮ
¤ በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ
¤ የኢያን ነገሥታት አጥፍቶ ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ::
የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዚያን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል : በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚያች ዕለትም ለ፲፪ [12] ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም [በኤሎም ሸለቆ] አቆመ::
ሰባት አሕጉራተ ምስካይ [የመማጸኛ ከተሞችን] ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ፵ [40] ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ አላቸው :-
"እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: [ኢያ.፳፬] (24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ ፫ [3] ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ::
ይህችውም የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ ፫ [3] ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ፫ [3] ወገን [በነፍስ: በሥጋ: በልቡና] ድንግል ናት:: አንድም በ፫ [3] ወገን [ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት] ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው አባ ሕርያቆስ "ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" [የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ] ሲል ያመሰገናት::
ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ፹ [80] ዓመት: በተወለደ በ፻፳ [120] ዓመቱ [ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ፻፲ [110] ዓመቱ ይላል] በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ፴ [30] ቀናት አለቀሱለት::
† በወዳጁ በኢያሱ እጅ የአሕብን ቅጥር ያፈረሰ እግዚአብሔር የእኛንም የኃጢአታችንን ግንብ በወዳጆቹ ምልጃ ያፍርስልን:: ከቅዱሱ ነቢይም በረከትን ያሳትፈን::
† ሰኔ ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩. ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን
፪. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት [ቅዳሴ ቤቱ]
† ወርሐዊ በዓላት
፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
፫. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፬. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
፭. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
† "አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ:: በእውነተኛም ልብ አምልኩት . . . እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ . . . የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ: የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን::" † [ኢያሱ.፳፬፥፲፬] (24:14)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክብር †
† † †
5 months ago | [YT] | 11
View 0 replies
wendmieneh
👉✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ ✝እንኩዋን ከዘመነ ጸደይ ወደ ዘመነ ክረምት መሸጋገሪያ ለሆነችው ዕለትና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞✝
=>ስንዱ እመቤት ቤተ ክርስቲያን (ሃገራችን) ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች:: እሊሕም ዘመናት መጸው (ጽጌ): ሐጋይ (በጋ): ጸደይ (በልግ)ና ክረምት ናቸው:: ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል::
+በተለይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና "ሽሽታችሁ (ስደታችሁ) በክረምትና በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ" ብሎናልና (ማቴ. 24:20) ልንጸልይ ይገባናል:: በዘመነ ክረምት ቅጠል እንጂ ፍሬ የለበትምና ፍሬ ምግባር ሣናፈራ ሞት እንዳይመጣ: አንድም ክረምት የዝናብና የጭቃ ጊዜ በመሆኑ እንኩዋንስ ለስደት ለኑሮም አይመችምና እንደ ሊቃውንት እንዲህ ብለን እንጸልይ:-
"በዝንቱ ክረምት በመዋዕሊነ:
እንበለ ፍሬ እንዘ በቆጽል ኀሎነ:
ናስተበቁዐከ እግዚኦ ኢይኩን ጉያነ::"
(ክረምት በተባለ በእኛ እድሜ:
ፍሬ ሳናፈራ በቅጠል /ያለ መልካም ሥራ/ ሳለን:
አቤቱ ጌታ ሆይ ስደትን አታምጣብን)
=>ቸሩ አምላካችን ከዘመነ መጸው በሰላም ያድርሰን:: ተረፈ ዘመኑንም የንስሃ: የፍሬና የበረከት ያድርግልን::
=>በዚሕች ዕለት እነዚህ ቅዱሳን ይከበራሉ:-
+" ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ "+
+በዘመነ ሐዋርያት ይሁዳ ተብለው ይጠሩ ከነበሩት አንዱ የሆነው ቅዱሱ የአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ልጅ ሲሆን እናቱ ማርያም ትባል ነበር:: እናቱ ስትሞትበት ተጎድቶ የነበረ ቢሆንም ገና በልጅነቱ ድንግል ማርያም አግኝታው በፍጹም ጸጋ አሳድጋዋለች:: አስተዳደጉም ከጌታችን ጋር በአንድ ቤት ነበር::
