🍹በታክስ ጉዳይ ማብራሪያ ከፈለጉ 0936-59-58-58 ምንም ነገር ቢሆን ያወኩትን አንድም ሳላስቀር ለናንተ አሳውቃለሁ። የኑፉግነት መጀመሪያ የሚያውቁትን ለሌች አለማሳወቅ ነው።
🍹በቻናላችን ትምህርቶች ከተደሰቱ እና እኛን ለማበርታታት ከፈለጉ በቴሌ ብር 0936-59-58-58 ውይንም
በ፥- ko-fi.com/hanitube

Welcome to Hanitube – Your Ultimate Resource for Ethiopian Accounting and Taxation!
🌍 About Us:
At Hanitube, we provide comprehensive tutorials and insights into the Ethiopian tax system, accounting principles, and Peachtree/Sage 50 software. Whether you are a beginner or a seasoned professional, our channel is designed to help you navigate the complexities of accounting and taxation in Ethiopia.

📚 What You’ll Learn:
🟡 Ethiopian Tax Laws: Understand the latest tax regulations and compliance requirements.
🟡 Accounting Courses: Gain foundational knowledge in accounting principles and practices.
🟡 Peachtree/Sage 50 Tutorials: Master this powerful accounting software with step-by-step guides.
#EthiopianTaxSystem #ታክስ #ግብር


Hani Tube

#ለንግድ ድርጅት ባለቤቶች፣ ለሂሳብ ባለሙያዎች እና ለአማካሪዎች በሙሉ!
የገንዘብ ሚኒስቴር ለዓመታት በርካታ ቅሬታዎች ሲነሱበት የነበረውን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008ን ለማሻሻል አዲስ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቷል። ይህ ማሻሻያ በኢትዮጵያ የንግድና የግብር ሥርዓት ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።


በሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሕግ አማካሪ በአቶ ዋሲሁን አባተ የቀረቡት ዋና ዋና ለውጦች ምን ምን ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሊደረጉ የታሰቡ ለውጦች በዝርዝር አቅርበንላቹዋል መልካም ንባብ


🔹 የ50% እና 75% የታክስ ይግባኝ ዋስትና ክፍያ ቀረ? በአዲሱ ረቂቅ ታክስ ባለሥልጣኑ በሚሰይመው ገለልተኛ ተቋም በሽምግልና የመጨረስ አዲስ አማራጭ ተፈጥሯል።
🔹 የታክስ ክሊራንስ እና የባንክ ብድር፦ ክርክር ያለበት ግብር ከፋይ ከባንክ ብድር ማግኘት የሚችልበት አዲስ አሠራር ተዘርግቷል።
🔹 ወደኋላ ተመልሶ ግብር የመጠየቅ የጊዜ ወሰን (Limitation Period)፦ ሰነድ ለሌለው ግብር ከፋይ እፎይታ የሚሰጥ የ5 እና የ10 ዓመታት ግልጽ ወሰን ተቀምጧል።
🔹 የደረሰኝ አለመስጠት ቅጣቶች ዳግም ተቃኝተዋል፦ በእያንዳንዱ ደረሰኝ 100,000 ብር አስተዳደራዊ ቅጣት እና የሥራ አስኪያጆች ተጠያቂነት ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች።
🔹 የትርፍ ክፍያ (Dividend) ወደ ውጭ ስለመላክ እና ሌሎችም…
ይህ ማሻሻያ የእርስዎን የንግድ እንቅስቃሴ ወይም የሂሳብ አያያዝ ሥራ እንዴት ያቀልለዋል?


👇 የማሻሻያውን ሙሉ ዝርዝር እና ትንታኔ አሁኑኑ ድረ-ገጻችን ላይ ገብተው ያንብቡ፦


🔗 hanitube.com/new-ethiopian-tax-administration...
#EthiopiaTax #TaxAmendment #HaniTube #EthiopianBusiness #TaxLaw #AccountingEthiopia #የታክስአስተዳደርአዋጅ

1 month ago | [YT] | 23

Hani Tube

የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባን ስለመሰረዝ ማወቅ ያለብዎት ወሳኝ ነጥቦች ምን መሆን እንዳለበተ ከተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ አንጻር በዚህ ጽሁፍ ተብራርቱዋል ለወዳጆ ሼር ያድርጉ !

