Healthy Africa Insight

Welcome to Healthy Africa Insights!
We share inspiring stories, data-driven facts, and real-life lessons from across Africa — focusing on maternal health, child well-being, nutrition, and community success.
Our goal is to turn numbers into stories that change lives.

🎥 New videos three days a week
Subscribe and be part of Africa’s healthy future. 🌍💚


Healthy Africa Insight

ዛሬ ህዳር 14 የአለም የስኳር ህመም ቀን ነው።

የስኳር በሽታ በሁሉም የሕይወት ደረጃዎች ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል።
የዘንድሮው የዓለም ጤና ድርጅት የዓለም የስኳር ህመም ቀን መሪ ቃል "በህይወት ደረጃ ያሉ የስኳር ህመምተኞች" የሚል ሲሆን እያንዳንዱ የስኳር በሽታ ያለበት ሰው ጤናን፣ ክብርን እና ራስን በራስ ማስተዳደርን የሚያበረታታ የተቀናጀ እንክብካቤ፣ ድጋፍ ሰጪ አካባቢዎች እና ፖሊሲዎች ማግኘት እንዳለበት ይገነዘባል።
የስኳር በሽታ በእያንዳንዱ የሕይወት ደረጃ ላይ ሰዎችን ሊጎዳ ይችላል; ከልጅነት እስከ እርጅና ድረስ የስኳር በሽታን የመከላከል እና የመንከባከብ ጥረቶች በህይወት ደረጃዎች ውስጥ መካተት አለባቸው; እና ደህንነትን እና እራስን መንከባከብ በእያንዳንዱ እድሜ ላይ የስኳር በሽተኞችን ያበረታታል።
የአለም የስኳር ህመም ቀን ስለ ስኳር በሽታ እንደ ወሳኝ የአለም አቀፍ የህዝብ ጤና ጉዳይ ግንዛቤን ለማሳደግ እድል ይሰጣል። በስኳር በሽታ ለተጠቁ ሁሉ ግንዛቤን በማሳደግ፣ እውቀትን በማስፋፋት እና ዘላቂ ለውጥ ለመፍጠር ያግዛል።

እኛ ሀገርም ዛሬ የተለያዩ ተቋማት ቀኑን ለመዘከር ነፃ የስኳር ምርመራ እና ህክምና እንደሚሰጡ የሚገልፅ ፖስት ሲያደርጉ አይቻለሁ። የሚበረታታና በሁሉም ተቋማት መለመድ ያለበት ነው ።


youtube.com/@healthyafricaininsight ላይ ሰብስክራይብ ማድረጉን አይርሱ።

10 months ago | [YT] | 0

Healthy Africa Insight

የአለም ጤና ድርጅት ( WHO) ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ትላንት November 12 የአለም የ2025 የሳምባ ነቀርሳ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። በሪፖርቱ መሰረት የሳምባ ነቀርሳ በ2024 ብቻ ከ1.2 million ሰዎችን ነፍስ የነጠቀን ሲሆን በአጠቃላይ በሳምባ ነቀርሳ የተጠቁ ሰዎች ብዛት ደግሞ ከ10 million በላይ እንደሚደርስ አሳውቋል።
ሆኖም ከcovid 19 ወረርሺኝ በሗላ አዲስ በTB ( የሳንባ ነቀርሳ) የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ሲሆን በተጨማሪም የሚመረሰሩ ሰዎች ብዛትም በዚያው ልክ በጣም ጨምሯል። ይሕም ከበሺታው አስከፊነት፣ በቀላሉ የመተላለፍ፣ እና በቀላሉም ልንከላከልው የምንችለው ከመሆኑ አንፃር ተስፋ ሰጪ ውጤት መሆኑን በሪፖርቱ ገልፀዋል።

እንዲሁም ለወጣቶች እና ለአዋቂዎች የሳንባ ነቀርሳን ሊከላከል ይችላል የተባለለት ክትባት መከኘቱን እና በቂ ጥናትና ሙከራ እየተደረገለት መሆኑን አብስረዋል።

ነገር ግን የሳንባ ነቀርሳ በሽታ በቀላሉ በትንፋሽ የሚተላለፍ ግዳያ እንደመሆኑ መጠን፤ የኛ ማህበረሰብ የአኗኗር ዘይቤ አስጊ ነው። የኛ ማህበረሰብ በአንዲት ትንሽ ክፍል ውስጥ ተቀላቅሎ የሚኖር፣ አንዲት ሲጋራ የሚቀባበል፣ በአንድ የውሀ ብርጭቆ ወይም ሀይላንድ የመጠቀም ልምድ ያለው ማህበረሰብ ስለሆነ በሽታው በቀላሉ ለመተላለፍ እድል ስለሚያገኝ በደምብ ሊታሰብበት ይገባል። በተጨማሪም ከውጭ ሀገር እስርቤት የቆዩ ቤተሰቦቻትን ሲመጡ በቂ ምርመራ እና ህክምና ሳይደረግላቸው ከህብረተሰቡ ጋር ስለሚቀላቀሉ በቀላሉ ለበሽታው ተጋላጭ የመሆን አጋጣሚዎች ይወዛሉና ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ ብንወጣ ለማለት ነው።

አመሰግናለሁ

Follow us on YouTube youtube.com/@Healthafricainsight

10 months ago | [YT] | 0