ጌታችን እርሱንና ወንድሞቹን (ያዕቆብና ስምዖንን) ከ72ቱ አርድእት ቆጥሯቸዋል:: ቅዱስ ይሁዳ ወንጌል ላይ ከጌታችን ጋር መነጋገሩን ዮሐንስ ወንጌላዊ መዝግቧል:: (ዮሐ. 14:22)
+ቅዱስ ይሁዳ ከጌታችን እግር 3 ዓመት ተምሮ: መንፈስ ቅዱስንም ተቀብሎ ብዙ አሕጉራትን ዙሯል:: አይሁድንም አረማውያንንም ወደ ክርስቶስ ይመልስ ዘንድ ብዙ ድካምና ስቃይን በአኮቴት ተቀብሏል:: አንዲት አጭር (ባለ አንድ ምዕራፍ) መልእክትም ጽፏል:: አጭር ትምሰል እንጂ ምሥጢሯ እጅግ የሠፋ ነው:: ቅዱስ ይሁዳን በዚህች ቀን አረማውያን ገድለውት በሐዋርያነቱ ላይ የሰማዕትነትን ካባ ደርቧል::
+" ቅዱሳን ዺላጦስና አብሮቅላ "+
=>ብዙዎቻችን መስፍኑን ዺላጦስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን እንዳይሰቀል ከአይሁድ ጋር ሲከራከር እናውቀዋለን:: የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ ነበርና አይሁድ እንቢ ሲሉት የክርስቶስን ንጽሕና መስክሮ: እጁንም ታጥቦ ሰጥቷቸዋል:: የዺላጦስ ታሪክ ግን እዚህ ላይ አያበቃም::
+ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ከተነሳ በሁዋላ ትንሳኤውን በራዕይ ገልጦለት አይሁድን ተከራክሯቸዋል:: ውሸታም ወታደሮችንም ቀጥቷል:: በመጨረሻ ግን በሮም ቄሳር ተጠርቶ ከእሥራኤል እስከ ሮም ድረስ ሰብኮ በሮም አደባባይ አንገቱ ተሠይፏል::
+ቅድስት እናታችን አብሮቅላም የዺላጦስ ሚስት ስትሆን ቁጥሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ነው:: ጌታችንን ተከትላ: ቤቷን ለሐዋርያት አስረክባ: ቤተ ክርስቲያንንም በዘመኗ አገልግላ ዐርፏለች:: ዛሬ ሁለቱም ቅዱሳን ይታሠባሉ::
=>ጌታችን ከሐዋርያው ይሁዳ: ከዺላጦስና አብሮቅላም ጸጋ በረከትን ያድለን::
=>ሰኔ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.ሰማዕቱ ዺላጦስ መስፍን
3.ቅድስት አብሮቅላ (ሚስቱ)
4.አባ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት
5.የጸደይ መውጫ / የክረምትመግቢያ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ /አባ ቡላ/
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
=>+"+ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ: የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ በእግዚአብሔር አብ ተወደው: ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ:
ምሕረትና ሰላም: ፍቅርም ይብዛላችሁ::
ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩዋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ:: +"+ (ይሁዳ. 1:1)
✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞
5 months ago | [YT] | 14
View 0 replies
wendmieneh
👉✞✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ✝እንኳን አደረሳችሁ ✝❖
❖ ሰኔ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ✝ቅዱስ_ሙሴ_ጸሊም (ጥቁሩ ሙሴ) ✝+"+
=>ግብጻውያን ስማቸውን ጠርተው ከማይጠግቧቸው
ቅዱሳን መካከል አንዱ ኢትዮዽያዊው አባ ሙሴ ጸሊም
ነው:: በእኛ
ኢትዮዽያውያን ግን ይቅርና በወርኀዊ በዓሉ (በ24)
በዓመታዊ በዓሉ እንኩዋ ሲከበር ብዙም አይታይም::
=>ቅዱሱ ሰው በትውልዱ ኢትዮዽያዊ
ሲሆን ያደገውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ እንደሆነ
ይታመናል:: ገና በወጣትነቱ አገር የሚያሸብር ሽፍታ ነበር::
ሙሴ ጸሊም
ወደ ግብጽ የሔደበት ምክንያት በግልጽ ባይታወቅም
መምለክያነ ጣዖት (ፀሐይን ከሚያመልኩ ሰዎች) ጋር
ይኖር ስለ ነበር
ምናልባት እነርሱ ወስደውት ሊሆን ይችላል::
+ቅዱስ_ሙሴ በምድረ ግብጽም በኃይለኝነቱ ምክንያት የሚደፍረው
አልነበረም:: ፀሐይን ያመልካል: እንደ ፈለገ ቀምቶ
ይበላል: ያሻውን
ሰው ይደበድባል:: ነገር ግን በኅሊናው ስለ እውነተኛው
አምላክ ይመራመር ነበርና አንድ ቀን ፀሐይን "አምላክ
ከሆንሽ
አናግሪኝ?" አላት:: እርሷ ፍጡር ናትና ዝም አለችው::
+ቅዱስ ሙሴ ምንም አስቸጋሪ ሰው ቢሆንም ፈጣሪን
መፈለጉን ግን ቀጥሏልና አንድ ቀን ተሳካለት:: መልካም
ክርስቲያኖችን
አግኝቶ . . . ወደ ገዳመ_አስቄጥስ ቢሔድ በዛ ያሉ መነኮሳት ወደ እውነት እንደሚመሩት
ነገሩት:: እርሱም ሰይፉን እንደታጠቀ ወደ ገዳም ገባ::
መነኮሳቱ
ፈርተውት ሲሸሹ ታላቁ አባ_ኤስድሮስ ግን ተቀብለው አሳረፉት::
+"ምን ፈለግህ ልጄ?" አሉት:: "እውነተኛውን አምላክ ፊት
ለፊት ማየት እፈልጋለሁ" የሙሴ ጸሊም መልስ ነበር:: አባ
ኤስድሮስም "የማዝህን ሁሉ ካደረግህ ታየዋለህ" ብለው
ወደ መነኮሳት አለቃ ቅዱስ_መቃርስ_ታላቁ ወሰዱት:: መቃሬም ክርስትናን አስተምረው አጠመቁትና
ለአባ ኤስድሮስ መለሱላቸው::
+ከዚህ ሰዓት በሁዋላ ነበር የአባ ሙሴ ጸሊም ሕይወት
ፍጹም የተለወጠው:: በጻድቁ እጅ ምንኩስናን ተቀብሎ
ይጋደል
ጀመር:: በጠባቧ በር ይገባ ዘንድ ወዷልና ያ በሽፍትነት
የሞላ አካሉን በገድል አረገፈው:: ከቁመቱ በቀር ከአካሉ
አልተረፈለትም:: ወገቡን በአጭር ታጥቆ መነኮሳትን
አገለገለ:: አጋንንት በቀደመ ሕይወቱ በሕልም: አንዳንዴም
በአካል
እየመጡ ይፈትኑት ነበር::
+እንዳልቻሉት ሲረዱ ተሰብስበው መጥተው በእሳት
አለንጋ ገርፈው አቆሳስለውት ሔዱ:: እርሱ ግን ታገሰ::
በበርሃ ለሚኖሩ
አበው መነኮሳት ሁሉ ብርሃን በሆነ ሕይወቱ ሞገስ ሆነላቸው:: ለኃጥአን ደግሞ መጽናኛ
ሆነ::
<< በተራራ ላይ ያለች ሃገር ልትሠወር አይቻላትምና ስም
አጠራሩ በመላው ዓለም ተሰማ:: ሁሉም "ሙሴ_ጸሊም ይል ጀመር ፡፡ >>
+በየበርሃው ያሉ አበው ብቻ ሳይሆነ ዓለማውያን