ብዙ ጊዜ የንግድ ስራ ሲቆም ወይም የታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ማከናወን ሲቆም፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ስረዛን በወቅቱ አለመፈጸም እና በዘፈቀድ ንግዱን ስላቆምኩ ወይም የታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ማከናወን ስላቆምኩ ከታክሱ ነጻ ነኝ በሚል መቀመጥ ለከፍተኛ አስተዳደራዊ መቀጫ ይዳርጋል።

በመሆኑም በኢትዮጵያ የታክስ ህግ መሠረት ስለ VAT ምዝገባ ስረዛ ማወቅ ያለብዎት ዋና ዋና ነጥቦች፦

1. የማሳወቅ ግዴታና የጊዜ ገደብ 🗓️

ማንኛውም የተመዘገበ ሰው ታክስ የሚከፈልበትን አቅርቦት ማከናወን ሲያቆም፣ ስራውን ካቆመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ቀናት ውስጥ ለታክስ ባለስልጣን ማሳወቅ አለበት።

ይህ ደግሞ በግልጽ በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 አንቀጽ 22 ላይ ተደንግጉዋል።

2. ባለስልጣኑ በራሱ አነሳሽነት ምዝገባን ስለመሰረዝ 🧐

አንድ ሰው ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 6 ወራት ምንም አይነት ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ካላከናወነ፣ ባለስልጣኑ ምዝገባው እንዲሰረዝ የመወሰን ስልጣን አለው።

3. ምዝገባ ስለተሰረዘ የታክስ ዕዳ ይቀራል? 🚫

አይቀርም!

የምዝገባ መሰረዝ ቀደም ብሎ ግዴታን ባለመወጣት የሚጣሉ መቀጫዎችን አያስቀርም።

እንዲሁም ምዝገባው ከተሰረዘ በኋላ እንኳ ያልታወቀ የታክስ ዕዳ ከተገኘ፣ ባለስልጣኑ በማንኛውም ጊዜ ታክሱን ከነመቀጫው የመጠየቅ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

4. ማመልከቻው ምን መያዝ አለበት? 📝

ማሳወቂያው በባለስልጣኑ የተፈቀደውን ቅጽ በመጠቀም መቅረብ ያለበት ሲሆን፤

🧿ስራው የቆመበትን ትክክለኛ ቀን፤
🧿በሚቀጥሉት 12 ወራት ውስጥ ወደ ስራ የመመለስ ፍላጎት መኖር ወይም አለመኖሩን መግለጽ ይኖርበታል።

5. ስረዛው የሚጸናው መቼ ነው? ✅

የምስክር ወረቀቱን ለመሰረዝ የተሰጠ ውሳኔ ተፈጻሚ የሚሆነው፦

👣 ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ከቆመበት የሂሳብ ጊዜ የመጨረሻ ቀን፣ ወይም
👣በስረዛው ማስታወቂያ ላይ በግልጽ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ ዋና ዋና የህግ ማጣቀሻዎች ቀጥሎ የተጠቀሱ ህጎችን ይመልከቱ ፦
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016
የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008
የፌዴራል የታክስ አስተዳደር ደንብ ቁጥር 407/2009

Hani Tube መጋቢት 23/2018

#EthiopianTax #VAT #TaxLaw #BusinessTips #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ታክስ #VATDeregistration #የታክስህግ

3 months ago | [YT] | 13

Hani Tube

5 months ago | [YT] | 3

Hani Tube

ጥያቄ፦ "ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት" ሲባል የዕቃ ሽያጭን ብቻ ነው የሚመለከተው? 🤔

5 months ago | [YT] | 13

Hani Tube

ሁሉም ነገር ላይ ቫት (VAT) ይከፈላልን? 🤔

5 months ago | [YT] | 3

Hani Tube

#የተጨማሪ_እሴት_ታክስ
"ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት"-በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 መሠረት የሚከተለውን ትርጉም ይይዛል፦  ‪@Ethiopiatax‬ ​

🎯ከታክስ ነፃ ከተደረገ አቅርቦት ውጪ ሆኖ፣ ታክስ የሚከፈልበትን የሥራ እንቅስቃሴ በማከናወን ሂደት በኢትዮጵያ ውስጥ የተመረተ ዕቃ ወይም አገልግሎት አቅርቦት ፤ ወይም

🎯በአዋጁ ድንጋጌዎች መሠረት ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት እንደሆነ የሚቆጠር ማንኛውም አቅርቦት ነው።

🎯 በተጨማሪም "አቅርቦት" የሚለው ቃል በራሱ የዕቃ አቅርቦትን፣ የአገልግሎት አቅርቦትን ወይም በቀጥታ በታክስ ሕጉ መሠረት ታክስ የሚከፈልበትን ማንኛውንም አቅርቦት ያጠቃልላል።

ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ ደግሞ ማንኛውም ሰው በቋሚነት ወይም በየጊዜው ለሚያገኘው ዋጋ (ዋጋን በመጠየቅ) በሙሉ ወይም በከፊል ዕቃ ወይም አገልግሎት ለማቅረብ የሚያደርገው እንቅስቃሴ መሆኑን በዚህ በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ላይ ተደንግጉዋል ።

