Kirub Tube - ኪሩብ ዩቲዩብ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የአብ ጸጋ የወልድ ቸርነት የመንፈሰ ቅዱስ ሕብረት አንድነት የእመቤታችን ምልጃ ከሁላችን ጋራ ይሁን። ባላችሁበት ሁሉ ሰላመ እግዚአብሔር አይለያችሁ። አገራችንንም አለማችንንም ሰላም ያድርግልን። ይህንን የዩቱብ ቻናል ለምትከታተሉ ሁሉ ፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ስርዓት ትምህርት ይሰጥበታል የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይነገርበታል ትምህርተ ሃይማኖት፣ ነገረ ቅዱሳን ይሰበክበታል የመንፈሳዊ እድገት፣ ግብረገብነትና ስነምግባር ትምህርትና ምክር ይሰጥበታል እንዲሁም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምሥጢር የምንማርበት ቻናል ነው። የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችህን ጋር ይሁን።

Subscribe, Like, Share በማድረግ እያበረታቱን ስለሆነ እናመሰግናለን::

In the name of the Father, the Son, and the Holy Spirit, one God, Amen. May God grant you peace wherever you are. May he grant peace to our country and our world. To all who follow this YouTube channel: - The Ethiopian Orthodox Church teaches the faith and system, the history of the Ethiopian Church, teaches religious doctrine, preaches about the saints, teaches and advises on spiritual growth, morality, and ethics, and is a channel where we learn the secrets of Orthodox Tewahedo. May the peace of God be with you all.


Kirub Tube - ኪሩብ ዩቲዩብ

‹‹ጥቅምት 5›› አባታችን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የእረፍት በዓላቸው ነው።

አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐገራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡

አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች፡፡

በዚህ መሠረት ቅዱስ አባታችን ጻድቁ አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ፡፡

አባታችን ዓይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ተነስተው «ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን» ብለው አመስግነዋል።

በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን ይመስላሉ፡፡

አባታችን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማጸነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል፡፡

ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው። ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ።

የጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ በረከታቸው አይለየን🙏

2 months ago | [YT] | 5