መኩዋንንት ሳይቀሩ ሊያዩት ይመኙ ነበር:: እርሱ ግን
ራሱን "አንተ
ጥቁር ባሪያ ስለ ኃጢአትህ አልቅስ" እያለ ይገስጽ:
ከውዳሴ ከንቱም ይርቅ ነበር:: ከቆይታ በኋላም
በመነኮሳት ላይ
እረኛ (አበ ምኔት) ሆኖ ተሾመ:: እንደሚገባም አገለገለ::
የበርካቶችን ሕይወት ጨው በሆነ ሕይወቱና ምክሩ
አጣፍጦ:
ድርሳናትንም ደርሶ እያረጀ ሔደ::
+ከቁመቱ መርዘም የጽሕሙ ነጭነትና አወራረዱን ያዩ
ሁሉ ሲያዩት ያደንቁት ነበር:: በመጨረሻም በ375 ዓ/ም
በርበረሮች
(አሕዛብ) ገዳመ አስቄጥስን ሲያጠፉ ሌሎች መነኮሳት
ሸሹ:: እርሱ ግን አልሸሽም ብሎ ከ7 ደቀ መዛሙርቱ ጋር
በዚሕች
ቀን ተሰይፎ በሰማዕትነት አልፏል::
=>ቅዱስ ሙሴ ጸሊምን ለርስቱ ያበቃ ጌታ ለእኛም ዕድሜ
ለንስሃ: ለዘመን ለፍስሃን አይንሳን:: ከበረከቱም ፈጣሪው
ያድለን::
=>ሰኔ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮዽያዊ)
2."7ቱ" ቅዱሳን መነኮሳት (ደቀ መዛሙርቱ)
3.አባ ኤስድሮስ ታላቁ
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት
2፡ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
3፡ ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ
4፡ ቅዱስ አጋቢጦስ
5፡ ቅዱስ አብላርዮስ
6፡ አቡነ ዘዮሐንስ ዘክብራን
7፡ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ
=>+"+ መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና
ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ
ሊፈልገው
የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት
በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ
ወዳጆቹንና
ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ "የጠፋውን በጌን
አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ" ይላቸዋል::
እላችሁአለሁ:
እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን
ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ
ይሆናል:: +"+ (ሉቃ. 15:3-7)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
5 months ago | [YT] | 9
View 0 replies
wendmieneh
👉✞✞✝ የሰኔ 23 ✝✞✞
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖✝ እንኳን አደረሳችሁ✝ ❖
❖ ✝ሰኔ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ ✝ቅዱስ_ሰሎሞን ንጉሠ እሥራኤል✝ +"+
=>መፍቀሬ ጥበብ:
¤ጠቢበ ጠቢባን:
¤ንጉሠ እሥራኤል:
¤ነቢየ ጽድቅ:
¤መስተሣልም (ሰላማዊ) . . . እየተባለ የሚጠራው
ቅዱስ ሰሎሞን የታላቁ ነቢይና ንጉሥ ልበ
አምላክ ቅዱስ_ዳዊትና የቅድስት ቤርሳቤህ (ቤትስባ) ልጅ ነው:: ከ3ሺ ዓመታት በፊት የተወለደው ቅዱስ
ሰሎሞን እስከ 12 ዓመቱ ድረስ በቤተ መንግሥት ከአባቱ
ጋር
አድጉዋል::
+ቅዱስ ዳዊት 70 ዘመን በሞላው ጊዜ የአካሉን
መድከም አይቶ አዶንያስ በጉልበት እነግሣለሁ ቢልም
አልተሳካለትም::
እግዚአብሔር ሰሎሞንን መርጧልና ገና በ12 ዓመቱ
ነገሠ:: ልበ_አምላክ አባቱ ዳዊት ነፍሱ ከሥጋው ከመለየቷ በፊት መከረው::
"ልጄ ሆይ! ልብህን ስጠኝ:: ፈጣሪህንም አምልክ"
አለው::
+ቅዱስ ሰሎሞን እንደ ነገሠ በገባዖን ለእግዚአብሔር
መስዋዕትን አቀረበ:: ጌታም ተገልጾ "ምን ትፈልጋለህ?"
አለው::
ሰሎሞንም ልክ እንደ አባቱ ማስተዋልን: ልቡናን ለመነ::
በዚህም ጌታ ደስ ስለተሰኘ "አልቦ እምቅድሜከ: ወአልቦ
እምድኅሬከ - ከአንተም በፊት: ከአንተም በኋላ እንዳንተ
ያለ ጠቢብና ባለጠጋ ሰው የለም: አይኖርም" ብሎት
ተሠወረ::
ቅዱስ ሰሎሞን ለ40 ዓመታት በእሥራኤል ላይ ነገሠ::
+ግሩም በሆነ ፍትሑ: በልዩ ጥበቡ ዓለም ተገዛለት::
እግዚአብሔር የመረጣት የእኛዋ ንግስተ_ሳባ /አዜብ/ማክዳም ትፈትነው ዘንድ ሒዳ ምኒልክን (እብነ_መለክን) ጸነሰች:: በኋላም ታቦተ_ጽዮንና ሥርዓተ ኦሪት መጣልን:: ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን ድንግል_ማርያም ከእነሱ ዘር እንደምትወለድ ነግሮት ነበርና ያበጀሁ መስሎት
ሴቶችን አብዝቶ ነበር::
+ነገር ግን:-
¤አንደኛ ሰው (ሥጋ ለባሽ) ነውና:
¤ሁለተኛ ደግሞ ከብዙ ሴቶች መካከል
ከአንዷ እመ_ብርሃን ትገኛለች መስሎት ነበር:: ነገሩ መንገድ ስቶበት ከአሕዛብ
(ከፈርዖን ልጅ) ጋር በመወዳጀቱ ለጣዖት አሰገደችው::
እግዚአብሔር እጅግ አዘነ::
+በራዕይ ተገልጦ "ስለ ወዳጄ ስለ ዳዊት ስል በአንተ ላይ ክፉን አላደርግም" አለው:: ታላቁ ነቢይ
ሰሎሞን ይህንን ሲሰማ ወደ ልቡ ተመለሰ:: ማቅ ለብሶ:
አመድ
ነስንሶ በፍጹም ልቡ አለቀሰ:: ንስሃ ገባ:: መፍቀሬ ንስሃ
ጌታችንም ንስሃውን ተቀበለው::
+የይቅርታው መገለጫም ተወዳዳሪ የሌላቸውን 5
መጻሕፍት ገለጠለት:: ተናገራቸው:: ጻፋቸው:: እሊሕም:-
1.መጽሐፈ ጥበብ
2.መጽሐፈ ተግሣጽ
3.መጽሐፈ መክብብ
4.መጽሐፈ ምሳሌ
5.መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ናቸው::
+ቅዱስ ሰሎሞን ልዩ የሆነውን ቤተ_መቅደስ በመስራቱም ይደነቃል:: ደጉ ንጉሥ: ጠቢብና ነቢይ
ሰሎሞን በዚህች ዕለት በ52 ዓመቱ ዐርፎ ወደ ፈጣሪው
ሔዷል::
+"+ አባ_ኖብ +"+
=>ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ሰማዕት አባ ኖብ አርፏል::
በዚሕ ስም የሚጠሩ ብዙ ቅዱሳን ቢኖሩም ዋናው ይኼው
ቅዱስ
ነው::
+አባ ኖብ እንደ ገዳማውያን በበርሃ የተጋደለ: እንደ
ሊቃውንት መጻሕፍትን ያመሰጠረ: በተለይ ደግሞ በዘመነ
ሰማዕታት
ጭንቅ ጭንቅ መከራዎችን የተቀበለ አባት ነው:: ስለ
ገድሉ ብዛት "ኃያል ሰማዕት": አንገቱን ስላልተቆረጠም