🎯ከታክስ ነፃ ከተደረገ አቅርቦት ውጪ ሆኖ፣ ታክስ የሚከፈልበትን የሥራ እንቅስቃሴ በማከናወን ሂደት በኢትዮጵያ ውስጥ የተመረተ ዕቃ ወይም አገልግሎት አቅርቦት ፤ ወይም


🎯በአዋጁ ድንጋጌዎች መሠረት ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት እንደሆነ የሚቆጠር ማንኛውም አቅርቦት ነው።

🎯 በተጨማሪም "አቅርቦት" የሚለው ቃል በራሱ የዕቃ አቅርቦትን፣ የአገልግሎት አቅርቦትን ወይም በቀጥታ በታክስ ሕጉ መሠረት ታክስ የሚከፈልበትን ማንኛውንም አቅርቦት ያጠቃልላል።

ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ ደግሞ ማንኛውም ሰው በቋሚነት ወይም በየጊዜው ለሚያገኘው ዋጋ (ዋጋን በመጠየቅ) በሙሉ ወይም በከፊል ዕቃ ወይም አገልግሎት ለማቅረብ የሚያደርገው እንቅስቃሴ መሆኑን በዚህ በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ላይ ተደንግጉዋል ።
#Ethiopiatax #vat

5 months ago (edited) | [YT] | 9

Hani Tube

አንድ ነጋዴ ለዓመታት ግብር ሳይከፍል ቆይቶ፣ አሁን ንግዱን ሊዘጋ ሲል ከፍተኛ ቅጣት ተጣለበት። ነጋዴው "አላውቅም ነበር" የሚል መከላከያ አቀረበ። እናንተ ምን ትላላችሁ?

6 months ago | [YT] | 9

Hani Tube

መኪናዎን ወይም ንብረትዎን ለአንድ ቀን ማከራየት የታክስ ግዴታ ያስከትላል?

#Ethiopia_Tax

ብዙዎቻችን ለግል መገልገያነት የምንጠቀምበትን መኪና ለሰርግ ወይም ለልዩ አጋጣሚዎች ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን አከራይተን ተጨማሪ ገቢ ልናገኝ እንችላለን። በዚህ ጊዜ "የንግድ ፈቃድ የለኝም፤ ስራውም ቋሚ አይደለም" በሚል ግብር የመክፈል ግዴታ የሌለብን ሊመስለን ይችላል። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው! ።በኢትዮጵያ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 መሠረት፣ ማንኛውም ገቢ ያገኘ ሰው ግብር የመክፈል ግዴታ አለበት። ለዚህ ዓይነቱ "አልፎ አልፎ" የሚገኝ የኪራይ ገቢ አዋጁ ልዩ ድንጋጌ አስቀምጧል።

1. "አልፎ አልፎ ሀብትን ማከራየት" (Casual Rental of Property) ምንድን ነው?

በአዋጁ አንቀጽ 58 መሠረት፣ አንድ ሰው የንግድ ሥራ ፈቃድ ሳይኖረውና ሥራውን በቋሚነት ሳይያያዘው፣ አልፎ አልፎ ንብረቱን (መኪና፣ ድንኳን፣ መሣሪያዎች...) በማከራየት የሚያገኘው ገቢ በዚህ ምድብ ይጠቃለላል።

2. የግብር መጠኑ ስንት ነው?

በዚህ መልኩ ለሚገኝ ገቢ የሚጣለው የግብር መጠን የጠቅላላ ገቢው 15% (15% of Gross Income) ነው።
ለምሳሌ፦ መኪናዎን ለሰርግ በ 10,000 ብር ካከራዩ፣ 1,500 ብሩን ለታክስ ባለሥልጣኑ ገቢ ማድረግ ይኖርብዎታል።

3. የታክስ አስተዳደሩ እንዴት ነው?

ግብር ከፋዩ ይህንን ገቢ በራሱ አሳውቆ ግብሩን የመክፈል ኃላፊነት አለበት። "አነስተኛ ገቢ ነው" በሚል ግብሩን ሳያሳውቁ መቅረት ግን የሚከተሉትን ከባድ መዘዞች ያስከትላል፦
የአስተዳደር ቅጣትና ወለድ፦ ታክሱ በወቅቱ ካልተከፈለ ወለድና መቀጮ ይታሰብበታል።
የወንጀል ተጠያቂነት፦ግብርን መደበቅ ወይም መሰወር በሕግ ያስቀጣል።

ለተጨማሪ የታክስ ትምህርቶች ገጻችንን Like እና Follow ያድርጉ!
#EthiopiaTaxAcademy #TaxEducation #CasualRental #EthiopianTaxLaw #IncomeTax #TaxAwareness

6 months ago | [YT] | 16