"ሰማዕት
ዘእንበለ ደም" ይባላል:: ዘመነ ሰማዕታትን ካለፉ 72ቱ
ከዋክብትም አንዱ ነው::
=>ከመፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን: ከኃያሉ ሰማዕት አባ
ኖብ በረከትን አምላካችን ይክፈለን::
=>ሰኔ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
2.ቅዱስ አባ ኖብ (ሰማዕት ወጻድቅ)
3.ቅዱሳን መርቆሬዎስ: ፊልዾስና ቶማስ (ሰማዕታት)
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ
2፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3፡ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
4፡ አባ ሳሙኤል
5፡ አባ ስምዖን
6፡ አባ ገብርኤል
7፡ ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
=>+"+ የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት
ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት
ሳይደርሱ:
ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም
ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ
እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ::
ሰባኪው:- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል:: +"+
(መክ. 12:1-9)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
5 months ago | [YT] | 11
View 0 replies
wendmieneh
👉†††✝ እንኳን ለቅዱሱ አባታችን የዋህ ዻውሊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። †††
†††✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ✝ቅዱስ ዻውሎስ የዋህ ✝†††
††† በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ግብፅ ውስጥ ተወልዶ ያደገው ቅዱሱ ስሙ ዻውሎስ ቢሆንም ብዙ ጊዜ የሚጠራው "የዋህ ዻውሊ" በሚል ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
የዋህ ዻውሊ ከሕጻንነቱ ጀምሮ መጻሕፍትን የተማረ: ግን ደግሞ ትዕቢት: ቁጣና ቂምን የማያውቅ ገራገር ሰው ነው:: እድሜው ለአካለ መጠን ሲደርስ ቤተሰቦቹ ሚስት አግባ አሉት:: እርሱ ባያስብበትም ወገኖቹን ላለማሳዘን አገባ:: እንዳለመታደል ሆኖ ግን ያገባት ሴት በጣም ቆንጆ በዚያም ላይ ክፉ ነበረች:: የዋህ ዻውሊ ክፋቷን ሁሉ ታግሶ ለበርካታ ዓመታት አብሮ ኖረ:: ልጆችንም አፈሩ::
አሁንም ግን እርሷ ከክፋቷ ልትታገስ አልቻለችም:: ይባስ ብሎ ዻውሊ በሌለበት ከሌሎች ወንዶች ጋር ትዘሙት ያዘች:: የዋሁ ሰው ይሕንኑ ያውቃል ግን የእግዚአብሔርን ሥራ ዝም ብሎ በተስፋ ይጠብቅ ነበር:: ለነገሩስ እሱ ያርሳል: ይቆፍራል: ነዳያንን ያበላል: እንግዳ ይቀበላል እንጂ ክፋትን ለማሰብ ጊዜ አልነበረውም::
አንድ ቀን ግን ለሥራ ወደ በርሃ ወጥቶ አንድ ግሩም ዜና ሰማ:: "አባ እንጦንስ ምንኩስና የሚባል ሕይወተ መላእክትን ጀምሯል: ደቀ መዛሙርትንም ይቀበላል" አሉት:: ግን ሚስትና ልጆች አሉትና ምን ያደርጋል?
የዋህ ዻውሊ ሙሉ ቀን ሢሠራ ውሎ ወደ ቤቱ ሲመለስ ግን የጠበቀው ሌላ ነው:: ሚስቱ በራሱ መኝታ ላይ ከአገልጋይ እረኛው ጋር ራቁታቸውን አገኛቸው:: ልብ በሉልኝ በትክሻው ሞፈርና ምሳር: መጥረቢያም ይዟል:: እርሱ ግን ክፉን አላሰበም:: ጥሩ ልብስ አንስቶ ሁለቱንም አለበሳቸው::
እንዲሕም አላቸው:- "ከዚሕ በሁዋላ እኔ አልመለስም:: ሀብት ንብረቴን ውረሱ: በደስታም ኑሩ:: የልጆቼን ነገር ግን አደራ" ብሏቸው ተነሳ::
በእጁ ምንም አልያዘም:: በትከሻው ያለችውን ብጣሽ ጨርቅ ይዞ ወደ በርሀ ተጉዋዘ:: አባ እንጦንስም ተቀብለው አስተምረው አመነኮሱት:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ራስን ዝቅ በማድረግ: በመታዘዝ አገለገለ:: ጾም: ጸሎትና ስግደቱንማ ማን ቆጥሮት::
እያለ እያለ ከብቅዐት ማዕርግ ደረሰ:: ምዕመናንም ሆነ መነኮሳት ሊጠይቁት ሲመጡ የእያንዳንዱ ኃጢአት በግንባራቸው ተጽፎ ይመለከት ነበርና ስለነሱ ሲያለቅስ ቅንድቡ ተላጠ:: ሰውነቱም አለቀ:: አንድ ቀን ጋኔን የያዘውን ሰው ፈውስ ብለው አመጡለት:: እርሱ ግን በአጋንንት ላይ ሥልጣን እያለው በትሕትና ተጠግቶ ጋኔኑን "አባ እንጦንስን ከምጠራብህ ቀስ ብለህ ውጣ" አለው:: ጋኔኑ ግን የፈራው መስሎት በትዕቢት "እንጦንስ ማነው?"አለው::
ያን ጊዜ የዋህ ዻውሊ እንደ እሳት ከጋለ ድንጋይ ላይ ቁሞ "ሕያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው:: ይሕ ጋኔን ካልወጣ አልወርድም" አለ:: ወዲያው በዘንዶ አምሳል ከሴትዮዋ ወጥቶ እየጮኸ ወደ ቀይ ባሕር ገባ::ቅዱስ ዻውሊ የዋሕም እንዲሕ በቅድስና ተመላልሶ በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፏል::
" የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር: ደስታ: ሰላም: ትእግስት: ቸርነት: በጐነት: እምነት: የውሃት: ራስን መግዛት ነው:: እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም:: የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ::" (ገላ. 5:22)
††† ሰኔ 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ዻውሊ የዋሕ
2.ቅዱሳን ወክቡራን ቆዝሞስና ድምያኖስ (ሰማዕታት)
3.ቅድስት ቴዎዳዳ ሰማዕት (እናታቸው)
4.አንቲቆስ: ዮንዲኖስና አብራንዮስ (ሰማዕታት)
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ እንጦንዮስ (አበ መነኮሳት)
††† አምላካችን ከቅዱስ ዻውሊ የውሃትን: ትእግስትን: በጐነትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን:: አሜን:: †††
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
5 months ago | [YT] | 13
View 0 replies
wendmieneh
#✞✞✞✝🌹 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✝🌹✞✞✞
❖✝🌹 እንኳን አደረሳችሁ ✝🌹❖
❖✝🌹 ሰኔ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት✝🌹
=>ትናንት ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና
መድኃኒታችን ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ ሐዋርያት ወረደ:: ፊልዽስዩስ በምትባል ሃገር በዼጥሮስ እጅ
የመጀመሪያዋን ቤተ_ክርስቲያን አነጸ ብለን ነበር:: በዚህች ዕለት ደግሞ አእላፍ
መላዕክትን: ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት
ድንግል
ማርያምን ይዟት ወረደ::
+ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን
ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ:-
1.አስቀድሞ ቤተ ክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ
ሥርዓተ ቤተ ክርረስቲያንን አሳየ::
2.ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ_ዼጥሮስን ከመካከል አቁሞ "አርሳይሮስ" ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት
(ፓትርያርክ) ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት
"አክዮስ" እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: አክዮስ ማለት በግዕዙ
"ይደልዎ": በዐማርኛው ደግሞ "ይገባዋል: ያሥምርለት"
እንደ
ማለት ነው::
+ጌታችን ይሕን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ::
¤አማናዊት ማሕደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ:
¤ቅዱስ ዼጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ:
¤ቅዱስ_እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ሆኖ:
¤ሐዋርያት ድንግልን ከበው:
¤መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቁመው ጌታችን ቀድሶ
ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ::
+በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር
የማይችል ደስታ ተደረገ:: ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን
ሐዋርያትን
አዘዛቸው::
"ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም
አብያተ ክርስቲያናትን እነጹ:: ይህችን ዕለት የሚያከብራትን
አከብረዋለሁ::" ብሏቸው ከድንግል እናቱ ከመላዕክቱ ጋር
ዐረገ::
+"+ ሰኔ_ጐልጐታ +"+
=>ዳግመኛ በዚህ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ
ይታሰባል::
ይኸውም ከሕንድ አውራጃዎች በአንዱ ወንጌልን ሰብኮ
እኩሎቹ ሲያምኑ እኩሎቹ እንቢ አሉ:: ቅዱስ ቶማስም
ያመኑትን
"ከጣዖት አምልኮና ከዝሙት ሸሹ" ብሎ መከራቸው::
+ምክሩን ከሰሙት አንዱ በዚያው ምሽት ሊጠጣ ወደ
መሸታ ቤት ይገባል:: ሰው ሁሉ ከወጣ በኋላ ባለ
መሸተኛዋ ሴት
እንደለመደችው አብረው እንዲተኙ ስትጠይቀው "እንዴት
ሐዋርያው ከዝሙት ሽሹ እያለ እንዲህ ትይኛለሽ?" በሚል
ሰይፍ
አውጥቶ አንገቷን ቆረጣት::
+እርሱ መልካም ያደረገ መስሎታል:: የሠራው ሥራ
(መግደሉ) ግን አሕዛባዊ ግብር ነው:: በማግስቱ ቅዱስ
ቶማስ ነገሩን
ሰምቶ ሰዎችን ሰበሰበና "ይህንን የአውሬ ድርጊት የፈጸመ
ማነው?" ሲል ጠየቀ:: ፈጻሚው ግን አልታወቅም በሚል
ዝም
አለ:: ወዲያው ቅዱሱ ሐዋርያ ዳቦ አንስቶ ቆረሰና
"ለበረከት እያነሳችሁ ውሰዱ" አለ:: ሰውየው ተራውን
ጠብቆ ሊያነሳ
ሲል እጁ ሰለለች::
+ሐዋርያው "ምነው ልጄ! ምን ሆንክ?" አለው:: እሱም
እንዳላመለጠ ሲያውቅ እውነቱን ተናዘዘ:: ቅዱስ ቶማስ
ግን ሕዝቡ
ሁሉ እንደተሰበሰበ ያን ወጣት ገስጾ "አስከሬኑን
አምጡልኝ" አለ:: የወጣቱን እጅ ፈውሶ "በል . . .
የገደልኩሽ
እኔ: የሚያስነሳሽ ግን ጌታየ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው . . . ብለህ አንገቷን ቀጥለው" አለው::
+እንዳለው ቢያደርግ የሞተችው አፈፍ ብላ ተነሳች::
ይህንን ተአምር ያዩ አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል::
=>ከሐዋርያው በረከት ይክፈለን::
=>ሰኔ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
2.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
3.ቅዱሳን ሐዋርያት
4.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
5.ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ
6.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
7.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
8.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘምስር (ሰማዕት)
9.አባ ከላድያኖስ ሊቀ ዻዻሳት
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ አበው ጎርጎርዮሳት
2፡ አባ ምዕመነ ድንግል
3፡ አባ ዓምደ ሥላሴ
4፡ አባ አሮን ሶርያዊ
5፡ አባ መርትያኖስ
6፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል
=>+"+ ስለ ጽዮን ዝም አልልም . . .
አሕዛብም ጽድቅሽን: ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ::
የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም
ትጠሪያለሽ::
በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል በአምላክሽም እጅ
የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ:: +"+ (ኢሳ. 62:1-3)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር>>>
5 months ago | [YT] | 12
View 0 replies
wendmieneh
👉👉🌹🌹 ሰኔ ፳ [20] ቀን 🌹🌹
†#እንኳን_ለእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ ሕንጸተ ቤታ (ሕንጸታ) በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †
†በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
† #በዓለ_ሕንጸታ †
† በዚሕች ቀን : በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በአምላክ እናት ስም ታንጻለች::
ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን "ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕበ" [አሕብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ] [ማቴ.፳፰፥፲፱] (28:19) ባላቸው ቃል መሠረት ዓለምን በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል::
የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና [ዮሐ.፮፥፶፮] (6:56) አበው ሐዋርያት ቁርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር::
በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን: ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲሕ ይከናወን ነበር:: ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኩራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአብ ያመኑ ሰዎች ቁጥር እጅጉን በዛ::
በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ:: በዚሕ ምክንያት መምሕራን ሕዝቡን "ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?" ቢሏቸው "እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት እንደሆን የለን" ሲሉ መለሱላቸው::
ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ጳውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች "ለምን አናንጽም" ብለው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ግን "ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም" አለ:: [ለዚሕ ነው ዛሬም ሊቀ ጳጳስ ካልፈቀደ ቤተ ክርስቲያን የማይታነጸው::]
ከዚያ ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ጴጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱም "የጌታችን ፈቃዱ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ" ብሎ አዋጅ ነገረ::
በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔአቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ::
ሁሉንም ሐዋርያት በደመና ጭኖ ፊልጵስዩስ አደረሳቸው:: ከከተማ ወጣ ብሎ ባለ መሬት ላይም "ቤተ ክርስቲያንን በእናቴ ስም አንጹ" ብሎ አዘዛቸው:: ለቅዱስ ጴጥሮስም ሦስት ዓለቶችን ሰጠው::
እነዚያን መሬት ላይ ተክሎ : ጌታችን ቆሞለት : ሐዋርያቱ እየተራዱት : ግርምት የምትሆን ሦስት ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን በ52 ዓ/ም በዚህች ቀን አንጿል::
ቤተ ክርስቲያኗን ነገ ጌታችን ቀደሳት የምንል ነንና ይቆየን::
† አምላካችን የድንግል እናቱን ፍቅር : የተቀደሰች ቤቱን ጸጋ : የቡሩካን ሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን::
† ሰኔ ፳ [ 20 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
፫. ቅዱሳን ሐዋርያት
፬. ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ [ዕረፍቱ]
† ወርኀዊ በዓላት
፩. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት [ሰማዕት]
፪. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፫. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
፬. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
፭. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
፮. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
† "በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" † [፪ቆሮ. ፲፩፥፳፫-፳፰]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክብር †
† † †
5 months ago | [YT] | 10
View 0 replies
wendmieneh
👉🌹🌹 ሰኔ ፲፱ [19] ቀን 🌹🌹
†#እንኳን_ለሐዲስ_ሰማዕት_ቅዱስ_ጊዮርጊስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †
† #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሐዲስ †
ሰማዕቱ የተወለደው በምድረ ግብጽ አሕ [ተንት] በሰለጠኑበት የመጀመሪያው ዘመን ነበር:: በተለይ ተንቱ ግብፅና ሶርያን ከያዙ በሁዋላ ባልተጠበቀ ፍጥነት በኃይልም በሰውም ተደራጅተው ነበር:: ቅዱስ ጊዮርጊስ [ልብ በሉልኝ ሊቀ ሰማዕታት አይደለም] የተወለደው በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር::
እናቱ የተመሠከረላት ክርስቲያን ብትሆንም እንዳለመታደል አባቱ ተንባላታዊ [አ] ነበር:: ስሙንም መዛሕዝም ይሉታል:: ሕጻኑ እንደተወለደ ያወጡለት ስም አባዊ ከመሆኑ ባለፈ በሰዓቱ መጠመቅ አልቻለም:: የወቅቱ ሕግ ከወላጆቹ አንዱ አዊ ከሆነና አጠምቃለሁ ቢባል የሚከተለው ሰይፍ ነበር:: በዚሕ ምክንያት ሳይጠመቅ ፯ [7] ዓመት ሞላው::
እናቱ ግን ሕጻን ቢሆንም ፍቅረ ክርስትናን ታስተምረው ነበር:: ባይጠመቅም ጸበሉን: እመቱን ትቀባው ነበር:: ደብቃ ቅዳሴ ታሰማውም ነበር:: አንድ ቀን ግን ሕጻናት ሲቆርቡ አይቶ ካልቆረብኩ ብሎ አለቀሰ:: ምን ታድርገው? ወደ ውጪ አውጥታ ከአውሎግያ [የሰንበት በረከት] አበላችው:: "ጌታየ! ልጄን እርዳው" አለች::
ልክ በአፉ ሲቀምሳት መዓዛ መንፈስ ቅዱስ አደረበትና ፍጹም ተደሰተ:: ትንሽ ከፍ ሲል ለምን እንደማይጠመቅና እንደማይቆርብ እናቱን ጠየቃት:: "ልጄ ሆይ! ይገድሉሃል" አለችው:: ከዚህች ቀን ጀምሮ የሚጠመቅበትን ዘዴ ይፈልግ ጀመር::
አስቀድሞ ትምሕርተ ክርስትናን ተማረ:: ለአካለ መጠን ሲደርስ አፈላልጐ ጠንካራ ክርስቲያን የሆነች ሴት አገባ:: ጥቂት ጊዜ ከቆየ በሁዋላ ሚስቱን ስለ መጠመቅ አማከራት:: "ሌላ ሃገር ሒደህ ተጠመቅ" አለችው:: ከግብፅ ተነስቶ ሶርያ ገባ:: አባቶችን አፈላልጎ ተጠመቀ:: ቀጥሎም መንገዱን ወደ ልዳ አደረገ::
ወደ ደብሩ ተጠግቶ አባቶችን "ስም አውጡልኝ" ቢላቸው መንፈስ ቅዱስ አናግሯቸው "ጊዮርጊስ" አሉት:: እሱም ደስ እያለው: ባጭር ታጥቆ የልዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያገለግለው ገባ:: ትንሽ ቆይቶ ሁከት መንፈሳዊ ተሰማው:: ማለትም ስለ ሃይማኖቱ ደሙን ማፍሰስ ፈለገና ወደ ግብፅ ተመለሰ::
በዚያ ያሉ አ በክርስትና ስም: ልብስና ሞገስ ሲመለከቱት ተበሳጩ:: ዕለቱኑ አሠሩት:: ሌሊት እናቱና ሚስቱ መጥተው አሉት:- "አደራ! ፍቅረ ዓለም እንዳያታልልህ:: ሰማዕት ብትሆን ላንተም ክብር: ለእኛም ሞገስ ነው" ብለውም አጽናኑት:: [እንዲሕ ያሉ እናትና ሚስት ማግኘትም ታላቅ እድል ነው!!!]
ሐዲስ ጊዮርጊስም ጸና:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ደበደቡት: አካሉን ቆራረጡት: ደሙንም መሬት ላይ አንጠፈጠፉት:: በየመንገዱ እየጎተቱ ተሳለቁበት:: እርሱ ግን ክርስቶስን ወዷልና ሁሉን ታገሰ:: ሌሊት በሆነ ጊዜም ጌታችን ተገልጦ "ከሰማዕታት ተቆጠርህ" አለው::
በማግስቱ በአደባባይ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት:: ክፋታቸው የጸና ነውና ሥጋውን በእሳት አቃጠሉት:: ወደ ባሕርም ጣሉት:: እናቱ ከባሕር ስታወጣው ግን ምንም አላገኘውም ነበር:: በዚሕች ቀን እናቱና ሚስቱ በክብር ቀብረውታል::
ቸሩ አምላክ ከሰማዕቱ ጽናትን: ትእግስትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን::
† ሰኔ ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ ሰማዕት
፪. አባ ብሶይ አኖብ ሰማዕት [በአንበሳ ጀርባ ላይ የተቀመጠ አባት]
፫. ቅዱሳን ፭ቱ "5ቱ" ጭፍሮች [በብዙ ስቃይ ሰማዕት የሆኑ ባልንጀሮች]
፬. አባቶቻችን የደብረ ቁዋዐት ጻድቃን
† ወርሐዊ በዓላት
፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
፫. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ
፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
"ስለዚሕ ወንድሞቼ_ሆይ! ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና::" [፩ቆሮ.፲፥፲፬-፲፰] (10:14-18)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክብር †
† † †
#ፐጁን #subscribers_like_share_copylink እያደረጋቹኝ አበረታቱኝ 💕🙏💕
5 months ago (edited) | [YT] | 12
View 0 replies
wendmieneh
👉👉🌹🌹 ሰኔ ፲፰ [18] ቀን 🌹🌹
† #እንኳን_ለጻድቅ_ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_ድምያኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
† #አባ_ድምያኖስ †
† አባ ድምያኖስ ተወልደው ያደጉት ግብጽ ውስጥ ነው:: ቤተሰቦቻቸው ክርስቲያኖች በመሆናቸው ገና በልጅነት ዕድሜአቸው ቅዱሳት መጻሕፍትንና በጐ ምግባራትን ተምረዋል:: ዕድሜአቸው ወደ ወጣትነቱ ሲጠጋ ሥርዓተ መነኮሳትን ለማጥናት ወደ ገዳመ አባ ዮሐንስ ሔዱ:: በዘመኑ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ፈተና ሳያልፍ እንዲመነኩስ አይፈቀድለትም ነበር::
አንድ ሰው ሊመነኩስ ካሰበ በትክክል መናኝ መሆኑ ቢያንስ ለሦስት ቢበዛ ደግሞ ለአሥራ ሁለት ዓመታት እንዲፈተን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታዝዛለች:: ይኸውም "ሥርዓተ አመክሮ" ይባላል:: ከአሥራ ሁለት ዓመታት በላይ መቆየት ከፈለገ ግን ይፈቀድለታል::
በዚህም መሠረት አባ ድምያኖስ ለአሥራ ሰባት ዓመታት በአጭር ታጥቀው ገዳሙን አገልግለዋል:: ገዳሙም ይገባሃል በሚል ዲቁና እንዲሾሙ አድርጓል:: ከዚህ በኋላ ከአባቶች ተባርከው: ገዳሙንም ተሰናብተው ወጡ:: ነገር ግን የወጡት ወደ ዓለም ሳይሆን ራቅ ወዳለ ገዳም ነው::
የረድዕነት ዘመናቸውን ጨርሰዋልና አዲስ በሔዱበት ገዳም ወደ መደበኛው ገድል ተሸጋገሩ:: ያም ማለት በጾም: በጸሎት: በስግደት: በትሕርምት: በትሕትናና በፍቅር ሙሉ ጊዜአቸውን ማሳለፍ ጀመሩ:: በእንዲሕ ያለ ግብርም ዘመናት አለፉ::
የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ አባ ጴጥሮስ በእረኝነት ሥራ የሚያግዛቸው ሰው እንዲፈለግላቸው በጠየቁት መሠረት ትምሕርትም: ጽሕፈትም: በጐ ምግባራትም የተሟላለት ሰው እንደ አባ ድምያኖስ አልተገኘምና ያለፈቃዳቸው ወደ እስክንድርያ ተወስደው የፓትርያርኩ ረዳት ሆነው ተሾሙ:: በረዳትነት በቆዩበት ጊዜ በወንጌል አገልግሎትና በመንኖ ጥሪት ሕዝቡንና ሊቀ ጳጳሳቱን አስደስተዋል::
ልክ አባ ጴጥሮስ ሲያርፉ ሕዝቡና ሊቃውንቱ በአንድ ድምጽ አባ ድምያኖስን ለፓትርያርክነት መርጧቸዋል::
ጻድቁ ሊቀ ጳጳሳት በዘመነ ፕትርክናቸው ከግል የቅድስና ሕይወታቸው ባለፈ እነዚህን ፈተናዎች በመወጣታቸው ይመሰገናሉ::
፩. ሕዝቡ ከሃይማኖታቸው እንዳይወጡና በምግባር እንዳይዝሉ ተግተው አስተምረዋል::
፪. በአካል ያልደረሱባቸውን በጦማር [በመልዕክት] አስተምረዋል::
፫. በዘመናቸው የተነሱትን መ ተከራክረው : የተመለሰውን ተቀብለው : እንቢ ያሉትን አውግዘዋል::
፬. ከአንጾኪያ ፓትርያርክ የመጣውን የኑ ጦ [መልዕክት] በይፋ ተቃውመው አውግዘዋል::
ለአርባ ሦስት ዓመታት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ሆነው ያገለገሉት አባ ድምያኖስ ከብዙ ትጋት በኋላ በመልካም ሽምግልና በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: ከግብጽ አበው ሊቃነ ጳጳሳት ዝርዝር ውስጥም አርባ አምስተኛ ሆነው ተመዝግበዋል::
† ልመናቸው : ክብራቸው : ጸጋ ረድኤታቸው አይለየን::
† ሰኔ ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩. አባ ድምያኖስ ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት
፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
† ወርኀዊ በዓላት
፩. ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት [ረባን]
፫. አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
፬. ማር ያዕቆብ ግብጻዊ
† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት : ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" † [ሐዋ. ፳፥፳፰]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክብር †
† † †
5 months ago | [YT] | 14
View 0 replies
wendmieneh
👉🌹🌹 ሰኔ ፲፯ [17] ቀን 🌹🌹
#እንኳን_ለአባ_ገሪማ_ይስሐቅ_መደራ_ለአባ_ለትጹን_የዋህ_እና_ለአባ_ዸላሞን_ፈላሲ የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት አደረሳችሁ።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
✞ #አባ_ገሪማ_ይስሐቅ_መደራ ✞
አቡነ ገሪማ የተወለዱት በ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን ሮም ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸው መስፍንያኖስና ሰፍንግያ እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ:: ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑ፡፡
እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን ይስሐቅ ብለው አሳደጉት:: ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ:: ለ፯ [7] ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ: መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል::
አንድ ቀን ግን ከግብፅ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው:: ላኪው አባ ዸንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና" የሚል ነበር::
ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ:: ድንገት ግን ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ ዸንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው::
እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው አመነኮሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ ኢትዮዽያ መጡ:: ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና ታላቁ አባ ይስሐቅ [ገሪማ] ናቸው:: ሰውነታቸውን በገድል ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር::
አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው አባ ዸንጠሌዎን አዘኑ:: ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ የሰማውብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ" አሉ:: አባ ይስሐቅ ግን "ሰዎች ብቻ አይደሉም: ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ ፰ መቶ ሜትር [800 ሜትር] ተጠራርጎ ሸሸ::
ይሕንን የተመለከቱት አባ ዸንጠሌዎን "ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ [ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ] አሏቸው:: ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "አቡነ_ገሪማ" ተብለው ቀሩ፡፡
አቡነ ገሪማ ወደ መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ" እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል::
ጻድቁ ወንጌልን: ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል :-
፩. ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር "በጽባሕ
ይዘርዕ: ወበሠርክ የአርር" እንዲል::
፪. ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር::
፫. አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ::
፬. ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች::
፭. አንድ ቀን ድርሳን እየደረሱ ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይን
አቁመዋታል::
ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በኋላ ጌታችን ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው:: "ስምሕን የጠራ: መታሰቢያህን ያደረገ: እስከ ፲፪ [12] ትውልድ እምርልሃለሁ:: አንተ ግን ሞትን አትቀምስም" ብሏቸው ተሰወረ:: ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ ብሔረ ሕያዋን አድርሰዋቸዋል፡፡
✞ #አባ_ለትጹን_የዋህ ✞
ስመ ጥሩ ጻድቅ አባ ለትጹን በ፬ [4] ኛው መቶ ክ/ዘመን በግብጽ የተወለዱ:
- በፍጹም ተግሣጽ ያደጉ:
- ከልጅነታቸው ጀምሮ ራሳቸውን በሕገ ወንጌል የመሩ:
- አንድ ቀን በሰሟት የወንጌል ቃል የመነኑ:
- ገዳም ገብተው በትሕትና ለዘመናት ያገለገሉ:
- በመጨረሻም ወደ ትልቅ ተራራ ወጥተው ተጋድሏቸውን
የፈጸሙ ታላቅ አባት ናቸው::
ከየዋሕነታቸው የተነሳ ኃጢአተኛ ሰው ሲያገኙ ራሳቸው ንስሃ ይገቡ ነበር:: አንዴ ግን እናቱን ፲ [10] ጊዜ በዝሙት ያረከሰ: ስትጸንስም መርዝ አጠጥቶ ጽንሱን በማሕጸኗ የገደለና በሥጋ ወደሙ ላይ የተዘባበተ ሰው ሊሞት ሲል ደረሱ::
አጋንንት ሲዖል ታች ሲጥሉትም ተመለከቱ:: ኃጢአቱ ጭንቅ ቢሆንም የእርሱን ንስሃ ሊቀበሉ ጀመሩ: ከንስሃቸው ጽናት የተነሳ ሞቱ:: ጌታችን ከሞት አስነስቶ "አትለምነኝ: አልምረውም" አላቸው::
ጻድቁ ተስፋ አልቆረጡምና ቀጠሉ:: ለ፪ [2] ኛ ጊዜ ሞቱ:: አሁንም ቀጠሉ: ፫ [3] ኛ: ፬ [4] ኛ: ፭ [5] ኛ ጊዜም ሞቱ:: በ፮ [6] ኛው ግን መፍትሔ መጣ:: ጌታችን አእላፍ መላእክትን አስከትሎ: ያችንም ኃጥእ ነፍስ ይዞ መጣ:: "ፍርዴ አይታጠፍምና ወደ ገነት አላስገባትም:: ስለ አንተ ጽድቅና የዋሕነት ደግሞ ሲዖል አልጥላትም:: ስለዚሕም እንዳልተፈጠረች ትሁን" ብሎ እፍ አለባት:: ፈጥና ወደ ትቢያነት ተቀየረች::
ጻድቁም የፈጣሪያቸውን ቸርነት አድንቀው ሰገዱ:: ከብዙ ዘመናት ተጋድሎ በኋላም በዚህች ቀን ዐረፉ::
✞ #አባ_ዸላሞን_ፈላሲ ✞
ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው ታላላቅ ገዳማውያን አንዱ አባ ዸላሞን የአባ ለትጹን ወዳጅ ነበር:: ይሕ ቅዱስ ከአጋንንት ጋር በገጠመው ጦርነት ምክንያት ለየት ይላል:: ከ፷ [60] ዓመታት በላይ እንኳን ሳቅና ደስታ ቀና ብሎም ሰው አላየም::
በነዚሁ ዘመናት ሁሉ ቅንድቡ እስኪላጥ አልቅሷል:: በዓለም ያሉ አጋንንት ሁሉ ተሰብስበው አሰቃይተውታል:: እርሱ ግን በእግዚአብሔር ቸርነት: በወዳጁ በአባ ለትጹን ጸሎትና በትጋት አሸንፏቸው ዛሬ ዐርፏል::
ቸሩ አምላካችን ከታላላቁ ቅዱሳን ጸጋ በረከት ይክፈለን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን::
† ሰኔ ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩. ብጹዕ አባ ገሪማ [ይስሐቅ] ዘመደራ
፪. አባ ለትጹን ዐቢይ ወየዋሕ
፫. አባ ዸላሞን ፈላሲ
፬. ቅድስት አርሴማ ጻድቅት
፭. ሰማዕታት እለ አኮራን
፮. ፯፼ ፹፻ ሰማዕታት ማኅበረ ቅዱስ ተክለሃ ይማኖት
† ወርኃዊ በዓላት
፩ ፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት
፪ ፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ዘቆጵሮስ
፫ ፡ ቅዱሳን መክሲሞስ ወደማቴዎስ
፬ ፡ ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ
" እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል. . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም:: " [መዝ. ፴፮፥፳፰-፴፩] (36:28-31)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክብር †
† † †
5 months ago | [YT] | 22
View 0 replies
Load more